የትግልና የአንድነት ጥሪ ከኢትዮጵያዊያን ተጋሩ የውይይት መድረክ፣ (ኢተውመ)

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

የካቲት 2010 ..

 

የኢትዮጵያ ህዝቦች የህወሓት/ኢህአዴግን የግፍ አገዛዝ በመቃወም የሚያካሂዱት ትግል ባሁኑ ሰዓት ከፍተኛ ደራጃ ላይ ደርሷል። ይህ ለዴሞክራሲና ለአንድነት የሚደረግ ህዝባዊ ትግል በተለይም ከ 3 ዓመት ጀምሮ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በተጠናከረ መልክ እየተካሄደ ይገኛል። በዚህ የህዝብ ትግል የተዳከመው አምባገነናዊ አገዛዝ ተገዶ የተወሰኑ የፖለቲካ እስረኞችን ቢፈታም ፣ የፖለቲካ ምህዳሩን አሰፋለሁ ያለውን ግን ተራ ማጭበርበር እንደሆነ በግልጽ እየታየ ነው። ይባስ ብሎም የህዝቡን ትግል ለመጨፍለቅ የአስቸዃይ ጊዜ አዋጅ ኣውጇል። አገዛዙ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲያውጅ ለመጀመሪያ ግዜ ባይሆንም ፣ ያሁኑ ግን በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ የታወጀ የጦርነት አዋጅ ነው። አዋጁ መሰረታዊ የሆኑ ሰብአዊ መብቶችን የሚከለክልና ለወታደሩ በየትኛው ቦታና ጊዜ ኢትዮጵያውያንን የመግደልና የማሰር የማሰቃየት ትእዛዝ የሰጠ ነው።ይህ የህወሓት/ኢህአዴግ ወንጀል ባሁኑ ሰዓት በኦሮሞ ህዝባችን ላይ እየተፈጸመ ይገኛል። ትግሉ እየተፋፈመ ሲሄድም ወንጀለኞቹ የህወሓት/ኢህአዴግ ገዢዎች በተቀረው ህዝባችን ላይ የጀመሩትን ፍጅት መቀጠላቸው የማይቀር ነው።

ኢተውመ አገዛዙ የጦርነት አዋጅ አውጆ አገሪቷን ወደ አጠቃላይ ቀውስ እያስገባት መሆኑ ስለተገነዘብን ከተለያዩ ታዋቂ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ከጀርመን፣ ቤልጀም፣ ነዘርላንድ፣ ስውዘርላንድ፣ ዩኬ፣ አሜሪካና ካናዳ በቴለ ኮንፈረንስ ተገናኝተን በጋራ በጉዳዩ መክረን አገራችን ከተጋረጠባት አደጋ በተጠናከረ ትግልና አንድነት አድነን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ምን ማድረግ አለብን የሚለውን ኣብይ ጉዳይ አስመልክቶ ቀጥሎ የተቀመጠውን ጥሪ ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ ያቀርባል።

ውድ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሆይ፣

ህወሓት/ኢህአዴግለ27 ዓመታት በመካከላችን የጥላቻ መርዝ ሲዘራ ቆይቷል። የህወሓት መሪዎች በቀደዱልን የጥፋት ቦይ በመግባት እርስ በርስ እንዳንፋጅና ጥንታዊትና ታሪካዊት የሆነችው የጋራ አገራችን ወደመበታተን እንዳታመራ ባስቸኳይ ትግላችን ማስተባበርና አንድነታችን ማጠናከር ይኖርብናል። ኢትዮጵያን ከተደቀነባት አደጋ ለማዳን በአገር ቤትም ይሁን በውጭ ሀገራት ያላችሁ ሃቀኛ የተቃዋሚ ፓርቲዎችና የሲቪል ማህበራት ትግሉን የማስተባበርና የመምራት ታሪካዊ ሃላፊነት እንዳላችሁ ለማሳሰብ እንወዳለን።አባቶቻችንና እናቶቻችን የጋራ አገራቸውን ከባዕድ ጠላቶች በጋራ ተከላክለው ለኛ እንዳስረከቡን ሁሉ ዛሬ ከውስጧ የተፈጠሩ የውስጥ ጠላቶቿ እንዳይበታትኗት በጋራ መመከት ከምንም በላይ ቅድሚ ያሊሰጠው የሚገባ የጋራ ዜግነታዊ ግዴታችን ስለሆነ፣ አገራችንን ለማዳን በጋራ እንረባረብ እንላለን።

 

ውድ በአገርቤት በብሄርና በሌላ መልክ ተደራጅታችሁ አገዛዙን በመታገል ላይ ያላችሁ ወገኖቻችን፣

በየአከባቢያችሁ በብሄር ሆነ በሌላ መልክ ተደራረጅታችሁ እየታገላችሁ ያላችሁ ወገኖች ትግላቹ አገዛዙ ላይ ብቻ ያተኮረ እንዲሆን፣ በየክልሉ የሚኖሩ ከራሳችሁ ብሄር ውጭ የሆኑ ከአገዛዙ ጋር ትስስር የሌላቸው ንጹሃን የሌላ ብሄር ዜጎች እንደራሳችሁ ብሄር አባላት አይታችሁ ከማንኛውም ወገን በህይወታቸው ሆነ ንብረታቸው ላይ ሊሰነዘርባቸው ከሚችለው ጥቃት እንድትጠብቋቸው በታላቅትህትና እንጠይቃለን።

