ወይ አድዋ! ባለሁለት ቢላዋ! (ሐይሉ አባይ ተገኝ)

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

ክብርና ዝና ለጀግናው አፄ ሚኒሊክና ለአድዋ አርበኞች! አድዋና የካቲትት 23 ቀን 1888 ዓ.ም!

‘የነፃነትን ጥቅም የሚያውቅ ነፃ የሆነ ህዝብ ብቻ ነው’

ነፃነት ምሴ ነውና ኢትዮጵያዊነቴ የአድዋ ድል ባለቤት አድርጎኛል!

ወይ አድዋ!

‘አድዋ በሁለት ገፅታዋ ማለትም በመከራዋ ጊዜ አንድም ኢትዮጵያውያን ጀግኖችን በማስጠለል ሌላም ወራሪን፣ ባንዳና ሹምባሽ በመፈልፈልና በማብቀልና ትታወቃለች።’

‘የነፃነትን ጥቅም የሚያውቅ ነፃ የሆነ ህዝብ ብቻ ነው’

ነፃነት ምሴ ነውና ኢትዮጵያዊነቴ የአድዋ ድል ባለቤት አድርጎኛል!

የአድዋ ገድልና ድል መረጃዎች!

በሪቻርድ ፖንክረስት ጥናት ከ73,000 እስከ 120,000 የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን በአድዋ ጦርነት ተሣትፈዋል:: ከዚሁም ህብረ ቀለማት ዘማቾች የሸዋ ጦር በአፄ ሚኒሊክ ስር 25,000 ጠመንጃና 3,000 ፈረሰኛ፣ በእቴጌ ጣይቱ የሚመራው ጦር በ3,000 ፈረሰኞች፣ የጎጃም ጦር በንጉሥ ተክለሃይማኖት አመራር 5,000 ፈረሰኛን ይዞ፣ በራስ መኮንን እዝ ስር 15,000 የሃረር ጦር፣ በራስ አሉላና በራስ መንገሻ ስር 12,000 ጠመንጃ የታጠቀ ሀይል፣ በራስ ሚካኤል የተደራጀ የወሎ ጦር 6,000 ጠመንጃና 5,000 ፈረሰኞችን ያካተተ ግብረሃይል ተሳትፏል:: ለዚህም ነው የአፄ ሚኒሊክ አድዋ ዘማች ጦር ኢትዮጵያዊ ነበር የምንለው:: የአድዋ ዘማቹ ህዝብ ዘር፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋና ባህል ይገለፅ የነበረው በኢትዮጵያዊነት ብቻ ነበር:: የኢትዮጵይ ጀግኖች ጠላትንም የገጠሙት በጎሣ ፌደራሊዝም ተደራጅተው፣ “በዲሞክራሲያዊ ብሄረተኝነት” ተጠፍንገውና በልዩነት ባቡር ተሣፍረው እርስ በርሳቸው እየተናጩና እየተሻኮቱም አልነበረም:: ጣሊያንንም ድል መንሳት የተቻለው ኢትዮጵያውያን በልባቸው አምነውና ፈቅደው ባሠረፁት ኢትዮጵያዊነት ነው:: ይህ ክቡር ነፃነትና ጀግና አዝማቾቹ የሚብጠለጠሉትና ጥላሸት የሚቀቡት በባርነት አፍቃሪዎች አንደበት ብቻ ነው:: ታሪክ እንደ ፖለቲካዊ አጀንዳ በድምፅ ብልጫ አይዘወርም:: ታሪክ ባለጋራ ብቻ ሣይሆን እሹሩሩ ባይም ባለቤት አለው:: ያውም እልፍ አእላፍ::

በደል ደረሰባቸው የተባልነው ዘማቾቹም ቂምና ቁርሾ አለመቋጠራቸውና መሪያቸው አፄ ሚኒሊክን አይንህ ለአፈር አለማለታቸው ዛሬ ላይ እነርሱን ነን ብለው በነሱ ስም እየማሉ ለሚቀጥፉት ባዶዎች እፍረትም ነው:: መሪያቸውን ብለውና ጥሪውን ተቀብለው አድዋ ድረስ “ከገዳያቸው ሚኒሊክ” ጋር መትመማቸው ለትርክቱ ፉርሽነትና ትርክቱንም ሌላ ማስረጃ ሊገኝለት ያልቻለ ባዶ ተረት ያደረገውም እውነት ይህ ነው:: በእርግጠኝነት ለመናገር ዛሬ ላይ በፀረ-ሚኒሊክነት የተሰለፉ ሃይሎች እንደሚያስተጋቡት በጊዜው በደል ደረሰባቸው የተባልነው ሰዎች ሚኒልክን ሲረግሙ ወይም በርሱ ላይ ሲሸርቡ (conspire)አልተስተዋለም:: ከስብዕና ውጭ የሆነ የሞራል ክስረት ለትላንት ቀን ውሎ ስኬትና ድክመት ዛሬን የመክሰስ አባዜ ነው:: ታሪክ ምንም ይሁን ምንም ታሪክ ነው:: ታሪክ ያለፈ ፖለቲካም ነው:: እውነታን፣ ስምና ዜግነትን በመቀየርና በመካድ ታሪክ አይለወጥም:: ታሪክ በጊዜ ሠሌዳ የሚከናወን ሂደት በመሆኑ በፖለቲካ ሃይሌች ዝግ ስብሰባ አይከወንም:: አይወሰንም::

