ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ስንት ወልድያ ያስፈልገናል? – ከዲያቆን ዳንኤል ክብረት

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

የጸጥታ ኃይሎች በወልድያ ነዋሪዎች ላይ የፈጸሙት ግድያ በምንም ዓይነቱ መመዘኛ ከውግዘት የሚያመልጥ አይደለም፡፡ በአንድ በኩል ‹ጸረ መንግሥት ዝማሬ ያሰሙ ነበር›፣ በሌላ በኩል ደግሞ ‹ድንጋይ ይወረውሩ ነበር› የሚሉት ምክንያቶች የጸጥታ ኃይሎች በሕዝብ ላይ ጥይት እንዲተኩሱ የሚያበቁ ሕጋዊና ሞራላዊ ምክንያቶች አይደሉም፡፡ ማንኛውም ጸጥታን የማስከበር ሥራ መከናወን ያለበት ሰላምን በሚያሰፍን፣ የሰዎችን ሕይወትና ንብረት በሚጠብቅና ተመጣጣኝ የሆነ ኃይልን ለመጠቀም በሚፈቅድ ሁኔታ መሆን አለበት፡፡

በኃይል የሚፈታ ችግር እንደሌለ መንግሥት ራሱ ከማናችንም በላይ የሚያውቀው ነገር ነው፡፡ የዛሬውን መንግሥት የመሠረተው ኢሕአዴግ ወደ በረሓ እንዲገባ ያደረገው ደርግ ችግሮችን ሁሉ በውይይት ሳይሆን በኃይልና በኃይል ብቻ ለመፍታት በመፈለጉ መሆኑን በየግንቦት ሃያ በዓሉ ስንሰማው ኖረናል፡፡ ለሰው የሚጠላውን ኃጢአት ራሱ ከመሥራት በላይ ውድቀት የለም፡፡ በዓሉ የአንድ ቀን በዓል ነው፡፡ ቢታገሡት ያልፍ ነበር፡፡ ሌላ ችግር ይከሰታል ተብሎ ከተጠረጠረና መረጃ ከተሰበሰበ እንኳን አያሌ የችግር መፍቻ አማራጮች ነበሩ፡፡ ‹የጸጥታ ችግርም› ‹የጸጥታ ኃይሎች›ም እኛ ሀገር ብቻ አይደለም ያሉት፡፡ ባለ ሥልጣኖቻችንም ለልምድ ልውውጥ በየሀገሩ ሲሄዱ ነው የሚኖሩት፡፡ ምነው ታድያ የተሻለ አማራጭ መማር አቃታቸው?

በዓሉ ሕጻናት፣ አረጋውያን፣ ዐቅመ ደካሞች፣ ነፍሰ ጡሮች፣ አካል ጉዳተኞች ሳይቀሩ የሚታደሙበት በዓል ነው፡፡ እንዴት ነው ወደነዚህ ሁሉ የሚተኮሰው? እንዴትስ ነው ‹ችግር ፈጠሩ› የተባሉትን አካላት ከሌሎች ለመለየት የሚቻለው? ጥይቱስ እንዴት ነው ከ9 ዓመት ሕጻን የሚጀምረው? እንዲህ ባሉ ዓመታዊ በዓላት ቀን የሚፈጠር ግፍ ከልጅ ልጅ ለመታወስና የበቀልን ስሜት ለመቀስቀስ ቀላል መሆኑን እንዴት ለማሰብ ከበደን? ከዚህ በኋላ ወልድያ ላይ የቃና ዘገሊላ በዓል ቃና ዘገሊላ ብቻ ሆኖ የሚታሰብ ይመስለናን? ገና ይዘፈንበታል፣ ይፎከርበታል፣ ይተረትበታል፣ ሙሾ ይወረድበታል፣ ውሎ ለቅሶ ይዋልበታል፡፡ ለመሆኑስ በየልቅሶ ቤቱ የተቀመጠው ሕዝብ ስለ ልማትና ዴሞክራሲ፣ ስለ መንገድና ትምህርት ቤት፣ ስለ ባቡርና አውሮፕላን ማረፊያ የሚጨዋወት ይመስለናል? ገና ተዝካር፣ መት ዓመት፣ ሰባት ዓመት፣ ሃያ አንድ ዓመት የሙታን በዓል አለ፡፡ በነዚህ ዘመናት ሁሉ ምን የሚባል ይመስላችኋል?

