በአሜሪካ ኢትዮጵያዊው ተማሪ በመኪና አደጋ ህይወቱ አለፈ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

(Pic. Noah with GA governor and first lady)

(አትላንታ) ኖሃ ከበደ ይባላል፣ ሃያ ሁለት ዓመቱ ነበር። እዚህ አትላንታ ጉኔት ኮሌጅ ተማሪ ነበር፣ ሊመረቅም የቀረው ጥቂት ወራቶች ነበሩ። እዚህ አትላንታ ሚሞርያል ድራይቭ የሚባለው መንገድ ላይ መኪና እየነዳ ሳለ ከቆመ ምሶሶ ጋር ባጋጠመው የመጋጨት አደጋ ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ህይወቱ አልፏል።

ይህ የሆነው ባለፈው ፌብሩዋሪ 27/2018 ነው። እናቱ ብቸኛ እናት ሆና እንዳሳደገችው የቅርብ ሰዎች ለአድማስ ሬድዮ ገልጸዋል። እናት አስከሬን ይዛ በርካታ ቤተሰብ ወዳለበት ሎስ አንጀለስ በመሄድ፣ ባለፈው ቅዳሜ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ተፈጽሟል።

ኖሃ ከበደ በትምህርቱ እጅግ ጎበዝ እንደነበር የህይወት ታሪኩ ያስረዳል። ሲመረቅም ከጆርጂያ ገዢና ባለቤታቸው ጋር ለክብሩ ፎቶ አብሮ መነሳቱንም የተያያዘው ፎቶ ያሳያል። ነፍስ ይማር። (Admas Radio)

Noah Kebede was 22. He was months away from graduation. His body was sent to LA, where many family members live and buried there.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.