“መንግስት” ለህዝቡ የገባውን ቃል ባለመፈጸሙ የሚገጥመው ተቃውሞ እጅግ የከፋ ነው | (ይድነቃቸው ከበደ)

Filed under: News Feature,ነፃ አስተያየቶች |

የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የፖለቲካ እስረኞችን ለመፍታት እና ማዕከላዊን ለመዝጋት መወሰኑን ታህሳስ 25 ቀን 2010 ዓ.ም አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ የኢህአዴግ የአራቱ ድርጅቶች ሊቀመናብርት መግለጫ መስጠታቸው የሚታወስ ነው። መግለጫ ከተሰጠ አንድ ወር ሊሞላው የተወሰኑ ቀናት ይቀሩታል። ሆኖም ግን እስካሁን ድረስ “መንግስት” የገባው ቃል በአግባቡ መፈጸም አልቻለም ። ከዚህም በተጨማሪ የሀገሪቱን ፖለቲካዊ ችግሮች ለዘለቄታው ለመፍታት “መንግስት” ተጨማሪ የለውጥ እርምጃዎችን ለመውሰድ ቃል የገባ ቢሆንም ፤አሁንም በአገራችን ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ አለመረጋጋት እና ቀውስ አል ። የአገዛዙ ጠባቂዎች እንደ በፊቱ አሁንም ወደ ህዝብ እየተኮሱ ንጹሃንን እየገደሉ ይገኛሉ ። ለዚህም እንደ ማሳያ የወልድያ አሰቃቂ ግድያ መመልከት በቂ ነው። በአጠቃላይ “በመንግስት” በኩል አበረታች የሆነ ምን አይነት ለውጥ እስካሁን ለማየት አልተቻለም ።

በዛሬው እለት የተሰማው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ የአገዛዙ ስርዓት ምን ያህል ውዥንብር ውስጥ እንደገባ የሚያሳይ ነው ። በፌደራል ደረጃ ይፈታሉ ከተባሉት 115 እስረኞች መካከልም 4ቱ በዛሬው እለት ከ4 ዓመት እስከ 5 ዓመት ተፈረደባቸው ። አቶ ሉሉ መለሰ 4 ዓመት ከ5 ወር 4 ፣ አቶ በጋሻው ድንጋ 4 ዓመት ከ5 ወር ፣ አቶ ጌታሁን ቀጶ 5 ዓመት እንዲሁም አቶ መርደኪዮስ ሽብሩ 5 ዓመት ተፈርዶባቸዋል ።በችሎት ታዳሚ የነበረው ናትናኤል ያለምዘውድ እንደገለጸው ፤ በዛሬው እለት የተፈረደባቸው እስረኞች ቀደም ብሎ ከእስር እንደሚፈቱ ተገልጾላቸው፤ተሀድሶ ስልጠና ወስደው ቤተሰብ ጋር ስልክ ደውለው ቤተሰብ በጉጉት እየጠበቃቸው ነበር።ፍርድ ቤቱ የፍርድ ውሳኔ በሚሰጥበት ወቅት እስረኞቹ ከተፈችዎቹ መካከል እንደነበሩ እንዲሁም አጠቃላይ ሁኔታ ለፍርድ ቤቱ የገለጹ ቢሆንም ፤ ፍርድ ቤቱ “ጉዳያችሁን ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጋር ጨርሱ”የሚል መልስ ሰጥቷቸዋል።

ይህ በእንዲ እንዳለ የአገዛዙ ስርዓት ከዚህ ቀደም ሃገራዊ መግባባት ለመፍጠርና ፣የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት፤በእስር የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ ሌሎች ግለሰቦች ክሳቸው ተቋርጦ ወይም በምህረት ከእስር እንደሚፈቱ ለህዝብ ቃል በመግባት መግለጫ መስጠቱ የሚታወስ ነው። መግለጫውን ተከትሎ የክስ ሂደታቸው ተቆርጦ ከእስር ከተፈቱት እጅግ በጣም ውስን ፖለቲከኞች መካከል ዶ/ር መረራ ጉዲና ይገኙበታል። ሆኖም ግን “መንግስት” ለህዝብ በገባው ቃል መሰረት በፖለቲካ ተሳትፎቸው የሚታወቁ ፖለቲከኞች እንዲሁም የሰብዓዊ እና የዴሞክራሲ መብት ተሟጋቾ እና ጋዜጠኞች እስካሁን ድረስ፤ በክስ ሂደት ላይ የሚገኙ ከሳቸው ያልተቋረጠ ሲሆን፤ ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የሚገኙ በምህረት አልተፈቱሙ። ማዕከላዊ እስር ቤት ተዘግቶ ሙዚየም እንደሚሆን የተገለጸ ቢሆንም፤ አሁንም ዜጎች እየተሰቃዩበት ይገኛል። “መንግስት” ለህዝቡ የገባውን ቃል በአግባቡ ያልፈጸመ እንደሆነ የሚገጥመው ተቃውሞ እጅግ በጣም የከፋ እንደሆነ የሚጠበቅ ነው ።

