የኤርትራው ቆራጥ የህዝብ አገልጋይ ሐጂ ሙሳ መሀመድ ኑር እስር ቤት ዉስጥ አረፉ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

ዲያእ የሚባለውን ኢስላማዊ ትምርት ቤት አመራር ዉስጥ ሻእቢያ መራሹ የኤርትራ መንግስት ያደረገውን ጣልቃ ገብነት በመቃወማቸው ሳቢያ ታስረው ሲሰቃዩ የነበሩት ሐጂ ሙሳ መሀመድ ኑር በትላንትናው እለት እስር ቤት ዉስጥ ማረፋቸው ታወቀ።

 

የነበረባቸውን የጤና ቀውስ ከግምት ዉስጥ በማስገባት ከእስር ቤት እንዲወጡ አማራጭ የተሰጣቸው ሐጂ ሙሳ «አብረዉኝ የታሰሩት ሰዎች ሳይፈቱ እኔ ብቻዬን አልወጣም» በማለት ለቆሙበት አላማ መስዋእት መሆናቸውን የቢቢኤን የኤርትራ ምንጮች አሳውቀዋል።

በሻቢያ የሚመራው አምባገነናዊው የኤርትራ መንግስት በአስመራ ከተማ ዉስጥ የሚገኘውን ዲያእ ኢስላማዊ ትምርት ቤት ስርዓተ-ትምርት (curriculum) በመቀየር ሴቶች ሒጃብ እንዳይለብሱ ለማድረግ ያደረገውን ጣልቃ ገብነት በቀዳሚነት በመቃወምና ድምጻቸውን በማሰማት «በክብር እሞታለሁ!» ያሉት ሐጂ ሙሳ ምኞታቸው ተሳክቶ የትዉልዱን አንገት ቀና እድርገው «በክብር ተሰዉተዋል» ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ያስረዳሉ።

የሐጂ ሙሳ መታሰርን ተከትሎ አኽርያ በመባል ከሚታወቀው የአስመራ የሙስሊሞች መንደር በርካታ ሰዎች ታፍሰው መታሰራቸው ይታወሳል። የታሰሩት ኤርትራዉያን ሁናቴና እጣ ፈንታቸው ባይታወቅም ሐጂ ሙሳ መሐመድ ኑር እስር ቤት ዉስጥ የሞቱ ብሔራዊ ጀግና ሆነው ሲታሰቡ ይኖራሉ ሲሉ ኤርትራዉያን ሙስሊሞች ያስረዳሉ።

ልክ ህወሃት መራሹ መንግስት የሙስሊሞች ተቋም የሆነውን አወሊያን ወርሶ በራሱ ካድሬዎች ለማስተዳደር በሐይማኖት ዉስጥ ጣልቃ እንደገባው ሁሉ፤ ሻእቢያ መራሹ የኤርትራ መንግስት ዲያእ የትምርት ማእከል ዉስጥ ጣልቃ ገብቶ የራሱን አስተምሮት ለመስጠትና በካድሬዎቹ አማካኝነትትምርት ቤቱን ለመውረስ ያደርገው ሙከራ ሐጂ ሙሳን በመሰሉ ቆራጥ ታጋዮች መሰናከሉን ኤርትራዉያን ሙስሊሞች ያስረዳሉ። ሻእቢያ መራሹ የኤርትራ መንግስት የገጠመውን ድንገተኛ ተቃዉሞ ለማለዘብና ኢትዮጵያ ዉስጥ የተከሰተው የሙስሊሞች ተቃዉሞ ድንበር ጥሶ ወደ ኤርትራ እንዳይዛመትበት ጥረት ማድረጉ የታወቀ ሲሆን፤ አጋጣሚው በሙስሊምና በክርስቲያን ኤርትራዉያን ዘንድ መቀራረብን የፈጠረ መሆኑ የሚዘነጋ አይደለም።