ለምሣሌ ያህል ፀጋዬ አራርሣ የተሰኘው የጎሣ ፓለቲከኛ እ.አ.አ በነሃሴ 21 ቀን 2017 በፌስ ቡክ ገፁ ላይ የአድዋን ገድልና ድልን ለሚያወድሱ ስለ አፄ ሚኒሊክ እንዲህ ሲል ታሪክን በትርክት ሊተካ ይሞክራል “ጥቁርነቱን ክዶ፣ “ነጭ ነኝ እያለ ኖሮ፣ ጥቁር አፍሪካዊያንን ያስፈጀና የፈጀ (ለዛውም ጡትና እጅ እየቆረጠ) ሰው በላ ወንጀለኛ እያነገሠ፤ ሚኒሊክ በዚህ ቀን ተወለደ እናክብር፣ በዚህ ቀን ሞተ እንዘክር!” እያልክ ስታበቃ “ዶናልድ ትራምፕ Neo-Nazism አስፋፋ’ኮ ብለህ አደባባይ ከወጣህ…ልብህ ወይ በክፋት ወይ በእብሪት ታውሯል ማለት ነው። ~ዘረኝነታቸውን እንኩዋን ለማያስተውሉ ሚኒሊካውያን!” ሲል አቀርሽቷል። የሚገርመው ሚኒሊክ አድዋ ላይ ያርበደበዳቸው ጣሊያኖች ጥቁር፤ እርሳቸውም ነጭ ነበሩ። ይህ “ጡት ቆራጭ” አፄ ሚኒሊክ ባይወለድ ፀጋዬ አራርሳ ወተት ሲፈልግ ከከብቶች እየጠባ ባላደገ ነበር። እነ አፄ ሚኒሊክ አድዋ ላይ የፈጁዋቸው ጣሊያኖች ጥቁሮች እንደነበሩ እኛና ታሪክ ባለማወቃችን ይህ ሰው እየነገረን ነው። በተጨማሪም ሚኒሊክ ጥቁር አፍሪካውያንን “በመፍጀቱና በማስፈጀቱ አፍሪካውያን የህብረቱን ጽ/ ቤታቸውን አዲስ አበባ ላይ እንዱሆን ወስነዋል ሊለንም አለመፈለጉ ገርሞኛል። ችራሹንም ከትራምፕ ይልቅ አፄ ሚኒሊክ ላይ ነው ሰልፍ መውጣት እያለን ናዚዝም ባልተወለደበት ዘመን የነበሩትን ሚኒሊክ ናዚ ብሎ ሊሰይምልን ይዳዳዋል። ሃሣቡ ገልቱ ሴት እንደጋገረችው ዳቦ ይፈረካከሳል። ይህ ነው መሪ “ምሁራቸው”። እንኩዋን ህዝብን ከብትን ለማገድ ብቃት የሌለው።
በአይምሯቸው ውስጥ ከሃሣብ ለፀነሱት የባርነት ስሜት (Slavish Mentality) የነፃነቱን አባት አፄ ሚኒሊክ ተጠያቂ የሚያደርጉና የሚያብጠለጥሉ ሁሉ ነፃነት የሚይቅለሸልሻቹው የባርነትና የማንነት ኪሣራ ምርኮኞችና የበታችነት ስሜት ተጠቂዎች ብቻ ናቸው::

ለነገሩ ‘ነቢይ በሐገሩ አይከበርም’ ይባል የለ?

“A prophet is without honor only in his hometown, among his relatives , and in his own household.”
Mark 6:4

2 Responses to ወይ አድዋ! ባለሁለት ቢላዋ! (ሐይሉ አባይ ተገኝ)

 1. The weyanne (TPLF)ethnic chiefs are the descendants of the local Tigray traitors and betrayers who served the Italian colonialists.The late weyanne chief tried to degrade and dismiss the Victory of Adwa and the anti-colnial struggle as the campaigns and resistance against civilization and modernity. The TPLF chiefs specifically blame the Amharas for closing the country to modernization and civilization, the poverty and backwardness in the country.

  Murad
  March 1, 2018 at 7:54 am
  Reply

  • Every aspect of modernity we see today was introduced during the reign of Menelik, be it railways,telecom,education,whatnot? They should blame governors from their own areas for the lock down during the era of the zemene mesafint.

   Desta lencho
   March 1, 2018 at 11:34 am
   Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<