እንዲህ ላሉ ችግሮችስ ጥይት መፍትሔ አለመሆኑን ባለፉት ሁለት ዓመታት ሀገሪቱ ያለፈችበት ሁኔታ ብቻ እንዴት አያስተምረንም? ይልቅ ለምን የችግሩን ምንጭ ለማድረቅ አንሠራም? ‹የሚያስለቅስ ነገር ነግሮ አታልቅስ ይለኛል› የሚል የትግርኛ አባባል አለ፡፡ ሕዝቡ ለምን ባሰው? ወጣቶቹ ለምን ተቃወሙ? የዚህ ሁሉ ችግር ምንጩስ ምንድን ነው? ብሎ መሥራት አይሻልም፡፡ ለምን ሕዝብን ከሕዝብ ወገንን ከወገን የሚያጋጭና ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ቂም እንዲቋጠር ይፈለጋል? ለምንስ የዘርና የጎሳ መልክ እንዲይዝ ይፈለጋል? ወንጀለኞችስ ለምንድን ነው በጎሳ ካባ ውስጥ እንዲደበቁ ሁኔታዎች የሚመቻቹት? ከመሬት መንቀጥቀጡ(shock) በላይ ድኅረ መንቀጥቀጡ(aftershock) ውጤቱ የከፋ መሆኑን አናውቅምን? ችግሩንስ ከመሠረቱ ለመፍታት ስንት ወልድያ ያስፈልገናል?

አሁንም ባለ ሥልጣኖቻችን ቆም ብለው የማሰቢያ ጊዜያቸው ባያሳጥሩት መልካም ነው፡፡ ችግርን ከመፍታት ይልቅ ‹የከተማዋ ሁኔታ እየተረጋጋ ነው› ዓይነት ዜና ራስን ማታለያ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ስብሰባ ደምን አድርቆ አያውቅም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዝምታ በመቀበል፣ ፋታም በፍጻሜነት ሊተረጎም አይችልም፡፡ በበላይ ዘለቀ ምክንያት በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ወታደሮች ግፍ የተፈጸመበት የጎጃም ገበሬ ምነው ዝም አለ? ሲባል
ዝም አልክ ይለኛል ዝምታ የታለ
ውስጤ እየጮኸ ነው እየተቃጠለ
ብሎ የገጠመው የልቅሶ ግጥም ሁኔታውን በሚገባ የሚገልጠው ይመስለኛል፡፡ አሁንም ሰይፍ ወደ ሰገባው፣ ቃታም ወደ ቦታው፣ ይግባ፡፡ ወንጀለኞችም ወደ ፍርድ፣ ችግሮችም ወደ መሠረታዊ መፍትሔ ይምጡ፡፡ መንግስትም ወደ ልቡናው ይመለስ፡፡

16 Responses to ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ስንት ወልድያ ያስፈልገናል? – ከዲያቆን ዳንኤል ክብረት

 1. I am still crying! We have to unite that is the only solution. We have to work together; if not TPLF/EPRDF will go on as usual

  ካህሳይ መረሳ
  January 24, 2018 at 11:28 am
  Reply

 2. ዳንዔል እስካሁን የት ነበርክ??????ለወያኔ ጭፍጨፋው አዲስ አይደለም።ወሎዬ ስለሆንክ ድምፅህን አሰማህ!!!!!
  ወልዲያዎች ጀግኖች ናቸው።በውስጣቸው እየኖሩ የሚያስገድሏቸው ላይ እርምጃ ወስደዋል።ወያኔ ለዳንዔል ክብረት ምን ዓይነት አውሬ እንደሆነ ገና አልገባውም።
  ዳንዔል ወያኔ መቼም የሚያስበው በትግል ወቅት ተሰው በሚላቸው ታጋዮች ብዛት ስለሆነ አሁን በየአካባቢው የሚገደለው ህዝብ ምኑም እንዳልሆነ ገብቶህ ሳይገባህ መቅረቱ ቀባጣሪ ያሰኝሃል።ዝም ብለህ ለወያኔ አለቅልቅ።ቀላማጅ ነህ።አዛኝ ቅቤ አንጓች!!!!!

