በአዲስ አበባ ሊካሄድ የነበረው የሽረ እንዳስላሴ እና ባህርዳር ከተማ ጨዋታ ተጫዋቾቹም፣ ተመልካቹም፣ ዳኛውም ሜዳው ውስጥ ከገቡ በኋላ እንዲቆም ተደረገ 

Filed under: News Feature,ስፖርት,የዕለቱ ዜናዎች |

(ሶከር ኢትዮጵያ) በኢትዮዽያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ ሀ 11ኛ ሳምንት ሽረ ላይ መካሄድ የነበረበት የሽረ እንዳስላሴ እና ባህርዳር ከተማ ጨዋታ በፌዴሬሽኑ ሊግ ኮሚቴ ውሳኔ መሰረት ባለፈው እሁድ ጥር 20 ለገጣፎ ላይ በ08:00 ላይ ሊደረግ መርሀ ግብር ቢወጣለትም የፀጥታ አካላት በበቂ ሁኔታ ባለመኖሩ በሚል ምክንያት ለዛሬ ማክሰኞ ተላልፎ እንደነበር ይታወሳል።

ይኸው ውድድር ታዲያ ዛሬ ማክሰኞ ጥር 22/2010 አዲስ አበባ በኦሜድላ ሜዳ እንዲደረግ በወሰነው መሰረት የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች ፣ አመራሮች ፣ ደጋፊዎች ፣ የህክምና ቡድን እና የጨዋታውን አመራሮች እንዲሁም በቂ የፀጥታ ኃይል በሜዳው ተገኝቶ ነበር። ጨዋታው እንደሚካሄድ በማሰብም የሁለቱም ቡድኖች ተጫዋቾች ወደ ሜዳ ገብተው ልምምዳቸውን ጨርሰው ዳኞችም ለመጫወት ብቁ መሆናቸውን አረጋግጠው፣ “ጀምሩ” ለማለት ጥቂት ሲቀራቸው፣ የፀጥታ አካላት ከበላይ አካል በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት ጨዋታው እንዳይደረግ የሚል ውሳኔ መጣ ተብሎ ጨዋታው ሳይጀመር እንዲቋረጥ ተደርጓል።

የባህርዳር ከተማ ክለብ አመራሮች በውሳኔው እጅግ አዝነው ሜዳውን ለቀው የወጡ ሲሆን ቅሬታቸውንም ለጨዋታው ኮሚሽነር አቅርበዋል። ረጅም ርቀት አቋርጠው ክለባቸውን ለመደገፍ የመጡ ጥቂት የማይባሉ የባህርዳር ከተማ ደጋፊዎች ከአንዴም ሁለቴ ጨዋታው በመቋረጡ ከፍተኛ እንግልት እንደደረሰባቸው ተናግረው ፌዴሬሽኑ ውድደሮችን የመምራት አቅሙ ላይ ችግሮች እንዳለበት ገልፀዋል።

በሽረ እንዳስላሴ በኩል ደግሞ አስቀድመው ጨዋታው ከጥር 22 በኋላ በአአ ስታዲየም መካሄድ እንዳለበት በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ፌዴሬሽኑ በእንቢተኝነት ውሳኔ በመወሰኑ ጨዋታው ለመቋረጥ በቅቷል ብለዋል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከብሄር ጋር በተያያዘ የሚፈጠረው ውጥረትና ጸብ የ እግር ኳስ ውድድሮችን የቡጢ ሜዳ እያደረጋቸው ከመምጣቱም በላይ፣ የኢትዮጵያው ፕሪሚየር ሊግ ግራ የገባው ሊግ ሆኗል።

3 Responses to በአዲስ አበባ ሊካሄድ የነበረው የሽረ እንዳስላሴ እና ባህርዳር ከተማ ጨዋታ ተጫዋቾቹም፣ ተመልካቹም፣ ዳኛውም ሜዳው ውስጥ ከገቡ በኋላ እንዲቆም ተደረገ 

 1. ይህን ስፓርት ቢዘጉት ምን አለበት እኔ ሳውቅ ስፓርት ለጤንነት ለወዳጅነት ነው አሁን ሀገራችን ምንስማው ምናየው የትግሬን የበላይነት ማሳያ ነው የሆነው በዝህ ጠብ ይጀመራል ከዝያ ለምን ተነክተው ትግሬዎች ተብሎ ጥይቱ እደ ቆሎ ወገኔ ላይ ይርከፈከፋል ምነው ቢያቆም ሌላው ብሄር ይህን ጨዋታ በቃ ያቁም በጥይት ከሚነድ!!!

  ራሄል
  January 30, 2018 at 1:00 pm
  Reply

 2. Thats the fruits of Vision of Meless. When bushmen take control of power they mess every aspect of life.

  Babilie
  January 31, 2018 at 6:10 am
  Reply

 3. ageru esekiregaga chewatawe bikoyes min albet ,wetatu eskiregaga ebakachuen

  makita
  January 31, 2018 at 8:55 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<