” ቆራጣው ዮሀንስን ” ፍለጋ [ ቬሮኒካ መላኩ]

Filed under: News Feature,ነፃ አስተያየቶች |

እኔ ከፌስ ቡክ ከተወገድኩ በኋላ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ብዙ ነገሮች ተከስተው አለፉ።
ምስኪኑ ጠቅላይ ሚ/ር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ከስልጣኑ ተወገደ ወይም ራሱን አስወገደ ።

ታላቁ የግሪክ ፈላስፋ አርሲጣጢለስ፤ “የሰው ልጅ ፖለቲካዊ እንስሳ ነው” ብሎ ያኖረው ዘመን ተሻጋሪን ምልከታ እውን ይሆን ዘንድ “ፖለቲካ አልወድም ” ሲል የከረመው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ቀጣዩን ጠቅላይ ሚኒስቴር በመተንበይና በጉዳዩ ላይ በመተንተን ተጠምዶ ከረመ ።

ፎቶው የተገኘው በኢትዮጵያ ከሚታተመው የአዲስ ፎርቹን ጋዜጣ የፊት ገጽ ላይ ነው::እርግጥ ስለመሪዎች ከዚህም የበለጠ መወራት አለበት የሚል እምነት አለኝ ። ግለሰብ መሪዎች የአንድን አገር እጣፋንታና የሚሊዮኖችን እድል የመወሰን እድላቸው ከፍተኛ ነው። አፄ ሀይለስላሴ ለአምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ እንደነገሩት ” ህዝብ መምራት የበግ መንጋ አሰማርቶ እንደ መጠበቅ ቀላል አይደለም ።” በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያውያን ” ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ማን ይሆን ?” እያሉ ቢብሰለሰሉ ትክክል ናቸው።

የሮማን ኢምፓየርን ዋና ከተማ ሮምን እሳት ለኩሶ ከተማይቱን ስትጋይና አመድ ስትለብስ እየሳቀ ሲዝናና የነበረው ፣ በሮማ ኮሎስየም ህዝቦችን ለቀናት ለተራቡ አንበሳና ነብር ወርውሮ ከትዳር ጓደኛዋ ጋር ወይኑን እየተዝናና ይጎነጭ የነበረው ፣። ” ምነው ይሄ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ህዝብ አንድ አንገት በኖረውና በሰይፍ በቀላሁት ። ” እያለ የተመኘውና ሮምን የሽብርና የቅዤት ከተማ ያደረጋት ኔሮ አንድ ግለሰብ ነበር።


ጀርመንን አዋህዶ ታላቅ ያደረጋት ኦቶ ቫን ቢስማርክም ሆነ ጀርመንን ወደ የሰው ልጅ መታረጃ ቄራና ምድጃ የቀየራት ሂትለር ሁለቱም ግለሰቦች ናቸው።
ኢትዮጵያን የአፍሪካ የነፃነት ጉልላትና የአለም ጥቁር ህዝቦች ምልክት ያደረጋት እምዬ ምኒልክም ሆነ ኢትዮጵያን ገነጣጥሎ የዜጎች መቀቀያ ድስት ያደረገው መለስ ዜናዊ አንድ ግለሰብ ናቸው። ግለሰብ መሪዎች በአንድ አገርና ህዝብ እድል ላይ በአዎንታዊውም ሆነ በአሉታዊ መልኩ ተፅእኗቸው ከፍተኛ ስለሆነ በጉዳዩ ላይ መወያየቱ ትክክል ነው።

አሁን ወደ ተጨባጩ የአገራችን ሁኔታ ስንመለስ ህውሃት ሀይለማሪያምን የሚተካ “ቆራጣው ዮሀንስን” ፍለጋ በር ዘግቶ እያሴረ ይመስላል። እዚህ ላይ ስለ 70 አመት አዛውንቱና እጄ ቆራጣው ዮሀንስ ለማውራት ጊዜ ባይኖረኝም ቆራጣው ዮሀንስ ማለት በ17ኛው ክዘ የሰሜን ጎርፍ አምጥቶ ጎንደር ላይ የጣለው ሚካኤል ስሁል የሚባል ወንበዴ ከወህኒ አምባ ደካሞችን እየመረጠ ዙፋን ላይ ወዝፎ እንደ አሻንጉሊት ከተጫወተባቸው ንጉሶች መካከል የመጨረሻው ንጉስ ነበር።

