የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህር ስዩም ተሾመ ታሰረ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

ስዩም ተሾመ

(ዘ-ሐበሻ) በተለያዩ ድረገጾች ላይ ሳይታክት በየዕለቱ በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ አስተያየት በመስጠት የሚታወቀው የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህር፣ የአምደ-መረብ ጸሀፊ እና የፖለቲካ ተንታኝ ስዩም ተሾመ ታሰረ::

ዛሬ ጠዋት 3 ሰዓት ገደማ ወሊሶ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ኃይሎች የተወሰደው ስዩም ተሾመ የኮማንድ ፖስቱ ታጣቂዎች ወደ አዲስ አበባ እንዳጓጓዙት የዓይን እማኞች ተናግረዋል::

ስዩም ተሾመ ከዚህ ቀደምም እንዲሁ ታስሮ የተፈታ ሲሆን ይኸኛው እስር ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው::

 

ስዩም ከመታሰሩ በፊት ይህን ብሎ ነበር >>> እዚህ ጋር ተጭነው ይመልከቱት

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

<