የትግራይ ህዝብንና ህወሓትን አንድ አድርጋችሁ በትግራይ ህዝብ ላይ ጥላቻ እየሰበካችሁ ያላችሁ ወገኖች፣

ህወሓት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለሚፈጽመው ግፍ የትግራይ ህዝብ ተጠያቂ አይደለም ። የትግራይ ህዝብ እንደ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ በህወሓት ኣገዛዝ ተጨቁኖ የሚሰቃይ ህዝብ ነው።ስለሆነም የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ተቃዋሚ ነን እያላችሁ፣ህወሓትና የትግራይ ህዝብን አንድ ላይ ጨፍልቃችሁ የምታዩና በትግራይ ህዝብ ላይ ጥላቻ እያሰራጫችሁ ያላችሁ ወገኖች በእጅ አዙር የህወሓት ስራ በመስራት እኩይ የህወሓት መሪዎች ዓላማ እያሳካችሁ መሆናችሁን አውቃችሁ ይህ ድርጊታችሁ እንድታቆሙና ትግላችሁን የመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ጠላት በሆነው በህወሓት/ኢህአዴግ ላይ ብቻ እንድታካሄዱ በጥብቅ እናሳስባችሁ አለን።

ውድ የትግራይ ህዝብ ሆይ፣

የህወሓት ባለስልጣኖች በስምህና ውድ ህይወታቸውን በከፈሉት ሰማዕታት ልጆችህ ስም የሚነግዱት የግፍ አገዛዛቸውን ለማጠናከርና ለማራዘም ነው። ለዘመናት ተፋቅረህና ተከባብረህ አብረኸው ስትኖር ከነበረው ሌላው ኢትዮጵያዊ ወገንህ ጋር እንዳትቀራረብና አንድነት እንዳትፈጥር ጥላቻን ሰብከዋል ፣ አስፋፍተዋል። ይህንን እኩይ ተግባራቸውን በመገንዘብ ተደራጅተህ ትግልህን ከሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በማስተባበር ራስህንና ኢትዮጵያን ለማዳን በሚደረገው ትግል ጉልህ ሚና እንድትጫወት ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የትግራይ ምሁራንና ወጣቶች ሆይ፣

በህወሓት አፈና ምክንያት ድምጹን ማሰማት ላልቻለው የትግራይ ህዝብ ድምጽ ማሰማት ያለባችሁ፣በህዝቡ ላይ በህወሓት እየደረሰ ያለውን አፈና ለሌላው ኢትዮጵያዊ ማሳወቅ ያለባችሁ እናንተ የትግራይ ምሁራን መሆን እየተገባችሁ እስከ ዛሬ በጣት ከሚቆጠሩት ጥቂቶች ውጭ ብዙዎቻችሁ ዝምታን መምረጣችሁ በታሪክ የሚያስወቅስ ትልቅ ስህተትነው።አገር ቀውስ ውስጥ ገብታ መስቀለኛ መንገድ ላይ በምትገኝበት ባሁኑ ወቅት ዝምታ መፍትሄ ስለማይሆን በተለይ እናንተ በነጻው ዓለም የምትኖሩ የትግራይ ምሁራን ዝምታን ሰብራችሁ ለድምጽ አልባው የታፈነ የትግራይ ህዝብ ድምጽ እንድትሆኑት፣በፈለጋችሁት መንገድ ተደራጅታችሁ አገዛዙን እንድትታገሉ፣ ጥሪያችንን እናቀርብላችሁአለን።

 

ኢትዮጵያበተባበረ የልጆቿ ትግል ከውስጥ ጠላቶቿ የተደገሰላት የመበታተን አደጋትድናለች!!!

 

5 Responses to የትግልና የአንድነት ጥሪ ከኢትዮጵያዊያን ተጋሩ የውይይት መድረክ፣ (ኢተውመ)

 1. THIS IS WHAT WE ARE LOOKING. UNITED WE WIN.

  LEIKUN
  March 8, 2018 at 1:12 pm
  Reply

 2. ያኔ ወያኔ አማራን ከወልቃይት: ጠገዴ : ሁመራ :ጠለምት :ራያ : መተክል: ጉራፈርዳ ሲያፈናቅልና ሲገድል ዝም ብላችሁ አሁን የትግሬ የበላይነት በህዝብ አመፅ ሊፈርስ እንደሆነ ስትረዱ እንደተጠበቃችሁት ብቅ አላችሁ::

  እዚህ መግለጫችሁ ላይ አውቃችሁ የተዋችሁትን ልጠይቃችሁ:

  1. ወያኔ በጉልበት ከርስታቸው አፈናቅሎና መሬታቸውን ቀምቶ ላባረራቸው የሰሜን ጎንደርና(ወልቃይት…) ሰሜን ወሎ አማሮች ምን መልእክት አላችሁ?
  2. ትግሬ ስለሆኑ ብቻ የሚፈልጉትን የአዲስ አበባ ሰፈር አስፈርሰው ሊመልሱት የማይጠየቁት የባንክ ገንዘብ እየተሰጣቸው የንግድ ህንፃወችን ለገነቡትና በመቶ ሽወች ከትግራይ ክልል መጥተው አማራው አገር ወልቃይት ጠገዴ ጠለምትና ራያ ለሰፈሩ የትግራይ ሰዎችስ ምን መልእክት አላችሁ?

