በኦሮሚያ ክልል እየተደረገ ያለው የሥራ ማቆም አድማ ለሁለተኛ ቀን እየተካሄደ ነው

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |


(ዘ-ሐበሻ) በሕገወጥ መንገድ ሕዝብ ላይ የተጫነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመቃወም እና መንግስት ቁጭ ብሎ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለሃገሪቱ ሰላም እና አንድነት ሲል እንዲደራደር ለማስገደድ በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለው የሥራ ማቆም አድማ ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ቀጥሎ ዋለ::

በትናንትናው ዕለት የሥራ ማቆም አድማ በተደረገባቸው ከተሞች በአጠቃላይ የሥራ ማቆም አድማው የቀጠለ ሲሆን የትራንስፖርት አገልግሎትም እንደቆመ ነው::

ተቃውሞ እየተደረገባቸው ባሉባቸው ቦታዎች ቄሮዎች በአካባቢው ለሚገኙና በቀን ሥራ ለሚተዳደሩ ወገኖቻችን ያላቸውን በማከፈል (በምግብም በገንዘብም) ለትግሉ ያለውን ጽናት እያጠናከሩት እንደሆነ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያስረዳል::

በተለይም ዛሬ ማክሰኞ የገበያ ቀን በሚደረግባቸው ከተሞች ሁሉም ገበያዎች ጭር ብለው ውለዋል:: በፎቶ ግራፉ ላይም በቄለም ወለጋ ቃቄ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የማክሰኞ ገበያ ተዝግቶ ይታያል::

በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉት ሰበታና ቡራዩ ከተሞች ፌደራል ፖሊሶች በግድ የተዘጉ ሱቆችን ለማስከፈት የኃይል እርምጃ ለመጠቀም የሞከሩ ቢሆንም ሕዝቡ በጽናቱ እንደቆመ ለማወቅ ተችሏል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<