ጥሩነሽ ዲባባ በለንደን ማራቶን እንደምትሳተፍ አስታወቀች

Filed under: News Feature,ስፖርት |

(ዘ-ሐበሻ) ጀግናዋ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በለንደኑ ማራቶን እንደምትሳተፍ ዛሬ በትዊተር ገጿ ላይ አስታወቀች::

“በመጪው ኤፕሪል ወር በሚደረገው የለንደን ማራቶን ላይ እንደምሳተፍ ስገልጽ በደስታ ነው” ስትል ጥሩነሽ በአጭሩ ተሳትፎዋን ገልጻለች::

The 2018 Virgin Money #LondonMarathon የሚሰኘው ይኸው ውድድር እሁድ ኤፕሪል 22, 2018 እንደሚደረግ ከወጣለት መርሀ ግብር ለመረዳት ተችሏል::

ጥሩነሽ ዲባባ ቀነኔ የተወለደችው፤ ከአባትዋ ከአቶ ዲባባ ቀነኔ እና ከእናትዋ ከወይዘሮ ጉቱ ቶላ በመስከረም 21 ቀን 1978 ዓ.ም. በኢትዮጵያ በአርሲ ክፍለ ሀገር በጨፋ ወረዳ ነው። ጥሩነሽ ለቤተሰብዋ ከአምስት ልጆች ሶስተኛዋ ናት።

ጥሩነሽ ዲባባ የመጀመሪያ አለም አቀፍ የውጪ ውድድር ያደረገችው በ 2001 በአለም አቀፍ አትሌቶች ውድድር ላይ ነው። ውድድሩን ስታካሂድ የ 15 አመት ልጅ ነበረች፤፤ በዚህ ውድድር አምስተኛ በመሆን ጨርሳለች። በ 2003 በተደረገው የአፍሮ ኤሽያ ውድድር ላይ በ 5000 ሜትር የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች። የጥሩነሽ ዲባባ አስደናቂ ውጤቶች ማምጣት የጀመረችው በአለም አቀፍ አትሌቶች ውድድር ላይ በ 2003 2005 እና 2007 ላይ ነው።

ጥሩነሽ በ 2003 በ 5000 ሜትር ተስፈንጥራ በመውጣት የስፔይኗን ማርታ ዶሚኒጌዝ እና የኬንያዋን ኤዲት ማሳያ ቀድማ በመግባት ነው። በወቅቱ የታወቀች አትሌት ባለመሆኗ ውድድሩን ያስተላልፉ የነበሩት እንግሊዛዊ ስቲቭ ክራም እና ብሬንዳን ፎስተር ውድድሩ 100 ሜትር እስኪቀረው አንድም ጊዜ ስሟን ሳይጠሩ ቀርተዋል። በ 2005 ውድድር ላይ ተስፈንጥራ በመውጣት ብርሀኔ አደሬን እና እህታዋን እጅጋየሁን ቀድማ በመግባት የመጀመሪያዋ 5000 / 10000 ሜትር የወርቅ ተሸላሚ ለመሆን በቅታለች።

በ2007 ኦሳካ ላይ በተካሄደው የ 10000 ሜትር ውድድር የቱርክዋን ኤልቫን አቢይ ለገስን ተስፈንጥራ በመቅደም በ 31:55.41 አሽናፊ ሆናለች። በ 2004 በ አቴንስ ኦሎምፒክ በ 5000ሜትር ጥሩነሽ ሶስተኛ ወጥታለች በመሰረት ደፋር እና በ ኢሳቤላ ኦቺቺ በመሸነፍ። በሁኔታው ብዙ ሰዎች ቢበሳጩም የ 19 አመትዋ ጥሩነሽ የመጀመሪያዋ ወጣት ባለ ኦሎምፒክ ሜዳል ኢትዮጵያዊ አትሌት አሸናፊ አድርጓታል። በ2006 በወርቃማው ማህበር ውድድር ከስድስት የወርቅ ሜዳሊያ አምስቱን አሸናፊ ሆናለች ። (5,000 ሜ) በዚህም $83,333 ተሸላሚ ለመሆን በቅታለች።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<