ገዱ አንዳርጋቸውና ደመቀ መኮንን ከሃላፊነት ተነስተዋል በሚል ለሚያስወሩት የሕወሓት ብሎገሮች ፤ አቶ ንጉሱ ጥላሁን “ዶሮ ብታልም ጥሬዋን” የሚል ምላሽ ሰጡ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

የሕወሓት ብሎገሮች አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአማራ ክልል ፕሬዚዳንትነት እንደተነሱ ፤ አቶ ደመቀ መኮንንም ከብአዴን ሊቀመንበርነት እንደተነሱ በሰበር ዜና መረጃውን እያሰራጩ መሆኑን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም:: የአማራ ክልል የኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ይህ ዜና እየተጻፈበት ባለበት ከ40 ደቂቃ በፊት በፌስቡክ ገጻቸው ለነዚህ ብሎገሮች “ዶሮ ብታልም ጥሬዋን” ሲሉ ምላሽ ሰጡ::

የአቶ ንጉሡ ምላሽ እንደሚከተለው ቀርቧል:-

የካቲት 10 ቀን 2010 ዓ.ም.
==================
“ዶሮ ብታልም ጥሬዋን”
===================
ብአዴን ስብሰባ ባካሄደ ቁጥር ለድርጅቱ እና
ለአማራ ህዝብ መሪ መሾም መሻር የሚመኙ ህልመኞች እነሆ የሰሞኑን ስብሰባ አስመልክቶ ምንም ፍንጭ ሲያጡ እንደተለመደው የህልም ዜና ሰብረውልናል።
ብአዴን የጀመረውን ውይይት እጅግ በሰከነ እና መደማመጥ በሰፈነበት ሁኔታ እያካሄደ ሲሆን ውይይቱን እንዳጠናቀቅንም ለህዝባችን መግለጫ የምንሰጥ ሲሆን “ውስጥ አዋቂ ነን” በማለት ምኞታቸውን በዜና መልክ ፤ ያውም በሰበር ዜና ለሚያሰሙን ህልመኞች መሪውን የሚመርጠው ድርጅቱ እና የአማራ ህዝብ ስለሆነ “መመኘት ይቻላል ፤ እዉነት ግን ወዲህ አለች ” እንላለን።
ህዝባችንም ይህንን አይነት ዘመቻ የተለመደ ስለሆነ የድርጅቱን ውሳኔዎች ውይይታችን በሚቀጥሉት ቅርብ ቀናት እስኪጠናቀቅ እና ትክክለኛው መረጃ በድርጅቱ በኩል እስኪሰጥ ድረስ ለሚለቀቁ እንዲህ ዓይነት የህልም ዜናዎች ጆሮ እንዳይሰጥ እንጠቁማለን።
“ዶሮ ብታልም ጥሬዋን”

2 Responses to ገዱ አንዳርጋቸውና ደመቀ መኮንን ከሃላፊነት ተነስተዋል በሚል ለሚያስወሩት የሕወሓት ብሎገሮች ፤ አቶ ንጉሱ ጥላሁን “ዶሮ ብታልም ጥሬዋን” የሚል ምላሽ ሰጡ

 1. The soa called ANDM is the handwork and servant of the TPLF. All the top leaders of the ANDM are Tigres (Bereket Simon) and non-Amharas (Addisu Legesse). The TPLF bloggers are indicating decisions taken or to be taken by TPLF regarding the ANDM.

  Negash
  February 17, 2018 at 4:25 am
  Reply

 2. ብአዴን ከህውሀትም ከሚመራው ህዝብም ውጭ እንዳይሆን አጥብቀህ ጎርሰህ ወደ ወገንህ ነውና የራሱን ህዝብ የልብ ትርታ ያዳምጥ አማራው ከትልቅ እስከ ትንሽ ከብአዴን ጎን ይቁም የለማ መገርሳ ጎልበት የተፈጠረለት ህዝቡ ከመሪው ጎን መሰለፉ ነው ተወደደም ተጠላም የአማራ ባለስልጣናትን ህዝቡ ማራቅና አሳልፎአ መስጠት የለበትም 4ነጥብ

  mesfinwassie099@gmail.com
  February 17, 2018 at 11:50 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<