ሕወሓት ኦህዴን ለማፍረስ እየሠራ ነው | የኦሮሚያ ፖሊስ ኮማንደሮች በኮማንድ ፖስቱ እየታሰሩ ነው

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

ኮማንደር ነገራ ዱፌራ

(ዘ-ሐበሻ) ሕወሓት ኦህዴድን ለማፍረስ ቀን ለሊት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ:: በኮማንድ ፖስቱ አማካኝነት የተለያዩ የክልሉ ባለስልጣናትን ወደ እስር ቤት መውሰዱን ቀጥሎበታል::

ከሁለት ቀናት በፊት የነቀምት ከተማ ከንቲባና ምክትል አስተዳደሩን ማሰሩን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ የሚታወስ ሲሆን እስሩ ቀጥሎ የኢሊባቡር ፖሊስ ኮማንደር ነገራ ዱፌራ; የምስራቅ ወለጋ ዞን ፖሊስ ኮማንደር ጫላ ተሰማ; የሐረር ፖሊስ ምክትል ኮማንደር እያሱ በኮማንድ ፖስቱ መታሰራቸው ታውቋል::

ሌሎች በርካታ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮማንደሮችና አዛዦች እየታሰሩ ሲሆን ስም ዝርዝራቸው እንደደረሰን እናቀርባለን::

የሕወሓት አገዛዝ በአሁኑ ወቅት በአቶ አባዱላ ገመዳ አማካኝነት በክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ እና በድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ዓብይ አህመድ መካከል ልዩነቶችን በመፍጠር ድርጅቱ 3 አቋም በያዙ ቡድኖች እንዲከፈል እያደረገው ሲሆን ሕወሓት ኦህዴድን አፍርሶ ሌላ ተላላኪ ኦህዴድ ለመፍጠር ከፍተኛ ሥራ እየሰራ መሆኑን የዘ-ሐበሻ/ሕብር ምንጮች ዘግበዋል::

 

ሕወሃት ኦህዴን ካፈረሰ በኋላ ወደ ብአዴን እንደሚሄድ ምንጮች እየተናገሩ ነው::

2 Responses to ሕወሓት ኦህዴን ለማፍረስ እየሠራ ነው | የኦሮሚያ ፖሊስ ኮማንደሮች በኮማንድ ፖስቱ እየታሰሩ ነው

 1. የጉጅሌ ጭምብሎቹ በየዓይነቱ እየተሟጠጡበት ራቁቱን አድርገን፣ሕዝብ ፊት ሰንገን ይዘን የፊጥኝ ለፍትህ ጉሮሮውን ጠምዝዘን ልናቀርበው ትንሽ መጠነኛ መስዋዕትነት ነው የቀረን።እናም ሕዝቡ ውስጥ የሚጣራ ነገር የለም፤”ማጣራት” ስለሆነ የተያያዝነው ትግል ከምንጩ ሊሆን ይገባዋል:: የነፍስ ወከፍ ብርበራ መፈለግ የአማራው ድርጅት ማጣራት ለኦሮሞውም ጥሩ ምሳሌ ሊሆን ይገባል።
  ለምሳሌ ማነው ታምራት ላይኔ(ሥሙም ያልተረጋገጠው)ከምባታ ነው ብሎ የጠረጠረ?የለም።እንደው መልከ-መልካም ስለነበረ ጠ/ሚ ሲሾም አማራ ነው ብለው ይግዛን ያላሉ አልነበሩም፤(ከትግሬው ይሻላል በማለት)ከመቃወም የታቀቡትን አንዘነጋም። ሆኖም ውስጥ ውስጡን እንደኃይለማርያም ደሳለኝ የበቀል ጥርሱን ልቡ ውስጥ በደሙ ሸሽጎ አማራውን አስፈጅቶታል፣ወይም እንዲፈጅ(እንደኦርቶዶክስ እምነታችን የፊርማ ግድያው)አስደርጎታል፤ወንጀል ነው።
  ዕውነቱ የዘር ሳይሆን በአፈፃፀም የምናየውን ውጤት ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ድርጊቶችን በማገናዘብ የተገኙ አንፃራዊ ማገናዘቢያዎች ናቸው።አማራ ተብሎ አማራን አምርሮ ገዳይ ሲሆን የቀበሮዎችን ማጭበርበር እንደፈፅጸሙ እንረዳለን።
  ይህን አቢይ የአጋጣሚ ትምህርት በቀላሉ ልንወስደው የማይገባን በሃያ ሰባት ዓመታቶቹ የተፈጸመውን ውንብድናና ግድያ:- በተለይም ከአማራው ድርጅት አመራር አባላት ጥፋት በቀላሉ ልንረዳው ይገባናል።በምሳሌ ከዚህ በታች ቀርበዋል፤እናም የኦሮሞውም ድርጅት ጊዜ ሳይፈጅ በውስጥ አሰራር ተጠርጣሪዎቹን ያለይሉኝታ፣አዎ ይሉኝታ ስለማያውቁ፤አጥብቄ እላለሁ ያለይሉኝታ ለድርጅቱ ደህንነት በማለት በማግለል መጀመር አለባቸው።
  በተለይም የኦሮሞው ድርጅት ፍዳ-መከራውን የሚያየው በሁለቱ ተኩላዎች ነው፦የጎጃሜው ምናሴ(አባዱላ) እና የትግሬው ወልደኪዳን አያቱ(ወርቅነህ ገበየሁ) የተባሉት ናቸው፤የአማራዎቹ ደግሞ በዝርዝር ሰፍረዋል።
  እነለገሠ(መለስ)ዜናዊ እንደራሱ ሥም በማወናበድ፦“በህወሓት የተረቀቀውን ፕሮግራም አምነን ተወያይተን ገምቢ ፖሊሲውን ተቀብለናል” ያሉትን የሚከተሉትን አፈንጋጭ ሰዎች ጠፍጥፎ የሰራቸው ናቸው።