ቢቢኤን ከአስመራ ባገኘው መረጃመሰረት ሐጂ ሙሳ መሐመድ ኑር ዛሬ ብዙ የአስመራና የአካባቢው ምእምናን በተገኘበት ተቀብረዋል። ቆራጡን የህዝብ አገልጋይ አስክሬን በመሸከም በአስመራ ከተማ ዉስጥ ህዝቡ መንቀሳቀሱ ታዉቋል። የህዝቡን ብዛትና ቁጣ የተመለከተው ሻእቢያ መራሹ የኤርትራ መንግስት ከፍተኛ የወታደር ስምሪትን ያደረገ ሲሆን ህዝቡንም ለመበትን ተኩስ ከፍቷል ሲሉ የቢቢኤን የኤርትራ ምንጮች ገልጸዋል።

ቀደም ሲል ሲል ሻእቢያ መራሹ የኤርትራ መንግስት በዲያእ ትምርት ቤት ዉስጥ ጣልቃ ለመግባት ያደረገውን ሙከራ ተከትሎ ቢቢኢኤን ሰፋ ያለ ዘገባ ማቅረቡ ይታወሳል። ሟቹ ሐጂ ሙሳ ሲታሰሩ 92 አመታቸው የነበረ ሲሆን፤ ከታሰሩ በሗላ በ93 አመታቸው በሻእቢያ መራሹ መንግስት እስር ቤት ዉስጥ ከተሰቃዩ በሗላ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን!

2 Responses to የኤርትራው ቆራጥ የህዝብ አገልጋይ ሐጂ ሙሳ መሀመድ ኑር እስር ቤት ዉስጥ አረፉ

 1. “ሴቶች ሒጃብ እንዳይለብሱ ለማድረግ ያደረገውን ጣልቃ ገብነት” ዘ-ሀበሻ በማታዉቁት ጉዳይ ባትዘግቡ መልካም ነዉ- አስመራ ዉስጥ የእስልምና ዕምነት ተከታይ የሆኑ ሴቶች አይደለም ሒጃብ አይናቸዉን ብቻ የሚያሳይ ሙሉ ጥቁር ልብስ የለበሱ ሴቶች ማየት በጣም የተለመደ ነዉ- ደሞም ችግሩ የተነሳዉ ትምህርት ቤቶች ከሀይማኖት ትምህርት በተጨማሪ ሴኪዩላር የሆነ ትምህርት ማስተማር አለባቸዉ በሚል ነዉ- ይህ ደግሞ ለኦርቶዶክሱም ለካቶሊኩም የተሰጠ መመሪያ ነዉ- ከአስመራ 100 ኪሎሜትር ሲወጣ እስከ ሱዳን ጠረፍ ድረስኮ ያለዉ ህዝብ ከሞላ ጎደል እስላም ነዉ በአብዛኛዉ የሚናገረዉም አረብኛ ነዉ አንዴት ሆኖ ነዉ ይህንን ህዝብ ሒጃብ አትልበስ ብለህ የምትነግረዉ. . . አልተባለም አልተነገረም ጉዳዩ ሌላ ነዉ። እባካችሁ ስትዘግቡ ዘገባዉ ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጡ። በነገራችን ላይ ኤርትራ ዉስጥ አምባገነንነት የለም ማለቴ አይደለም- እንዲያዉም እንደ ሻዕቢያ አይነት የለየለት ክፉ አምባገንነ በአለም ላይ አለ ብዬ አላምንም- ሰሜን ኮሪያን ጨምሮ- ግን እሱም ቢሆን ባላደረገዉ መከሰስ የለበትም! እዉነቱ የተገርኳችሁ ነዉ- All in all, please don’t sensationalize stories. Tell them as they are!

  ስሜን ደብቁት አንዳልጎዳ
  March 4, 2018 at 5:34 am
  Reply

 2. ይህ ዜና ሙሉ በሙሉ እውነት ነው። እንድያውም ኤርትራ ነጻነትዋ ከተቀዳጀች ጀምሮ በህዝቡ ላይ የወረደው ስቃይና መከራ፡ የመጀመርያ ግልጽ የኣደባባይ ተቃውሞ ነው። ሓጂ ሙሳ በኤርትራዊ የተቃውሞ የታሪክ መዝገብ ሰፍሮው በጀግንነት ኣልፈዋል።

  Aman Kidane
  March 10, 2018 at 9:12 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<