አዋጁ!!! 

Filed under: News Feature,ነፃ አስተያየቶች |

ከመለሰ ድርቤሳ

ኦህዴድ በፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስቀረት ከፈለገ በምክር ቤቱ ካሉት ከራሱ አባላት ውጭ ውስን ድጋፍ ማግኘት ብቻው በቂ ነው፡፡ የኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 93 ቁጥር 3 (ሀ) ላይ አዋጁ በ2/3ኛ ድጋፍ ድምፅ ካልጸደቀ ውድቅ እንደሚሆን ተደንግጓል፡፡ ይህ ማለት ከ547 የምክር ቤቱ ኣባላት የ182ቱ መቃወም ብቻ አዋጁ እንዳይፀድቅ ማድረግ ይችላል፡፡ ኦህዴድ ለማሳለፍ ካልተባበረና ከራሱ አባላት ውጭ የተወሰኑትን የምክር ቤቱን አባላት ካስተባበረ በቀላሉ እንዳያልፍ ማድረግ ይችላል፡፡

ኦህዴድ ይሄን እንዲያደርግ የሚያስገድዱ ነገሮች እየተስተዋሉ ነው፡፡

1ኛ. አሁን ሁሉም ሰው ከየአቅጣጫው የሚያሰማውና በተጨባጭም የሚታየው ነገር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያሳውጅ አስገዳጅ ነገር ኣለመኖሩ ነው፡፡

2ኛ. ኦህዴድም ካለው የፖሊትካ ትኩሳት አንፃር ሲታይ አዋጁን መቃወም ነው የሚያዋጣው፡፡ አሳማኝ ባልሆነ ምክኒያት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደፈለገ ከህዝብ ጋር በፍቅር ስቦርቅበት የነበረውን ነፃ ግዛቱን አሳልፎ መስጠቱ በተለይ በአሁኑ ወሳኝ ሰኣት suicide እንደመፈፀም ነው፡፡ ለምን ቢባል አንድም የራስን ሜዳ ለሌላ አሳልፎ መስጠት ነው፡፡

ስቀጥልና ትልቁ ነገር የተማመነህን ህዝብ በግለጭ ሜዳ ላይ ትቶ እንደማፈግፈግ ስለሚታይ ህዝባዊነትህን ልያስነጥቅ ይችላል፡፡ ዞሮ ዞሮ ኦህዴድ አሁን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማሳለፍ ራስን ለጥቃት ማጋለጥ ነው፡፡ ከምሽግ ወጥቶ ሜዳ ላይ ቁሞ ጥሻ ውስጥ የተደበቀውን ጠላት ለመዋጋት እንደሚሞክር ወታደር መሆን ነው፡፡ አራት ኪሎ ለመግባት ኦሮሚያን ማጣት የለብህም፡፡ ኦሮሚያን ጠበቅ አድርገህ ከያስክ አራት ኪሎን አንተ ባትፈልግ እንኳ እሱ ራሱ ይፈልገሃል፡፡ ያላንተ ድጋፍ መኖር እንደማይችልም ለአፍተ እንኳ መዘንጋት ለብህም፡፡

ያለአንተ መኖር ስለማይችል ነው አሁን ራሱ ወንበሩ የተናጋው፡፡ ከአራት ኪሎ ወንበር ኦሮሚያን ጠቅልሎ መያዙ በስንት ሺ እጥፍ ይበልጣል፡፡ የአራት ኪሎ ወንበር በራሱ ካወቅህበት ኦሮሚያ መዳፍ ውስጥ ነው ያለው፡፡ ይሄ እንዴት ይጠፈሃል!!!??? የፌዴራል ስርኣቱን በአግባቡ ተግበረን ስለማናውቅ ነው ይሄ ነገር የማንረዳው፡፡ ኦሮሚያን በደምብ ጠቅልለን ስላልያዝን ነው ኦሮሚያ ምን ያክል ወሳኝ እንደሆነ የማንገነዘበው፡፡

ኣራት ኪሎም ቅርባችን ነው!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<