ንግስቲቱ 5ተኛውን ወርቅ አጠለቀች

Filed under: News Feature,ስፖርት,የዕለቱ ዜናዎች |

(ኢትዮ-ኪክ) የአለም የቤት ውስጥ ውድድሮች ንግስት ገንዘቤ ዲባባ በእንግሊዝ በበርኒገሀም እየተካሄደ በሚገኘው የአለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በቀናት ልዮነት ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሯ አስገኝታለች።

ገንዘቤ የ1500 ሜትር ርቀቱን በ4:05.27 በመግባት ከማሸነፏ በተጨማሪም በአለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ያገኘቻቸውን የወርቆች ቁጥር 5 አድርሳለች።

One Response to ንግስቲቱ 5ተኛውን ወርቅ አጠለቀች

 1. ጠይቁ ይቅርታ።

  ሰንደቅ ዓላማችንን ገንዘቤ ወርውረሽ፤
  ያኔ ትዝ ይልሻል ስንቱን እንደአሳፈረሽ።
  ኃይሌስ ቢሆን ስንቴ አውቆ ተታለለ፤
  ጀግና እንዳልተባለ በወቸገል-ሥም ማለ።
  ፈንጂ ነው ዕውነታ ሐቅ ነው መናገር፤
  ጉጅሌ ኢትዮጵያን ከፋፍሏታል በዘር።
  ይኼን አትመስክሩ፤
  የኢትዮጵያ ሕዝብ አውቋል፤
  ግና ይቅርታችሁን ዓመታት ጠብቋል።
  እናም ሕዝቡን ስሙት አድምጡት ላንድአፍታ፤
  ታሪክ ሳይጠራችሁ የማታ የማታ፤
  ዛሬ ቁረጡና ቆማችሁ በዕውነታ፤
  እንደልጅ ማዲንጎ
  ጠይቁ ይቅርታ።
  እንደው ስንቴ ከዱን ከመካከላችን፤
  መንግሥትን ወግነው አሾፉ በሕዝባችን።
  በኪነት-በስፖርቱ በፖለቲካ-ስልጣን፤
  በምርጫ በትግል ስንቱን ጀግና አጣን።
  ይህን የሕዝብ በደል ማዲንጎ አሸንፎ፤
  አስደሰተው ሕዝቡን በይቅርታው አቅፎ።
  ሕዝቡ ትዕግስት አለው ሳይነጋ ይጠብቃል፤
  እነማን በዳዮች እንደሆኑም ያውቃል።
  እናም የበደላችሁ ያኔ ተለጥፋችሁ፤
  ዛሬውኑ ይቅርታ ጠይቁ ፈጥናችሁ።
  ባንዳውን ሳይጨምር፣ስንቱ ስው ተረታ???…
  በሆዱ በሥልጣን ለገንዘብ ተፈታ።
  ዛሬ ቁረጡና ቆማችሁ በዕውነታ፤
  እንደልጅ ማዲንጎ
  ጠይቁ ይቅርታ።

  Abiy Ethiopiawe
  March 3, 2018 at 4:58 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.