ሰው አይጥፋ! ከሚሊዮን አንድም ቢሆን እውነተኛ ሰው አይጥፋ! እንደ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ያለ ሰው አይጥፋ!

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

ከጌታቸው ሽፈራው

ሰው አይጥፋ! ከሚሊዮን አንድም ቢሆን እውነተኛ ሰው አይጥፋ! እንደ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ያለ ሰው አይጥፋ!
ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ የደቡብ ወሎ ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ረዳት ናቸው። ስለ ጭፍጨፋው የሚከተለውን እውነት ተናግረዋል! ይህኔ አቡነ ማቲያስ ከገዥዎቹ ጋር እየመከሩ ይሆናል!
~የጸጥታ ኃይሎች ለምን እንደመጡ አናውቅም፤ እንዳይመጡ ነግረናቸዋል! ሆን ብለው ለመምታት የመጡ ይመስላል።
~እነርሱ አይምጡ፤ እኛው በእኛው ፕሮግራማችንን እንመራለን ብለን ነበር
~ወጣቱን አሳበዱት፤ ከዚያም ወጣቱ የተሳደበም ይመስለኛል፤ ድንጋይም ሳይወረውር አይቀርም፤ ወዲያው በጥይት ለቀሙት!
~የእነርሱ መዘዝ ነው፤ እኛ ወጣቱ አበላሸ የምንለው ምንም ነገር የለም፣ ብዙ ሰው ነው የተጎዳብን፤ ያላወቅነውም ይኖራል
~የጸጥታ ኃይሎቹ ለብተና በተጠቀሙበት አስለቃሽ ጢስ ታቦቱን ያከበሩት ካህናት ተጎድተዋል ። በጎናቸው ባሉ ካህናት ተገድፈው ነው እንጂ ወድቀዋል።
~ወጣቱን ሌላ የፖሊቲካ አካል ቀሰቀሰው ይባል፤ እነርሱን ወታደሮቹን ማን ነው የቀሰቀሳቸው? ሰላም እንዳይኾን!

______

ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ! ስለ ወልዲያ ግድያ የሰጡት ምስክርነት !!

“የጸጥታ ኃይሎች ለምን እንደመጡ አናውቅም፤ እንዳይመጡ ነግረናቸዋል ።ኾን ብለው ለመምታት የመጡ ይመስላል።”


በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ፣ በጥምቀት እና በቃና ዘገሊላ በዓል አከባበር ወቅት የተቀሰቀሰው ግጭትና የተፈጸመው ግድያ፣ በጸጥታ ኃይሉ ስሕተት የደረሰ ነው ሲሉ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ረዳት፣ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ አወገዙ። የቃና ዘገሊላ በዓል፣ እንደ በዓለ ጥምቀት ኹሉ በሥርዐቱ እየተከበረ በሰላም ሊጠናቀቅ በተቃረበበት ሰዓትለበዓሉ አከባበር፣ ሀገረ ስብከቱ ከዞኑ ኃላፊዎች ጋራ እየተናበበ በመሥራቱ፣ የተጠየቀ ተጨማሪ ኃይል እንዳልነበርና “እነርሱ አይምጡ፤ እኛው በእኛው ፕሮግራማችንን እንመራለን፤” በማለት ቀድሞ እንዳሳወቀ ብፁዕነታቸው ጠቁመዋል፡፡ ይኹንና ወታደሮቹ በመምጣታቸው ወጣቱን ለተቃውሞ
እንዳነሣሡ የገለጹት አቡነ ኤርሚያስ “ወጣቱን አሳበዱት፤ ከዚያም ወጣቱ የተሳደበም ይመስለኛል፤ ድንጋይም ሳይወረውር አይቀርም፤ ወዲያው በጥይት ለቀሙት፤” በማለት የእርምጃውን ኢ-ፍትሐዊነት መግለጻቸውን ሐራ ተዋህዶ አስነብቧል።

በማግሥቱም ቀጥሎ ስለነበረው ግጭትና የንብረት ውድመት መንሥኤ አቡነ ኤርሚያስ ሲናገሩም፦ “የእነርሱ መዘዝ ነው፤ እኛ ወጣቱ አበላሸ የምንለው ምንም ነገር የለም፤” ብለዋል። “ብዙ ሰው ነው የተጎዳብን፤ ያላወቅነውም ይኖራል፤” ያሉት ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ፡፡ ግጭቱ በተከሠተበት ወቅት ከመርሳ ከተማ ወደ ወልዲያ ተመልሰው በዚያው አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ለማስተማር በዝግጅት ላይ እንደነበሩ በማውሳት ፣ “የጸጥታ ኃይሎቹ ለብተና በተጠቀሙበት አስለቃሽ ጢስ ታቦቱን ያከበሩት ካህናት ተጎድተዋል ። በጎናቸው ባሉ ካህናት ተገድፈው ነው እንጂ ወድቀዋል፤” ብለዋል ጥልቅ ቅሬታ በሚደመጥበት አነጋገር፡፡ “የጸጥታ ኃይሎች ለምን እንደመጡ አናውቅም፤ ኾን ብለው ለመምታት ይመስላል፤ ከራሳቸው መካከልም የሚያጠፋ ያለ ይመስለኛል ፤” ብለዋል፡፡ አያይዘውም ፣ “ወጣቱን ሌላ የፖሊቲካ አካል ቀሰቀሰው ይባል፤ እነርሱን ወታደሮቹን ማን ነው የቀሰቀሳቸው? ሰላም እንዳይኾን!” ሲሉም ጠይቀዋል -አቡነ ኤርሚያስ !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<