በአዲስ አበባ ያሉ የጸጥታ አካላት ቁጥር እንዲጨምር ተደረገ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መጽደቁን ተከትሎ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የጸጥታ አካላት ቁጥር እንዲጨምር መደረጉን ለማወቅ ተቻለ፡፡ ቢቢኤን እንዳገኘው መረጃ፣ በመሐል ከተማዋ፣ በተለይ ደግሞ በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች ከፌደራል እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት በተጨማሪ ወታደሮች ጭምር ተሰማርተዋል፡፡ የጸጥታ አካላቱ ቁጥር እንዲጨምር የተደረገው አንድም በህዝብ ላይ ፍርሃት ለመንዛት እና በሌላም በኩል አዋጁን በመቃወም ሰልፍ ሊደረግ ይችላል ከሚል ስጋት መሆኑን ያገኘነው መረጃ አስረድቷል፡፡

አገዛዙ፣ ትላንት እና ዛሬ በኦሮሚያ ከተሞች የተካሄዱት ጸረ-አዋጅ ሰልፎች እና ተቃውሞዎች በተለይ በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች ሊደገሙ ይችላሉ የሚል ጭንቀት ውስጥ መግባቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከተማዋ ዙሪያዋን በታጠቁ ወታደሮች እንድትወረር የተደረገውም ከዚህ ጭንቀት የተነሳ መሆኑን የገለጹት መረጃዎች፤ አልፎ አልፎ ቢሆንም በመንገድ በሚያልፉ ነዋሪዎች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ እንደሚካሄድ መረጃዎቹ ይጠቁማሉ፡፡ የአዋጁን መጽደቅ ተከትሎ የአዲስ አበባ የጸጥታ ሁኔታ በእጅጉ የተጠናከረ ሲሆን፤ ከምሽቱ አራት ሰዓት በኋላ መንገድ ላይ መታየት በጸጥታ አካላት ዓይን ውስጥ እንደሚያስገባ የዓይን እማኞች ገልጸውልናል፡፡

በቅርቡ በኦሮሚያ ከተሞች ሲካሄድ የነበረውን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ ከተሞችም አድማውን በመቀላቀል ህዝባዊ ትግሉ የአዲስ አበባን ደጃፍ እንዲረግጥ ማስቻላቸው ይታወሳል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መጽደቅ በመቃወም በኦሮሚያ ከተሞች የተጀመረው ህዝባዊ ተቃውሞ እና የስራ ማቆም አድማ፣ በተለይ በከተማዋ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች ሊከሰት እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመቃወም እየተደረገ ያለው ተቃውሞ አዲስ አበባ ከደረሰ፣ በመውደቅ ላይ የሚገኘው አገዛዝ፣ ትልቅ የፖለቲካ ሽንፈት ሊገጥመው እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡ አዲስ አበባ የሀገሪቱ ዋና ከተማ እና የውጭ ኤምባሲዎች እንዲሁም ዲፕሎማቶች መቀመጫ በመሆኗ፣ በከተማዋ የሚከሰተው ተቃውሞ ሰፊ ትርጉም እንደሚኖረውም ተንታኞቹ ያስረዳሉ፡፡ (BBN)

3 Responses to በአዲስ አበባ ያሉ የጸጥታ አካላት ቁጥር እንዲጨምር ተደረገ

 1. There is NO decree that has been ratified (“yetsedeqe”). Please DO NOT say “tsedeqe’. The so called TPLF parliament rejected the decree by denying it the 2/3 vote that is required to pass it thanks to the heroic members who braved to vote NO and abstain. So, please DO NOT use “tsedeqe”. This verb is used only by the TPLF media and not by an independent media that sides with the Ethiopian people. The so called the state of emergency is the futile war declared on the Ethiopian people by the TPLF militia leaders. It is the last ditch effort on the part of the TPLF militia that is controlling the state power in Ethiopia. Let there be no doubt that TPLF will be be defeated and the Ethiopian people will prevail.

  Guyyaasaa
  March 4, 2018 at 10:32 pm
  Reply

 2. I completely agree!!

  TPLF Has used up all the tactics it has! State of emergency is the last weapon and it has failed!! It was voted against!! But you know what? TPLF’s apartheid rule was a mafia regime from hell,it can not save it self from a tragic fall. Like many dictators around the world, like Ghadafi, like Sadam Hussein, TPLF criminals will be dragged to the floor very soon, No amount of army can save this mafia regime. Derg had half a million army who abandoned Mengistu because of his cruelty. Woyane (TPLF) is more cruel and internal colonizer. EVEN fascist Italy did not commit the crime that woyane is committing on us. So, let Woyane continue in it’s crime. When the final moment comes no earthly army save it’s disgraceful fall.

  Hara Abdi
  March 5, 2018 at 12:38 am
  Reply

 3. Yetseteta Akalat weyes yeshiber Akalat?

  nabil
  March 5, 2018 at 4:00 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<