  ጋምብሬ
  January 24, 2018 at 11:46 am
  Reply

  • ጋምብሬ
   ምነው ሁሌ መነቃቀፍ መነቋቀር /?ለመሆኑ አንተ ኢትዮጵያ ውስጥ ነህ?እስከዛሬስ ምን አስተዋጽስ አድርገሃል?ማንኛውም
   ሰው ስለተሰማው ስሜት ቢገልጽ ነውሩ ምኑጋር ነው?
   የግል ጠብ ካለህ ወይም ችግር ካለብህ ግልጽ አድርገህ ንገረው
   በተረፈ መገንዘብ ያለብን ሁላችንም የኢትዮጵ ልጆች ነን።

   NARDI
   January 26, 2018 at 9:59 am
   Reply

   • ናርዲ የስነ ፅሁፍ ሰው መሆን ለግል መተዳደሪያ ነው።ዳንዔልም በዚህ ሙያ ላይ እንዳለ ይታወቃል።እኔ እስካሁን ዳንዔልን የማውቀው በፅሁፉ እና ላለው መንግስት አለቅላቂነቱን ነው።
    ናርዲ ካለፉት 2 ዓመታት ጀምሮ እስካሁን ያሁሉ ሰው ሲያልቅ ዳንዔል እንደ ባለሙያነቱ የት ነበር??????? አሁንም አይገፋበትም።አድርባይ ብዕር ያለው ሰው ነው።ዝም ብሎ ቢዝነሱን ያሳድድ።ይህን ምከሪ(ረ)ው።

    ጋምብሬ
    January 27, 2018 at 2:36 am
    Reply

 3. Thank you, this is what we all have to say and agree. Whoever writes and shows the wrong and abusive things done by these people we need to read and give positive comments. We should not criticize those who are against these evil people, we should not waste our time and energy criticizing each other. Support everyone who shows the wrong.

  chaltu
  January 24, 2018 at 2:17 pm
  Reply

 4. We don’t have government any more..Down down Weyane…Death to the killers!!!

  Shuluqa
  January 24, 2018 at 2:56 pm
  Reply

 5. የኔ እንኳን መልእክት ለአቶ ጋምቤሬ ትንሽ በነገር ዳንኤል ክብረትን በመዉጋቶት የተሰማኝን ልግለፅሎት።
  ለመሆኑ ኣቶ ጋምቤሬ ከስሞት ጀምሮ ብንነሳ ኢትዮጵያዊ እንዳልሆኑ ፀጉረ ልዉጥ እንደሆኑ ያስታዉቅቦታል።ዳንኤልን መሳይ ታላቅ መንፈሳዊ ኣባት ወንድማን ይሄ ቂጣ በቀደደው መደዴ ባለጌ ምላሶት ሲሽነቁጡ ትንሽ እፍረት ብጤም ያለመሰማትኦ ገርሞኛል።ለመሆኑ ሰዉ ኣያዉቀኝም ብለዉ እንዲህ መለፋደዶን የቅርብ ጓደኞቾ እንደምናውቀው ሲረዱ ምን ይሰማዎት ይሆን?ነገሩ እርሶ የግርረገብ የስነምግባር ኣይነት ለእርሶ ከመንገር ድንጋይ ላይ ዉሃን ማፍሰስ ይቀላል።እናም ወዳጄ ይሄ ብዙዎች የኢትዮጵያዊያን ሰዎች ቁም ነገር የምናወራባት መድረክ ስለሆነ ከነብልግናዎት ኣርፈዉ ቢቀመጡ መልካም ነዉ!!!

  እዮብ ኣስመላሽ
  January 24, 2018 at 10:45 pm
  Reply

  • እዮብ የኛ ሰው ለምን ተነካሁ እንደሚል ይታወቃል።ራሳችንን untouchable(የማይነካ)አድርገን ስለምናይ ነው።ደካማነት ማለት ይህ ነው።ስለስድብህ አመሰግናለሁ።ትንሽ ስለሆንክ ንቄሃለሁ።

   ጋምብሬ
   January 27, 2018 at 2:41 am
   Reply

   • ጋምብሬ ስምህ በራሱ አደጋ ነው። ዳንዔልን ጥሩ አይተኸዋል።እጥር ምጥን ባለ ሁኔታ ገልፀኸዋል።አቦ ይመችህ።እዮብ የተባለው በሱ ቤት የእርስዎን ትችት በስድብ መውቀሱ ነው።ጋምብሬ ግዴሎትም ጨቅላ ጭንቅላት ብዬሎታለሁ።ይመችዎት።

    ምናቡ
    January 27, 2018 at 2:47 pm
    Reply

 6. Saniel kkkkkkk

  eskezare yet neberk ???????

  ante rasih ye weyane cadre aydeleh ende ?

