ታቦቱ ፊት መገደል መቼ ነው የሚያበቃው? – በቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

ታቦት በቆመበት ሰውን መግደል አዲስ የዘመኑ አሰቃቂ ወንጀል ነው። በቅ/እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን አንድ ባህታዊ ሕዝቡም ፓትርያርኩም በተሰበሰቡበት ከተገደሉ ወዲህ ታቦት አቁመን ሰው መግደልን፣ ለታቦት የሚገባውን ክብር መንፈግን እየተለማመድነው ነው። ከ1997 ዓ.ምሕረቱ ምርጫ ቀጥሎ በመጣው የጥምቀት በዓል ላይ አስለቃሽ ጢስ በመተኮስ ታቦቱን የያዙ ካህናት ላይ ሳይቀር ምን ያህል ወንጀል እንደተፈፀም እናስታውሳለን።

 

አሁን ይባስ ተብሎ በዓላቸውን ለማክበር የወጡ የወልዲያ ወጣቶች ላይ በጅምላ ተኩስ ብዙ ግድያ መፈፀሙ ይኸው እየታየ ነው። ከቅ/ሚካኤል ዕለት የጀመረው ግርግር አሁንም እንዳልቆመ እየሰማን ነው። የወልድያ ወጣቶች በምን ዓይነት ጥይት ተገደሉ? በክላሽ ወይስ መኪና ላይ በተጠመደ ከባድ መሣሪያ እና ከሕንጻዎች አናት ላይ በሚተኮስ የአልሞ ተኳሾች አረር የሚለውን አንስቼ ጉንጭ አልፋ ክርክር ማድረግ አልፈልግም። ይሁን እንጂ የወልዲያውን ግርግር የሚያሳይ ቪዲዮ ላይ የሚሰማው የጥይት ድምጽ የክላሽና የሽጉጥ ድምጽ እንዳልሆነ ግን ለመገመት ብዙም አይከብድም። ጥይት ሲተኮስ ሰምቶ የሚያውቅ ማንም ሰው ሊለየው የሚችለው ነገር ነው። (ዝረዝሩን ለሙያው ባለቤቶች ልተወው)

 

መጀመሪያውኑስ እንዲህ የታጠቀ እና ከባድ መሣሪያ ያለው «ጦር» መሐል አገር ምን ያደርጋል? አንደኛውኑ ሕዝቡ በጠላትነት ካልተፈረጀ በስተቀር። እነ እንቶኔ ሱቃችን ተቃጠለ የሚሉት ልቅሶ ሌላ ቂም በሰው ልቡና እንዲቋጠር ከማድረግ ያለፈ ምንም ትርጉም ያዘለ ሐሳብ ስላልሆነ ለውይይት እንኳን ላነሳው አልፈቅድም። ደግሞስ ድንጋይ ለወረወረብህና ለሰደበህ ሁሉ ጥይት በማጉረስ አገር ማስተዳደር የሚባል ፈሊጥ ከየት የመጣ ነው። በርግጠኝነት ይህ «ለድንጋይ ውርወራ ጥይት» መለወጥ የሚባል ነገር ያለው ሕዝቡ ሕዝብህ ካልሆነ ብቻ ነው።

 

ለዚህ ነው የዚህ ወንጀለኛ ፓርቲ አገዛዝ «አምባገነንነት» ሳይሆን «ቅኝ ገዢነት» ነው የምንለው። ልድገመው። አገሪቱን እያስተዳደራችሁ ያላችሁት እንደ ቅኝ ገዢ ኃይል ነው። አምባገነንነትን በዘመነ ደርግ እናውቀዋለን። በጅምላ መታሰርንና መገደልንም ቢሆን በዘመነ ደርግ እናውቀዋለን። አገራችን በደርግ የደረሰባት ቁስል መልኳን አስቀያሚ አድርጎታል። ነገር ግን እስከዚያ አስቀያሚነቷ መኖር ችላ ነበር። የዚህ ዘመኑ በሽታ ግን ቆዳን የሚቀይር የላይላይ በሽታ ሳይሆን ካንሰር ነው። ካንሰር ደግሞ ለጊዜም መቆጣጠር ይቻል ካልሆነ ዞሮዞሮ መግደሉ አይቀርም። አገራችንን የተጣባት ካንሰር ነው፡፡ ጥያቄው ካንሰሩ ተስፋፍቷል ወይስ በሰውነት ሙሉ አልተሰራጨም የሚለው ነው። ሥጋታችን መላውን ሰውነት ከሚያበላሽበትና ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ከሚገድልበት ደረጃ የደረሰ መስሎን ሁላችንም አዝነን ነበር። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነት እንዳልጠፉ፣ በወንዝና በቋንቋ ልዩነት እንዳልመከኑ ግን ዓይተን ደስታችንን አጣጥመን ሳንጨርስ ይህ ደስታ የማይመቸው አካል በውኃ ሊጠመቅ የወጣውን ምእመን በደም አጥምቆ ደስታችንን አደብዝዞታል።

 

በግፍ የተጨፈጨፉትን በሙሉ ነፍሳቸውን ይማርልን። መታወቅ ያለበት ነገር ግን ይህንን ግፍ መቸም አንረሳውም። ይቅር ብንላችሁም ግን አንረሳውም። ደግ ዘመን ሲመጣ ወልዲያም እነዚህን ልጆቿን የምትዘክርበት እና እንዲህ ያለው ግፍ እንዳይደገም ለስማቸው ምልክት የምታቆምበት ቀን ይመጣል። በታቦታችን ፊት መገደላችን የሚያበቃበት ዘመን ይመጣል። ይዘገያል እንጂ አይቀርም።