በእኔ አመለካከት የመጨረሻው ” ቆራጣው ዮሀንስ” ሀይለማሪያም ደሳለኝ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር ነገር ግን ደመቀ መኮንን ሽፈራው ሽጉጤና አቢይ አህመድ የሚባሉ ተራ ይዘው ተኮልኩለው እየጠበቁ ነው።


ሽፈራው ወይም ደመቀ መኮንን የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ስልጣን የሚይዙ ከሆነ የአቦይ ስብሃት የሽንት ጨርቅ ቀያሪ ከመሆን የዘለለ ሚና አይኖራቸውም ። በአቢይ አህመድም ቢሆን መተማመን ያስቸግራል።

እርግጥ የኦሮሞ አክቲቪስቶች አቢይ አህመድ የሚባል “ነቢይ ” እየመጣ እንደሆነ በመስበክ
ዳረጎቱን ህዝቡ አሜን ብሎ እንዲቀበል እውነታውን በማጥበረበር ወይም “ፎልስ ኮንሸስነስ” መፍጠር የፕሮፓጋንዳቸው ተቀዳሚ ሥራ ሆኗል።

ከነዚህ ሶስት ሰዎች የተሻለውን ለመምረጥ
በቅድሚያ በአገራችንን የናኘውን ውስብስብ ነባራዊ የፖለቲካ ሁኔታ መመርመር ያስፈልጋል። አሁንም ህውሃት የተባለው ቡድን የሚናከስበት አብዛኛው ጥርሱ ወላልቆ በድዱ ቢቀርም አሁንም መከላከያና ደህንነት የሚባሉ ሁለት ጥርሶች ቀርተውታል ። ቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር በህግ በተሰጠው ስልጣን ተጠቅሞ እነዚህን ሁለት ጥርሶች መንግሎ የሚጥል ከሆነ ታሪክ ይሰራል።

አሜሪካኖች እንደሚሉት ” ትላልቅ ችግሮች ታላላቅ መሪዎችን ይወልዳሉ ።”

ሁለተኛው

የአለም ጦርነት ዌንስተን ችርችልንና ሩዝቬልትን ወልዷል። በእኛም አገር ዘመነ መሳፍንት የሚባለው የችግርና የፈተና ወቅት አፄ ቴዎድሮስን የሚያክል ታላቅ መሪ ወልዶልናል ።
ዛሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ችግር ውስጥ ነች ። ነገር ግን ዛሬም ኢትዮጵያ የወላድ መካን አይደለችም ። ከወያኔ ውስጥ መሪ የሚሆን ቢጠፋም ከተቃዋሚው ጎራ ውስጥ ታላላቅ መሪዎች ተፈጥረዋል። ኮለኔል ደመቀ ዘውዴ ፣ እስክንድር ነጋ ፣መረራ ጉዲና ፣ በቀለ ገርባ አንዱአለም አራጌ እና ሌሎችን ታላላቅ ሰዎች ወልዳለች።

አሁን በተጨባጭ እንደምንመለከተው ወያኔ እንደ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የሚዘውረው ባለተራ ” ቆራጣው ዮሀንስ ” ከመፈለግ ለአንድትም ሰከንድ አያርፍም።።
ስሁል ሚካኤል በ17ኛው ክዘ እሱ ራሱ ንጉስ ሆኖ መግዛት ስለማይችልና የነጋሲነት ዘር ስላልነበረው ደካሞችን አየፈለገ በእጅ አዙር ለመግዛት ሞክሮ ነበር ።
ዛሬም ህውሃት የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ እንደማታገኝ ስታውቅ በእጅ አዙር “ጡል ጡል ” እያለ የሚላላካትን አሻንጉሊት ጠቅላይ ሚኒስትር ፍለጋ ላይ ነች ። ሽፈራውሽፈራው ሽጉጤ በመላላክ ከሀይለማሪያም ቢበልጥ እንጅ የሚያንስ አይደለም። ደመቀ መኮንንም “የጎባጣ አሽከር ” የሚባለው አይነት ነው ። ብዙ ተስፋ የተጣለበት አቢይ አህመድ ነው ። አቢይንም ቢሆን ከጣሪያ በላይ የሚሰማው ያልተገራና ያልበሰለ የቄሮ ጫጫታ አደንቁሮት ሊሆን ስለሚችል አስተማማኝ አይደለም ። በዚህ ሁሉ ፍትጊያ ቀጣዩ ” ቆራጣው ዮሀንስ ” ማነው ካላችሁኝ ደመቀ መኮንን ይመስለኛል።የዚህን ግምታዊ ስሌት ለማወቅ በጣም ቀላል ነው። ህውሃት ከኦህደዱ እጩ አቢይ አህመድ ይልቅ የብአዴኑን ደመቀን ይመርጣል ። ሌላው ድርጅት ዴኢህዴን የህውሃት የጓሮ እርሻና የአትክልት ቦታ ስለሆነ በህውሃት የታዘዘውን መሪ እንድመርጥ ይደረጋል ። አቢይ አህመድ የሚያገኘው ድምፅ የኦህዴድን እና ትንሽ የብአዴንን እጆች ብቻ ነው። በዚህ ስሌት መሰረት ቀጣዩ “ቆራጣው ዮሀንስ ” የገደል ስባሪ የሚያክለው ደመቀ መኮንን ይሆናል ማለት ነው።