  Manin lematalel ,,teqawame honeh biq alk ??

  ewnetachewin new Qesis Asteserye Tige,, tesleklaki zendo yaluh !!

  BEMOQEBET SENAGONEBIS ALNEBER ß YEBETEMENGISTU dABO KORASH man honene

  ye Dashen bera mastaweqeya kejerbah be adarashu seqleh ,,yemitsebk !

  ASMESAY YE CHQA ESHOK !!

  Lema Anbesaw
  January 25, 2018 at 12:53 am
  Reply

 7. kelay temelketu ,, S besitet new

  Daniel kibret!! tebilo yenebeb pls

  ty

  Lema Anbesaw
  January 25, 2018 at 12:56 am
  Reply

 8. ኣባ ይፍቱኝ
  (በእውቀቱ ሥዩም)

  ኣባ ይፍቱኝ !
  ሲኦል አለ ሲሉኝ፤ የለም ብየ ክጀ
  የባልቴት ተረት ነው፤ በማለት ቀልጀ
  ኣውቄ በድፍረት፤ በድያለሁና
  ያንጹኝ በንስሃ፤ ያንሱኝ በቀኖና
  ሲኦል ከነጭፍራው፤ በጉም ተሸፍኖ
  እንዴት ሳላየው ኖርኩ፤ ካጠገቤ ሆኖ?
  ኣባ ይፍቱኝ
  ሰይጣን ብሎ ነገር፤ የተጭበረበረ
  ዋዛ ነው ቧልት ነው፤ ብየ ኣስብ ነበረ
  ይሄው እውነት ሆኖ፤ ዋዛና ተረቱ
  ባይኔ በብረቱ
  ዲያብሎስን ኣየሁት፤ በሸሚዝ ዘንጦ
  እልፍ ግዳይ ጥሎ፤ ቸብቸቦ ጨብጦ፡፡
  ኣባ
  ልክ እንደ ብርሌ ፤ኣጥንት ሲከሰከስ
  ኣባይን ኣዋሽን፤ የሚያስንቅ ደም ሲፈስ
  ለምለም ፍጥረት ሁላ፤ ወደ ኣመድ ሲመለስ
  ልክ እንደ ጧፍ ሃውልት፤ ምስኪኖች ሲጋዩ
  ምድጃው ዳር ሆነው፤ ይሄንን እያዩ
  ገሃነም ከላይ ነው፤ ብለው መሳትዎ
  እስዎ እንደፈቱኝ ፤ እግዚሃር ይፍታዎ።

  Belay
  January 25, 2018 at 5:44 am
  Reply

 9. Daniel is part of the problem, you are the messenger woyane. Why you have to bring teret? why don’t you denounce it your self outright?

  tena taye
  January 25, 2018 at 6:32 am
  Reply

 10. tena taye ty bro !

  Daniel kibret belo , debterea –

  26 amet ye weyane Gibre bela-

  ye Dashen birra delala

  ejihen atawenachfbin , Tultula !

  Lema Anbesaw
  January 26, 2018 at 12:10 pm
  Reply

 11. Eyob kkkkkkkk

  Daniel kibret rasu weyane yemedebelet cadre alew eko

  ante tihon !??

  WERADA WEYANE !

  Lema Anbesaw
  January 26, 2018 at 12:14 pm
  Reply

 12. አስመሳይ ወያኔዎችና ባንዳዎች እጃችሁን ከዳንኤል ላይ አንሱ !!! ገዳዮችና በከንቱ የንፁኃን ደም አፍሳሾች ሆይ
  ከሚመጣው ምድራዊው ኃይልና ከሰማያዊ ቅጣት የሚያድናችሁ ማን ይሆን ? የአባቶች ኡኡታ የእናቶች ጩሄትና
  ስቆቃ የልጆች እንባና ምሬት ወደ ስማይ አርጏልና ዋ ለእናንተ !!!

  Chala alemu
  January 26, 2018 at 2:40 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<