6 Responses to ታቦቱ ፊት መገደል መቼ ነው የሚያበቃው? – በቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ

 1. ታቦት ሥር መግደሉና መገደሉ የሚቆመው ታቦቱን የተሸከሙትና የበላይ “መንፈሳዊ” አለቆቻቸው ከተዘፈቁበት ሞራላዊና እምነታዊ ውድቀት ለመውጣት እና በዕዉነት ስለዕውነት መንፈሳዊ ተልኳቸውን ለመወጣት ፈቃደኝነቱና ድፍረቱ ሊኖራቸው ከቻሉ ብቻ ነው ። መደባበቅ የሚያስፈልግና የሚጠቅም አይደለምና የሃይማኖት መሪዎችና ሊሎችም አገልጋዮች ማስመሰሉን ትተው ሆነው እስከ አልተገኙ ድረስ ጨቃኝ ገዥዎች ገና ከቤተ መቅደስ አውጥተው ይገድላሉ ።

  T. Goshu
  January 22, 2018 at 9:20 pm
  Reply

 2. ረብሻውን ለማስጀመር ታቦት ተሸካሚን አባት በድንጋይ የጣሉ ጋጠወጥ
  ባለጌ ረብሸኞች እርሱ ይቀጣቸዋል ፡፡ አሜከላ ትውልድ የማንም መጠቀምያ ይሆናል ፡፡

  ነቄ
  January 23, 2018 at 10:47 am
  Reply

 3. እስልምናንም ለፖለቲካቸው ለመጠቀም ፈልገው የከሸፈባቸው የሻእቢያ አሽከሮች በሀይማኖት ተቋማት ዙርያ እንደ ጥንብ አንሣ እያንዣበቡ ነው ፡፡
  ስሜት ይኮረኩርልኛል ብለው ይሆን ቅቅቅቅቅቅ

  nana
  January 23, 2018 at 11:03 am
  Reply

 4. Good timely article & the answer is when the cruel, liars, looters & killers fascist minority weyanne Tigrean government ends & coming soon! Unless the Tigrean weyanne cruel minority government ends and buried for good the people of Ethiopian will never get peace and live in brotherhood regardless of their ethnic origin.

  Yared
  January 25, 2018 at 7:42 pm
  Reply

 5. “እነ እንቶኔ ሱቃችን ተቃጠለ የሚሉት ልቅሶ ሌላ ቂም በሰው ልቡና እንዲቋጠር ከማድረግ ያለፈ ምንም ትርጉም ያዘለ ሐሳብ ስላልሆነ ” ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ

  REMEMBER , THE WRITER IS A ቀሲስ.

  MR. FAKE PRIEST , HAVE GUTS TO CONDEMN LOOTING , KILLING AND BURNING BECAUSE OF RACE .

  FAKE PRIESTS
  January 26, 2018 at 3:27 am
  Reply

 6. ወያኔ የሚፈልግሽ ማንም የለም! ትግሉ ገና ተጀመረ እንጂ መች ተሟሟቀ! በተጋድሎ ለመሞት ሁሉም አማራ ይነሳል እመነኝ:: በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር አዲስ አበባዊ ገና ይነሳል:: ይህ ህዝብ አንዴ ሲወጣ መከላከል በፍጹም አይቻልም:: ይልቁን አወዳደቄን አሳምርልኝ ብለህ ጸልይ:: ምክንያቱም ወያኔ ከነግሳንግሱ ይደመሰሳል:: እኔ ምንግዜም የሚገርመኝ ነገር አለ: ኧረ እንዴት የዋህ ብንሆን ነው አዲስ አበባ ድረስ ሊመጡ የቻሉት? በዚህ ላይ ይሄን ሁሉ ዓመታት ሊቆዩ የቻሉት ምክንያቱ አንድ ና አንድ ብቻ ነው:: ይኸውም እኛ በረጅሙ ታሪካችን ማንኛውንም የውጭ ጠላት አርበድብደን ስለገረፍን ነው:: ይህንን ለመበቀል ከውጭ መምጣት ስለአልተቻለ የውስጥ ባንዳዎች ከአንድ አካባቢ ተመለመሉ:: መስፈርቱ ደግሞ የበታችነት ና ትንሽነት ስሜት የሚያጠቃው ስብስብ መሆን ነበረበት:: አንዳንድ ጅሎች እነኝህን ስብስብ አሁንም እንደ ኢትዮጵያዊ ሊቆጥሯቸው ይችላሉ:: ግን አይደሉም:: ልብ በሉ ቅድም እንዳልኩት የአዲስ አበባ 56% አማራ, 19% ኦሮሞ እና 16% ጉራጌ በአጠቃላይ 91% በአንዴ ይነሳል:: እና የተቀማውን የራሱን ከተማ መልሶ ይረከባል:: ያኔ እንኳን አጋዚ ማንም ሌላ የውጭ ኃይል ተጨምሮ ወያኔን አያድናትም:: ወያኔ በድል አድራጊነት የማትወጣው ጦርነት ውስጥ ገብታለች:: ምክንያቱም ሁሉም ነገር ትላንትና እንደነበረ ወደፊትም እንዲሁ የሚቀጥል ይመስላታል:: ግን እኮ የትላንትናው የሞት ፍርሃት ዛሬ የለም:: እንግዲህ ሞት ካልተፈራ ምን ይፈራል!? ወታደር? ታንክ? ቦንብ? አዋጅ? ማስፈራራት? መንጠራራት? ወይስ ቡዋ ማለት?

  truth
  January 26, 2018 at 2:41 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<