ለማንኛውም ለእኛ ኢትዮጵያውያን ሁነኛ መፍትሄው ሀይለማሪያም የተባለ ጉልቻ በአቢይ ወይም በደመቀ መቀየር ሳይሆን ስርነቀል ለውጥ ነው። ማንኛውም ስርዓት እንደ ሰው ይወለዳል፤ ያረጃል ይሞታል ። ወያኔ ከማረጀትም አልፎ አርጧል ። ከዚህ በኋላ ወያኔ ላባውን በማራገፍ ንስር መሆን አይችልም። በዚህም መሰረት ከልሂቃኑ የሚጠበቀው ለውጡ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት፤ ከለውጡ ቅኝት ጋር ተስማሚ የሚሆን አቋም በመያዝ፤ ለለውጥ ፈላጊው ህብረተሰብ ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ የሚመጥን ስርአት ይመጣ ዘንድ ትግሉን መቀጠል ብቻ ነው።

4 Responses to ” ቆራጣው ዮሀንስን ” ፍለጋ [ ቬሮኒካ መላኩ]

 1. የቄሩን እንቅስቃሴ በተቀናጀ ሁኔታ የሚመራ በይፋ የሚታወቅ ድርጅት ወይም አካል ስለመኖሩ ላናውቅ እንችላለን።የሚደረገውን እንቅስቃሴ ወይም ትግሉን ስንመለከት ግን በቄሩዎች መካከል ከዳር እስከዳር የመናበብና በየወቅቱ ለሚደረጉት ጥሪዎች አንድ ላይ ከመነሳት ባሻገር አልፎ የህወሃትን አፈና ተሻግሮ ከፋኖዎችና ከሌሎችም ጋር ግንኙነት ለመፍጠር ሲሞከር እናያለን።

  እነለማና አቢይም ትናንት ህወሃት/ኢህአዴግ የነበሩና ወደውም ሆነ ተገደው ወደ ትግሉ እንዲመጡና ዛሬ ላይ የመነጋገሪያ አጀንዳ ያደርጋቸው፤ ህወሃት እጁን ተጠምዝዞ የፖለቲካ እስረኞች በኢትዮጵያ የሉም በማለት ሲክድ የነበረውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከማመን አልፎ “ህገመንግቱን በአመጽ ለመናድ የተንቀሳቀሱ” በማለት አስሮ ሲያሰቃያቸው የነበሩትን ዜጎች ለመፍታት ለመገደድ፤ ህወሃትን ውልቅልቁን ያወጣውና የቆሰለ አውሬ ያደረገው የህዝቡ ትግል አካል የሆነው የቄሩ እንቅስቃሴ ስለሆነ ሊደገፍ ይገባል።እርግጥ ሲጀመር በተለትይም የመጀመሪያው እንቅስቃሴ 2015 ያልጠራ ከመሆኑም ባላይ ላብዛኞቻችን የስጋት ምንጭም ነበር ። ዛሬ ግን ያ ስጋት ያለ አይመስለኝም ሆኖም ግን በጥራትና በስትራቴጂ መመራት እንዳለበት ይታመናል። ዘላቂ መፍትሄ ሊያምጣ የሚችለውም ያ ሲሆን ነው።በተረፈ ግን ትንተናህ/ሽ እንደወትሮው ድንቅ ነው።

  ከአጻጻፍሽ/ህ እውነተኛው/ዋ ቬሩኒካ ስለምትመስዪ/ል እንኳን ደህና መጣሽ/ህ።እንዳንቺ/ተ ያሉት ትግታጎች በአሁኑ ሰአት አገራችን ትፈልጋለች። ጥንቃቄ ካልተወደደ ከመስቀለኛ መንገድ አልፈን አፋፍ ላይ እንገኛለንና ህወሃት ይዞን ገደል ስይገባ ህዝባችን ማዳን ይኖርብናል።እናት አገር ትጣራለች ልዩነታችን ለጊዜ ባለበት አቆይተን እናድናት!።