  ሙሉአለም አበበ፣ አማራ
  ህላዊ ዮሴፍ፣ ኤርትራ
  ሃይለ ጥላሁን፣ ትግራይ፣ እድገቱ ጎጃም
  ተፈራ ዋልዋ፣ ሲዳማ
  ታምራት ላይኔ፣ ከንባታ
  ታደሰ ካሳ፣ ትግራይ
  ዮሴፍ ረታ፣ ትግራይ፣ ኤርትራ .
  መለሰ ጥላሁን፣ አማራ፣ ትግራይ
  በረከት ስምኦን፣ ኤርትራ
  ሲሳይ አሰፋ፣ ትግራይ
  አዲሱ ለገሰ፣ ሂርና ሃረር
  ኢያሱ በላቸው፣ ትግራይ፣ አማራ

  እንግዲህ የአቶ ገብረመድህን አራዓያ ጽሁፍ በሚያስረዳው መሰረት ወያኔ በነዚህ ጸረ-አማራ ሰዎች ነው የአማራውን ድርጅት አቋቁሞ ለሀያሰባት አመታት የአማራውን ህዝብ እየገደለ እና እያስገደለ ቁጥሩ እንዲቀንስ ያደረገው።

  Abiy Ethiopiawe
  March 8, 2018 at 11:29 am
  Reply

 2. abay Ethiopia
  አስተያየትህ ወይም COMMENT ህ፡ እንደ ስምህ አይደለም። COMMENT መስጫው ቦክስ ውስጥ ያስቀመጥከው፡ አስተያየትህ እንደ አባይ ኢትዮጵያ ሳይሆን እንደነ ሃጎስና እንደ አለቆችህ በጎጥ ተጠርንፈህ የተነፈስከው አሰምስሎሃል። ምክንያቱም የነ ሃጎስን መልክተኞች እነ አባዱላን ለመመታት፣ እስከዛሬ ከተጋለጡበት ማንነታቸው፣ አንተ የተለዬ ነገር አላስቀምጥክም። የተለዬ ነገር ካሳቀመጠው ነገር አንዱ እንደ ደደቢቶች አለቆችህ ሰዎችን ሓጎስ የነበረውን አሽብር ፤ ገብረእግዚአብሄር ወልደኪዳን የነበረውን ምንትሴ እያልክ አባትቶችህ ትግሬ ወያኔው የዘራውን፤ እንደ አዲስ ማስተጋባትህ ነው። but to Late and you are really very very Narrow Minded Person. እነ ሃጎስ እባካችሁ ነቄ ብለናል ግፍ የወለደን ወጣቶች እና ላናዳምጣችሁ አትችኩብን አቦ

  ጳውሎስ
  March 9, 2018 at 5:08 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<