ገንዘቤ ዲባባ 1500 ሜትር ፈጣኑን ሰአት አስመዝግባ ድሏን ድርብ ስታደርግ ፤ ሀጎስ ገ/ ህይወት በቀደሚነት አሸንፏል

Filed under: ስፖርት,የዕለቱ ዜናዎች |


በምዕራባዊቷ የጀርመን ካርልሱር ከተማ ላይ ምሽቱን በተካሄደው የIAAF World Indoor Tour 2018 ውድድር በ1500ሜትር ርቀት አትሌት ገንዘቤ ዲባባ ከታናሽ እህቷ አና ዲባባ ጋር በውድድሩን ተካፍለው ገንዘቤ ውድድሩን በ1ኛነት ከማሸነፏም በተጨማሪ በ1500 ሜትር እስከዛሬ ከተመዘገበው ውጤት እጅግ ፈጣኑን ሰአት 3:57:45 በመግባት አዲስ ታሪክ አስመዝግባለች።

በዚህ ውድድር ላይ የተካፈለችው የገንዘቤ ታናሽ እህት አና ዲባባ በ10ኛነት መጨረሻ ሆና ውድድሩን ብታጠናቅቅም በውድድሩ ከታላቅ እህቷ ጋር በመሳተፍ ለወደፊቱ የሚጠቅማታን ታላቅ ልምድ አካብታለች።

በ3000 ሜትር የወንዶች የቤት ውስጥ ውድድር ሀጎስ ገ/ ህይወት 7:37:91 በአሸናፊነት ሲያጠናቅቅ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ዮሚፍ ቀጀላ በ7:38:67 በሁለተኛነት አጠናቋል።

ምንጭ: ኢትዮኪክ ኦፍ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<