ትምህርት ቀሰማ (lesson learning) የሚባል የዉይይት መድረክ ቢዘጋጅስ ? :- ነገረ አባዱላ ለመነሻነት

Filed under: News Feature,ነፃ አስተያየቶች |

ሸንቁጥ አየለ
—————-
አባዱላ የተባለ የወያኔ አገልጋይ አንድ ሰሞን እንደ ወንድ በሚዲያ ላይ ወጣና “የፓርቲዬ ክብር ተነክቷል::የህዝቤ ክብር ተነክቷል” ሲል ደነፋ::ተቃዋሚ መሳይ አንዳንድ ጀሌዎች ግን ተስፋን እና የህዝብን ደህንነትን ከአባ ዱላ አይነቱ የወያኔ አገልጋይ ጠብቀዉ “ሆ በል” እያሉ እስክስታ ያዙ::እረ በስሙ ሁሉ ብዙ ንግድ ቤት ምናምን ተሰዬመለት ሁላ::

በርካታ አስተዋይ ሰዎች ” ተዉ አባዱላ በራሱ አዕምሮ የሚያስብ ሰዉ አይደለም::ይሄ ሰዉ በሆዱ የተገዛ ነው አሽከር ነዉ::አሁን እንዲህ የሚሆነዉ ወያኔ ተል ዕኮ ሰጥታዉ ነ” ሲሉ ቢናገሩም ሰሚ አላገኙም::ይባስ ብሎ በረከት ከኢህአዴግ ለቀቅሁ ብሎ ሲል እነ ኤርምያስ ለገሰ ሳይቀሩ እየተነሱ አስገራሚ ትንታኔ መስጠት ጀመሩ:: “በረከት ነዉ ኢህአዴግን/ህዉሃትን ብትንትኑን የሚያወጣው” የሚል ትንታኔ ሁሉ ቀረበ::

“ስጥ እንግዲህ ማለት ይሄኔ ነዉ” ብለን ዝም አልን::ለነገሩ ዝም አላልንም::የምንለዉን ብለን ዝም አልን እንጂ::ዛሬ አባዱላ ስንት ተቃዋሚ ወጣቶችን ሚስጢር ጠጋ ብሎ ክሩን በማግኘት በወያኔ ሰራዊት በዬቤቱ እያስደበደበ/እያስገደለ እንደሆነ መከራዉ የሚደርስባቸዉ እና እግዚአብሄር ብቻ ናቸዉ ያወቁት::በሚዲያ ጫጫታ በርካታ እዉነተኛ ተቃዋሚ ወጣቶች አባዱላ እዉነትም ወገናቸዉ መስሏቸዉ ስንት ሚስጢር አሳልፈዉ እንደሰጡት መገመት ይቻላል::

በአንድ ወቅት ስዬ አብርሃ የተባለ ኢትዮፕያን ያፈረሰ ሰዉዬ ነዉ ነጻ የሚያወጣን የሚሉ ታዋቂ የግል ጋዜጦች ተነስተዉ ስዬን አንግሰዉ የኢትዮጵያን ህዝብ ተቃዉሞ አፈር እንዳበሉት እናዉቃለን:: ካንዳንዶቹ ጋር የመከራከር እድል አጋጥሞኝ ነበር:: “ምን ሆናችሁ ነዉ? ስዬን እንደ ተቃዋሚ የምታነግሱት?” ሲባሉ የሚመልሱት መልስ “አሁን ቀመሩን አገኘንዉ” የሚል ነበር:: አንዳንዴ ህዝቡ ያሳዝናል::ደግሞም ያናድዳል::ሚዲያ የለፈለፈለትን ሁሉ አምኖ ሳያመዛዝን “ሆ በል ..” የሚል ይመስላል::ግን እንደዚያ አይደለም::የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉንም ነገር ያስተዉላል::ግን ማልመጥ ይወዳል እንደተባለ አንዳንድ እዉነት ያልሆኑ ነገሮች ሲነገሩት እያለመጠ ዝም ይላል::ባያለምጥ እማ ኖሮ ስህተት የሆነ ነገር አስመሳይ አክቲቪስቶች እና ተቃዋሚ መሰል ፖለቲከኞች ሲያሰራጩ የለም ተሳስታችኋል ማለት ነበረበት::

