የአገዛዙ ሹማምንት ግራ መጋባታቸው ታወቀ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ የሚገኘው አገዛዝ ሹማምንት በወቅታዊው የሀገሪቱ የፖለቲካ አካሄድ ግራ መጋባታቸውን ምንጮች ጠቆሙ፡፡ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ብርቱ ህዝባዊ ትግል ተከትሎ፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ብቻ ከአንዴም ሁለቴ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጀው አገዛዙ፤ ትግሉን መቀልበስ አለመቻሉ ግን ግራ እንዳጋባው ታውቋል፡፡ ገዥው ቡድን፣ በህዝባዊ ትግል አስገዳጅነት የህሊና እስረኞችን ለመፍታት መወሰኑ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ እስረኞችን በማስፈታት ብቻ ያልተገደበው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን በመቃወምም ዛሬም ተጠናክሮ መቀጠሉ እየተስተዋለ ይገኛል፡፡

ባለፈው አርብ የካቲት 23 ቀን 2010 በፓርላማ የጸደቀውን አዋጅ ተከትሎ፤ በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ ትግል ይዳፈናል ብለው አቅደው የነበሩት የአገዛዙ ሹማምንት፣ ትግሉ ከአዋጁ መጽደቅ በኋላም እየተጋጋለ መምጣቱ አሳስቧቸዋል ይላሉ-ምንጮች፡፡ ሁኔታው ከማሳሰብም አልፎ ምን ቢደረግ ትግሉ ሊቆም ይችላል የሚል ግራ መጋባት ውስጥ መውደቃቸውን ከምንጮች ገለጻ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማለት የአገዛዙ የመጨረሻ የአፈና አማራጭ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ ሆኖም ለፖለቲካዊ ቀውሱ የመጨረሻ ‹‹መፍትኤ›› ተደርጎ የታወጀው ይኸው አዋጅ፤ እንደታሰበው ትግሉን አለማቀዝቀዙ በሹማምንቱ መንደር መደናገጥን ፈጥሯል በማለት የመረጃው ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡

ህዝቡ በአልሞ ተኳሽ ወታደሮች እየተገደለ እንኳን ትግሉን አለማቆሙ፣ የአገዛዙን ሹማምንት ሽብር ውስጥ እንደከተታቸውም ምንጮቹ ያክላሉ፡፡ አዋጁ ከታወጀበት ዕለት እስከዛሬ ድረስ ያለማቋረጥ ህዝባዊ ትግል እየተደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ንጹኃን ሰዎችን ‹‹አሸባሪ›› በማድረግ የሚፈርጁት የአገዛዙ ሹማምንት፣ እነሱም በተራቸው ሽብር ውስጥ መግባታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ተቃውሞ በተደረገ ቁጥር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መመሪያ ይፋ ሆነ በማለት ደጋግመው መግለጫ የሚሰጡት፣ ከገቡበት የድንጋጤ እና የጭንቀት አዘቅ አንጻር እንደሆነም ለመረዳት ተችሏል፡፡ በተለይ ደግሞ፤ ራሱን የአዋጁ አስፈጻሚ እያለ የሚጠራውን ኮማንድ ፖስት በማዘዝ ግድያ የሚያስፈጽሙት የሕወሓት ሹማምንት፣ ያለ ማቋረጥ እየተካሄደ በሚገኘው ህዝባዊ ትግል ከፍተኛ ግራ መጋባት ውስጥ መሆናቸውን ከምንጮች ጥቆማ ለመረዳት ተችሏል፡፡

 

BBN news March 6, 2018

4 Responses to የአገዛዙ ሹማምንት ግራ መጋባታቸው ታወቀ

 1. የሲራጅ ፈጌሳ ፎቶ እዚህ ጋ ለምን ተለጠፈ? ሲራጅ ባለስልጣን ይባላል እንዴ? እስኪ ምን ስልጣን አለው? ከሱ ይልቅ የአዲስ አበባ ቀበሌ አስተዳደር ባለስልጣን ነው።
  ሲራጅ ማለት የኢህአዴግ አሻንጉሊት ማለት ነው። የጉራጌ ዞን የስልጤን ህዝብ ሲበድል ከጉራጌ ካድሬዎች ጋር በመሆን ስልጤ ጉራጌ ነው በማለት አብሮ ሲበድል ነበር። የስልጤ ሕዝብ ለአስር አመታት ኢሕአዴግን በመታገል ከፍተኛ መስዋዕት ከፍሎ ለአራት ዞኖች ተከፋፍሎ ተሰጥቶ የነበረውን ሕዝብ በአንድ በማሰባሰብ ዞን ሲመሰርት ኢሕአዴግ በጉልበት ሲራጅን የዞኑ አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመው።
  ኢሕአዴግ ለስልጤ ሕዝብ ምንም የተለየ ነገር አላመጣም ጭራሹንም ለሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሰጠውን መብት ለስልጤ ሕዝብ ከ10 ዓመታት በሗላ በከፍተኛ መስዋዕት ሰጠ እንጂ።
  የስልጤ ሕዝብ ታታሪ በመሆኑ (ይሕ ደሞ በመላው አገሪቱ በየሄደበት የሚታወቅ/የሚታይ ሓቅ ነው) ዞን እንዲመሰርት ከተፈቀደለት በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዞኑን በትምህርት፡ በጤና በመሳሰሉት ዘርፎች በመለወጥ ላይ ይገኛል።

  Fozi
  March 7, 2018 at 3:10 am
  Reply

 2. ተሽከረከሩ በለኛ! በአንድ አቅጣጫ ከሆነ! መቼስ ግርግባታቸውን ብዙ ጊዜ ሰማነው:: አዙሪቱ እስኪበርድላቸው ማዘጋዘጋቸው(zigzag) አይቀርም; ወይንም ይጠበቃል:: ስለዚህ ሳይበርድላቸው ሕዝብ በቁርጠኝነት አቅጣጫቸውን ማስያዝ ግድ ይለዋል:: አይደል እንዴ?

  truth
  March 7, 2018 at 9:11 am
  Reply

 3. Are you really hard working? The Siltes are widely known in Ethiopia in general and Addis Ababa in particular for their deceitful acts in trading harmful products that are damaging to the health of consumers. The are known for adulterating pepper with brick; ‘teff’ flour with sand and gypsum; butter with animal fat and banana; etc. Siltes should be deported from other regions to their beloved zone.

  Wotabo Kebede
  March 8, 2018 at 8:41 am
  Reply

  • I don’t agree with you, do you have any evidence. I know there is a project to humiliate the Silte people.
   Like any other Ethiopian they are may be part of deceitful businesses. Look the crime statistics of 2009 and 2010 EC, there is a widespread use of harmful materials in Injera and the likes almost all are not Siltes.
   What I learned from your post is that you are a very blind enemy of Silte.

   Fozi
   March 9, 2018 at 1:00 am
   Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<