አቶ መላኩ በቀለ በሚኒሶታ የተቋቋመው የኢትዮጵያውያን የዕርቅና የዲሞክራሲ መድረክ ስብሰባ ላይ ያደረጉት ንግግር

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

(ዘ-ሐበሻ) ልዩነቶችን አቻችሎ አንድነትን ለማጎልበት በሚል ዋና ዓላማ በሚኒሶታ የተቋቋመው የኢትዮጵያውያን የዕርቅና የዲሞክራሲ መድረክ ባለፈው ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 24, 2018 በሴንት ፖል ከተማ የተሳካ ሕዝባዊ ስብሰባ ተካሂዶ ነበር::

ከተለያዩ ማህበረሰብ አካላትና ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት የተሰባሰቡት ኢትዮጵያውያን በወቅታዊ የሃገራችን ጉዳዮች እና እንዴት ልዩነቶችን አቻችሎ ወደ አንድነት መምጣት እንደሚቻል ውይይት ተደርጓል:: በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ የተለያዩ ምሁራን እና የሃይማኖት አባቶች ንግግር ያደረጉ ሲሆን ከነዚህም መካከል የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግምባር (ኦዴግ) ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር ሃሰን ሁሴን ያደረጉትን ንግግር ከቀናት በፊት ይዘን መቅረባችን ይታወሳል::

በዛሬው ዕለት ደግሞ አቶ መላኩ በቀለ ያደረጉትን ንግግር ይዘናል – ይመልከቱት::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.