ከኦህዴድ እና ከብአዴን ዉስጥ የተወሸቁ ገልቱ የወያኔ አገልጋዮችን እንደ ሰዉ ቆጥራችሁ ተስፋ ከነዚህ ሰዎች የምትጠብቁ ሰዎች በተቃዋሚነት ተሰልፋችሁ የምትደክሙት ድካም ደግሞ ይበልጥ ያሳዝነኛል::አሁን ሰሞኑን የወያኔ አገልጋይ ገልቱ ሰዎች የተሰበሰቡበት ፓርላማ ይሄን አጸደቀ ያን አጸደቀ የሚለዉ ነገር በራሱ ይገርማል::አዉቆስ ከዚህ ፓርላማ ምን ይጠበቃል?

እባካችሁ አቢይ : ለማ: ገዱ እንቶኔ እያላችሁ በከንቱ አሁንም ህዝብ አታደናቁሩ::በወያኔ ሜዳ ዉስጥ ማንም ሰዉ (ምናልባት ልባም ቢሆን እንኳን) የህዝብም ግብና አላማ ይዞ መጫወት አይችልም::ወያኔ እያንዳንዱን ነገር ይቆጣጠራል::ይገላል::ተቃዋሚ ሁሉ በጋራ መስራት ያለበት ወያኔን ከስልጣን በማዉረድ ዲሞክራሲያዊት ሀገር መገንባትን መሰረት አድርጎ ብቻ ከሆነ ዉጤታማ ሊሆን ይቻላል::
ከአባ ዱላ አክሮባት አንድ ትምህርት ዉሰዱ::አባ ዱላ ትናንት ጀግናችሁ ነበር::ዛሬ ግን አይናችሁ እንዳፈጠጠ ፓርላማዉ የኢትዮጵያን ህዝብ እንዲገል አዋጁን እንዲያጸድቅ ዋናዉ ተዋናይ ነው::

እንዴ? እረ ትምህርት ቀሰማ (lesson learning) የሚባል ፕሮግራም ተዘጋጅቶ በአክቲቪስቶች ዉይይት ይደረግ:: እስኪ ፈቃደኛ የሆናችሁ አክቲቪስቶች የመወያያ መድረኩን አዘጋጁት እና የሀሳብ መንሸራሸር ይደረግበት:: አዉቀዉ ለማስመሰል ተቃዋሚ ነን የሚሉ ሰዎች ባይማሩበት እንኳን ህዝቡ በተወሰነ ደረጃ የጋራ ግንዛቤ ይያዝ::ወያኔ/ኢህአዴግ ዉስጥ ተስፋ የሚሆኑ ሰዎች ፈጽሞ እንደሌሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ተስፋዉን ቆርጦ እና አሟጦ ማወቅ አለበት::

አቋራጭ የሚባል የድል መንገድ የለም::በግል ህይወትም ሆነ በሀገር የመዳን እና የመበልጸግ ሂደት ዉስጥ አቋራጭ የአዬር በአዬር ንግድ ስር ያለዉ ዘላቂ መሰረት ላይ የቆመ ፍሬ አፍርቶ አያዉቅም::የድል ጎዳናዉ መራራ እና እረዥም እዉነተኛ እና ቁርጠኛ ጉዞ የሚጠይቅ ነዉ::የኢትዮጵያ ህዝብ በደንብ ሊወሳለት የሚገባዉ ከጠላቶቹ እና ኢትዮጵያን ካጠፉ ሀይሎች ምንም አይነት ተስፋ እንደማይመጣ ነዉ::ተስፋዉም በራሱ እጅ ብቻ እንደ ሆነ ተደጋግሞ ሊስተጋባ ይገባል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.