2 Responses to “መንግስት” ለህዝቡ የገባውን ቃል ባለመፈጸሙ የሚገጥመው ተቃውሞ እጅግ የከፋ ነው | (ይድነቃቸው ከበደ)

 1. TPLF can’t be qualified to be a gouvernment. It is only a mafya terrorist organisation::

  nabil
  January 25, 2018 at 12:06 am
  Reply

 2. በጉራጌ ዞን በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል በወልቂጤ ከተማ ከ8000 እስከ 10,000 የሚሆኑ ሰዎች አለ ስለሚባለው የመልካም አስተዳደር መጓደል እና ባጠቃላይ በአገሪቱ ስለሚታየው የፖለቲካ ሁኔታ ቅሬታቸውን እና ስጋታቸውን ለማሰማት ዛሬ ለተቃዉሞ መዉጣታቸዉን የአይን እማኞች ገልጸዋል።

  በከተማይቱ ሆስፒታል ለመገንባት ካሁን ቀደም የተገባዉ ቃል ለምን ዘገየ በሚል ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ ሶስት ሰዓት ድረስ ሰዎች ለታቃዉሞ መዉጣታቸዉን የዞኑ የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች አላፍ አቶ ፋንታሁን ወለደማርያማም ለዶይቼ ቬሌ አረጋግጠዋል።

  የዛሬዉን ተቃዉሞ በቅርበት የተከታተሉት በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የፖለትካ ሳይንስና የዉጭ ግንኝነት መምህር አቶ ዳንኤል መኮንን ለሀኪም ቤቱ ግንባታ ከዉጭ ገንዘብ እንደተገኘና መሰረተ ድንጋይ ተቀምጦለት «ህዝቡ ግንባታዉን በጉጉት ሲጠብቅ» እንደነበረ ይናገራሉ። እንደ አቶ ዳንኤል አስተያየት፣ የከተማይቱ አስተዳደር የሆስፒታሉን ግንባታ በፍጹም አለማስጀመሩ ሰለማዊ ሰልፈኞቹን አስቆጥቷል።

  ለሆስፒታሉ ግንባታ የተገኘው ገንዘብ የት እንደደረሰ ሳይታወቅ መጥፋቱ ዋናው የተቃውሞው መነሻ ምክንያት ቢሆንም፣ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ መሰረታዊው ችግር አድርገው ያነሱት ግን አሳሳቢ ያሉትን በዞኑ ደረጃ እና በአገሪቱ አሁን የምታየዉን የፖለትካ አለመረጋጋት መሆኑን መምህር ዳንኤል አስረድተዋል።

  የዞኑ ኩሙኒኬሸን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ወለደማርያማም ግን የተቃዋሚ ሰልፈኞቹ ጥያቄ አሁን በአገሪቱ ካለዉ የፖለቲካ ጥያቄ ጋር በምንም እንደማይገናኝ ጠቅሰዋል።

  በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች በተነበቡ መረጃዎች መሰረት፣ በትናንትናውም ዕለት በምስራቁ ክፍል በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በዱግዳ ቦራ ወረዳ ወይም አሌም ጤና በመባል በሚጠራው አከባብ ወጣቶች ለተቃዉሞ ወጥተው እንደነበር እና የፀጥታ አካላት ወሰዱት ባሉት ርምጃ የሰዉ ህወት አልፏል። ከትናንት በስቲያ ሰኞ ደግሞ በደቡቡ ክፍል በኦሮሚያ ክልል በቦራና ዞን በሞያሌ ከተማም የፀጥታ አካል እንዲሁ ወሰዱት በተባለ ርምጃ ሰዎች መሞታቸዉን የማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎቹ አክለው ጠቅሰዋል።

  ሚኒሊክ አለማየው
  January 25, 2018 at 1:03 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<