ኃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣን ከመልቀቁ በፊት የሶስት ቀን ጸሎት እንዲደረግለት ጠይቋል ተባለ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

ኤች.አር. 128 ህገ-ረቂቅ በአሜሪካ ተወካዮች ምክርቤት ሊጸድቅ ይችላል መባሉ በህወሃት ቁንጮዎች ዘንድ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል

በልኡል አለሜ

 • ኃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣን ከመልቀቁ በፊት የሶስት ቀን ጸሎት እንዲደረግለት ጠይቋል ተባለ

ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሚገለገልበት የፕሮቴስታንት ሐዋሪያት ቤ/ክርስቲያን ደዉሎ ለፓስተሩ “ስልጣን እንለድቅ ከባድ ጫና ተፈጥሮብኛል በመላዉ አለም የሚገኙ የቤ/ክርስቲያን አባላቶች በሚስጥር ጸሎት ያድርጉልኝ” በማለት መጠየቁን ማረጋገጥ ተችሏል።

ኃይለማርያም ደሳለኝ በገዛ ፍቃዱ ስልጣን እንዳለቀቀ የሚያመላክተዉ ይህ እዉነተኛ መረጃ ህወሃት የገባበትን ጥልቅ ገደል እርቀት በቀጥታ እንደሚያሳይ የገለጹት የቤተ ክርስቲያን ምንጮች… ስርዓቱ በኤች.አር. 128 የአሜሪካ አስገዳጅ ህግ መሰረት ጭንቅ ዉስጥ መግባቱን በግልጽ አስቀምጠዋል።

ምንጩ እንደሚሉት ወደ 17 ያህል አደገኛ መጠይቆችንና ነጥቦችን ያካተተዉ የኤች.አር. 128 አስገዳጅ ህግ እስከ ጥር 28/2018 ድረስ ተግባራዊ ካልሆነ የህወሃት ባለስልጣናት እና ድርጅቶች በመላዉ አለም ላይ ያላቸዉ እሴት፣ ተንቀሳቃሽ ንብረቶችና የንግድ እንዲሁም የግል ባንክ አካዉንቶች በሙሉ እደሚታገዱ የሚያስጠነቅቅ ከመሆኑም ባሻገር ማንኛዉም የህወሃት ባለስልጣን የጉዞ እግድ ሰለባና የመከሰስ ግዴታ ይጣልበታል።

የኤች.አር. 128 አስገዳጅ ህግ ህወሃት በአጠቃላይ በእጁ የሚገኙትን የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፣ የህሊና እስረኞች፣ ጋዜጠኞች እንዲሁም በሐይማኖትና በዘር (በማንነታቸው) ምክንያት የታሰሩ ወገኖች በሙሉ እንዲለቀቁ የሚያዝ ሲሆን በተለይም የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ድርጅት አጣሪ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ዘልቆ ገብቶ መንግስት በህዝብ ላይ የወሰደዉን ኢሰብአዊ ጭፍጨፋዎች በሙሉ እንዲያጣራ የህወሃት አንጃ ቡድን እንዲፈቅድ ያስጠነቅቃል።

በዚህ ከፍተኛ አጣብቂኝ ዉስጥ የሚገኙት የህወሃት ባለስልጣናት ከተጠያቂነት ለማምለጥ የሚያደርጉት ግብግብ በከፍተኛ ሁኔታ ከመጨመሩም ባሻገር መለሳለስና መቀዝቀዝ የሚገባዉ የሰላም መንገድ ጭራሹኑ በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መታጀቡ የስርአቱን አጣብቂኝ ዉስጥ መግባት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

አደገኛ ዉጥረት ላይ የሚገኘዉ የህወሃት ወያኔ ቡድን በዛሬዉ እለት ከፍተኛ ድብደባና በደል የደረሰባቸዉን የህሊና እስረኞች አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌን ጨምሮ ለመፍታት እየመከረ ቢሆንም ፊት ለፊት የተጋረጠባቸዉን አደጋ ለመከላከል በማይችሉበትና ተስፋ የመቁረጥ መንፈስ በሁሉም ባለስልጣኖች ላይ ጎልቶ እየታየ መሆኑን ለመረዳት ግዜው መስታወት ነዉ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

2 Responses to ኃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣን ከመልቀቁ በፊት የሶስት ቀን ጸሎት እንዲደረግለት ጠይቋል ተባለ

 1. there will be no way to escape from justice.we’ll find them all those people who washed their hand with blood’s of innocent children ,peace and freedom seekers.

  One Ethiopia
  February 18, 2018 at 5:36 am
  Reply

 2. This man is criminal. He must not be allowed to escape scot-free. He should be charged by the International Criminal Court. There are tons of evidences to indict him. this coward has mindlessly supervised the cold blooded killing of innocent civilians at much greater magnitude than has ever been seen under this fascistic regime. We have seen the displacement and ethnic cleansing particularly of close to 1 million Oromos in what was state-sponsored campaign. Hailemariam was at the epi-center of this cynical misdeeds. He is the willing actor and executioner. He is now forced out of office because things were crumbling before his eyes. A man who sanctified himself with “Tigre is God” religion is suddenly caught in a tremor of unending public protest. He of course did his animal-best to maintain the Tigre apartheid statusquo. But he failed and failed miserably. Now he is jumping the ship. What a born coward.

  Murad
  February 18, 2018 at 2:18 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<