  አላህ ኢትዮጵያን ከነህዝቦቿ የባርካት።አሚን።

  Tarik
  February 27, 2018 at 7:53 am
  Reply

 2. ewnet kero man new ? semeslegn degmom endemayew kero tnshu ye oneg hbret honal elalehu. mn tlalachu ?

  eyasu belete
  February 28, 2018 at 7:34 am
  Reply

 3. ይህ ጽሑፍ በርግጥም ከሴት ልጅ ብዕር የወጣ ከሆነ ጸሐፊዋ ከሴት ቁንጮዎች ውስጥ የምትመደብ ናት፡፡ ትባረክ፡፡ መስከረም አበራንም አልረሳም፡፡ እርሱዋም ጎበዝ ጸሐፊ ናት – ሰሞኑን ጠፋ ብትልም፡፡
  ቬሮኒካ ያስቀመጠችው እውነት ማንም የሚክደው አይደለም፡፡ ስለቄሯውያን የሰጠችው አስተያየት በተለይ መሬት ጠብ አይልም፡፡ በዱባ ጥጋብ ሀገር መፍረስ የለበትም፡፡ ይህ የኦሮሞ ንቅናቄ ታላቅ ድል እያስዘገበ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን እንቅስቃሴው በነጃጋማኬሎ፣ በነአብዲሣ አጋ፣ በነፀጋየ ገ/መድኅ ዋቀዮ፣ በነ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሣ፣ በነወጣት ኢብሣ ቶሎሣ … መንፈስ ካተመራ በአክራሪዎች ሊጠለፍና ለሦስተኛ ጊዜ የማንወጣው አዘቅት ውስጥ ሊከተን ይችላል፡፡ ዘረኝትና ጎሠኝነት የት ሊያደርሰን እንደሚችል ያለፉት 30 እና 40 ዓመታት ቁልጭ አድርገው አሳይተውናል፡፡ አዲስ ወረተኛ ዘረኛ አራት ኪሎን ቢቆጣጠር ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት አይከብድም፡፡ ለነገሩ ፈጣሪም ጥሎ አይጥለንምና ከእንግዲህ እየነጋልን ይመስለኛል፡፡ አካሄዳችን ግን አስፈሪ መሆኑን መደበቅ አያስፈልግም፡፡ በዘረኝነት አረንቋ እንዲለወስና እንዲርመጠመጥ የተደረገ ትውልድ እንደቴፕ የተሞላውን እየዘረገፈ ሀገርንና ሕዝብን አይበታትንም ብሎ መደምደም ያስግራልና በተለይ ምራቅ የዋጥን ዜጎች ከደምባራና ከሰካራም አስተሳሰብ ወጥተን በምክንያት እንጓዝ፡፡ ለሌላ የጥፋት ዙር የሚወራጩ ኃይሎችን በጭፍን ከመከተል እንቆጠብ፡፡ የዝንጀሮ መንገድ ቢከተሉት ገደል… ነውና የማሰቢያ አካላችንን መጠቀም በምንችልበት ወቅት እንጠቀምበት – ኋላ ትርፉ ጸጸት ብቻ ነው፡፡ ቬሮኒካ እጅሽን ይባርከው፡፡ በሴት እንዲጠራ የፈለገ ወንድ ጸሐፊ ከጻፈውም ምርጫውን ማበር ተገቢ ነውና ዕድሜ ይስጣት፤ ልጅም ይውጣላት፡፡

