በኦሮሚያ ሁሉም ከተሞችና በጉራጌ ዞን የ3 ቀን አድማው በስኬት ተጀመረ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

(ዘ-ሐበሻ) በህገወጥ መንገድ ሕዝብ ላይ የተጫነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ ለመጠየቅ ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ የሥራ አድማ በመላው የኦሮሚያ ከተሞች እና በጉራጌ ዞን በስኬት ተጀመረ::

ዘ-ሐበሻ በፌስቡክ በቀጥታ የየከተማውን የተቃውሞ ሁኔታ ስታስተላልፍ የቆየች ሲሆን ከዘገባው ለመረዳት እንደሚቻለውም በኦሮሚያ ሁሉም ከተሞች ትራንስፖርትና ንግድ ቆሟል::

ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ አራቱም መውጫና መግቢያዎች የተዘጉ ሲሆን ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ እንዲሁም ከነቀምት ወደ ጎጃም ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳልነበር የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘግበዋል::

ከነቀምት ወደ አዲስ አበባ የሚሄዱ የጭነት መኪናዎች ባሉበት በመቆም አድማውን ሲቀላቀሉ፣ በሰበታ፣ በቡራዩ፣ በዓለም ገና የተጠናከረ አድማ ተደርጎ ውሏል::

በጉራጌ ዞን ሁሉም ከተሞችም አድማው የተጀመረ ሲሆን አንድ ታንክ ከተማውን ሲዞር እንደነበር የዓይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

በኦሮሚያ ከተሞች እየተደረገ ያለውን አድማ መንግስታዊው ሚዲያ ኢቢሲ መደበቅ ተስኖታል:: የኢቢሲን ዘገባ እዚህ ተጭነው ይመልከቱት >>>>

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.