  Netsanet Zeleke
  March 1, 2018 at 2:03 am
  Reply

 4. ይይህ ጽሑፍ በርግጥም ከሴት ልጅ ብዕር የወጣ ከሆነ ጸሐፊዋ ከሴት ቁንጮዎች ውስጥ የምትመደብ ናት፡፡ ትባረክ፡፡ መስከረም አበራንም አልረሳም፡፡ እርሱዋም ጎበዝ ጸሐፊ ናት – ሰሞኑን ጠፋ ብትልም፡፡
  ቬሮኒካ ያስቀመጠችው እውነት ማንም የሚክደው አይደለም፡፡ ስለቄሯውያን የሰጠችው አስተያየት በተለይ መሬት ጠብ አይልም፡፡ በዱባ ጥጋብ ሀገር መፍረስ የለበትም፡፡ ይህ የኦሮሞ ንቅናቄ ታላቅ ድል እያስመዘገበ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ነገር ግን እንቅስቃሴው በነጃጋማኬሎ፣ በነአብዲሣ አጋ፣ በነፀጋየ ገ/መድኅን ዋቀዮ፣ በነ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሣ፣ በነወጣት ኢብሣ ቶሎሣ … መንፈስ ካልተመራ በአክራሪዎች ሊጠለፍና ለሦስተኛ ጊዜ የማንወጣው አዘቅት ውስጥ ሊከተን ይችላል፡፡ ዘረኝነትና ጎሠኝነት የት ሊያደርሰን እንደሚችል ያለፉት 30 እና 40 ዓመታት ቁልጭ አድርገው አሳይተውናል፡፡ አዲስ ወረተኛ ዘረኛ አራት ኪሎን ቢቆጣጠር ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት አይከብድም፡፡ ለነገሩ ፈጣሪም ጥሎ አይጥለንምና ከእንግዲህ እየነጋልን ይመስለኛል፡፡ አካሄዳችን ግን አስፈሪ መሆኑን መደበቅ አያስፈልግም፡፡ በዘረኝነት አረንቋ እንዲለወስና እንዲርመጠመጥ የተደረገ ትውልድ እንደቴፕ የተሞላውን እየዘረገፈ ሀገርንና ሕዝብን አይበታትንም ብሎ መደምደም ያስቸግራልና በተለይ ምራቅ የዋጥን ዜጎች ከደምባራና ከሰካራም አስተሳሰብ ወጥተን በምክንያት እንጓዝ፡፡ ለሌላ የጥፋት ዙር የሚወራጩ ኃይሎችን በጭፍን ከመከተል እንቆጠብ፡፡ የዝንጀሮ መንገድ ቢከተሉት ገደል… ነውና የማሰቢያ አካላችንን መጠቀም በምንችልበት ወቅት እንጠቀምበት – ኋላ ትርፉ ጸጸት ብቻ ነው፡፡ ቬሮኒካ እጅሽን ይባርከው፡፡ በሴት እንዲጠራ የፈለገ ወንድ ጸሐፊ ከጻፈውም ምርጫውን ማክበር ተገቢ ነውና ዕድሜ ይስጣት፤ ልጅም ይውጣላት፡፡ እንዲህ ያ ፀሐፍት ባኖይሩ ምን ይውጠን ነበር – ሳይደግስ አይጣላም፡፡ ዐይናቸውን እንዳልገለጡ ቡችሎች በድንቁርና እየተርመሰመስን እንኖር ነበር፡፡ ለማንኛውም አቅል ይስጠን፡፡ ቅድሚያውን ለሰው ልጅነት እንስጥ፤ ከዚያም ለኢትዮጵያዊነት፡፡ ኦሮሞና አማራነት ወይም ትግሬነት የመጣው ከዘመናት በኋላ ነው – ሰዎች በመልክዓ ምድር ሲለያዩና ወደያቅጣጫው ሲበታተኑ፡፡ እንጂ ዱሮ ሁሉም ከአንድ ግንድ የወጣ ነው፡፡ ምግብና መጠጥ አይለያየን – ሥልጣንና ሀብት የሚለያዩት ሆድን ተመትኩዘው ነውና ለዚህ ብልጭልጭ ዓለም ተንበርክከን እንደነስብሃት ነጋና አባይ ፀሐዬ በወገናችን ላይ የሲዖልን በር አንጠርቅም፡፡ ሁሉም ያልፋል፡፡ የኅሊና ጠባሳ ግን ዕድሜ ልክ ሲጋረፍ ይኖራልና በንጹሕ ኅሊና እንፈቃቀር፡፡ ቋንቋ ደግሞ ከማረሻና ከወገል የማያንስ ወይም የማይተልቅ መገልገያ መሣሪያ ነው – የመግባቢያ ዕቃ/መሣሪያ፡፡ ያን ያህል ሊያገዳድል የሚገባው ትልቅ ነገር አይደለም፡፡ እንደሰው ሊወለድ፣ሊያድገና ሊሞት የሚችል ተራ ነገር ሰዎችን ሊያፋጅ አይገባም፡፡ ከየተጀቦንበት የራሳችን ሥሪት ትንንሽ ዓለም እንውጣና ሰው እንሁን፡፡ የሰው መሣቂያ እንደሆንን ዓለም ልታልፍ ተቃርባለችና እስኪ አሁን እንኳን ልብ እንግዛ፡፡…

  Netsanet Zeleke
  March 1, 2018 at 2:17 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<