  ይሉኝታ የትጠፋች?
  March 8, 2018 at 5:39 pm
  Reply

 3. ትግሬ ማመን ቀብሮ ነው። ህወሓት/ዎያኔ ሲጨንቀው ጊዜ ለመግዛት የሚልካቸው የዎያኔ ቅልቦች ናቸው። ህዝቡም አነዚህ ስዎች በምንም ተአምር አምኖ መዘናጋት የለበትም። እስካሁን የት ነበሩ ነውና እንደ መስቀል ወፍ ብቅ እያሉ ዎያኔን ለመታደግ የሚመጡት? ላለፈው 27 ዓመታት የኢትዮጵያ ህዝብ ሲታረድ፥ ሲታሰር፥ ሲስደድ፥ መሬቱና ንብረቱ ሲዘረፍ ገና 100 ዓመት እንገዛቹኋለን እያሉ ሲፎክሩብን የነበሩ ስዎች አሁን ህወሓት ላይ ጀንበር መጥለቅ ስትጀምር ብቅ አሉ። ባለፈውም ህወሓት አጣብቂኝ ሲገባ ብቅ ብለው ነበር። ተመልሰው ግን ወደ ፉከራቸው ነበር የተመለሱት።

  አሁን በሰፈሩት ቁና መሰፈር የሚጀመርበት ስዓት ላይ ነን ምንም ብትወራጩ የሚሰማቹህ የለም። የኢትዮጵያ ህዝብ 27 ዓመታት ለመናቹህ ሆኖም ግን ጥጋባቹህ ለከት አጥቶ ሽቅብ ሸናቹህ። እና እየመጣባቹህ ያለው ማዕበል በጸጋ ከመቀበል አማራጭ የላቹሁም።

  ሌላው በመግለጫው “የትግራይ ህዝብንና ህወሓትን አንድ አድርጋችሁ የምታስቡ ስዎች” ብለው ላሉት ስብሃት ነጋና ሳሞራ የኑስ “ትግራይ ማለት ህወሓት ህወሓት ማለት ትግራይ ነው ብለው ሲሉ የለም አይደለም ብላቹህ አንድ መግለጫ አንኳን አላወጣቹሁም ሌላው በትግራይ ስም EFFORT ተብሎ የተቋቋመው የዝርፍያ ኩባንያ ኢትዮጵያን ሙልጭ አድርጎ ሲዘርፍ የለም እኛ EFFORT የሚባል የትግራይ ኩባንያ አናቅም ካለም ለህዝብ ግልጽ ይሁን ብላቹኋል? ስለዚህ ይህን የማዘናግያ ስልታቹህ የተበላበት እቁብ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ልብ ብለዋል።

  bandageday
  March 9, 2018 at 1:42 am
  Reply

 4. የትግራይን ህዝብ ከሌላው ወንድሞቹ ጋር ያስተሳሰረ ፣ ”ህወሃት ማለት ትግራይ ፣ትግራይ ማለት ህወሀት ” ተብሎ የትግራይን ህዝብ ጭዳ ለማደርግ የሚሞከረውን የሚንድ፣ ከጎጥ ያለፈ ሀገራዊ ምልከታ ያለው አና በብዙዎቻችን ዘንድ ሲጠበቅ የንበረውን የሰጠ ከእውነተኛ ኢትዮጵያዊ ትግራዊያን መግለጫ ነው።
  ስልጣን ላይ ያሉት የህወሃት ታጋዮች ደርግን ለመጣል ያደረጉትን መሰዋትነት የሚረሳ ባይሆንም ህዝብ የጠላቸው በትግራዊነታቸው ሳይሆን ትናንት ደርግን ለመጣል የተነሱበት ጭቆናን እና Injustice ,unequality መልሰው ራሳቸው ሲተገብሩት በመታየታቸው ነው።
  ያላሁችሁትን በርግጥ ለመሆኑ በተከታታይ ተግባራዊ እርምጃ እንደምታሳዩን እንጠብቃለን።
  ለመሆኑ AIGA FORUM እና TIGRAI ONLINE የናተን ምልከታ ይጋራሉ ??
  በርቱ !!

  Zega
  March 9, 2018 at 8:45 am
  Reply

 5. በኦሮሞ ህዝባችን በየክልሉ የሚኖሩ ከራሳችሁ ብሄር ውጭ የሆኑ ከአገዛዙ ጋር ትስስር የሌላቸው ንጹሃን የሌላ ብሄር ዜጎች እንደራሳችሁ ብሄር አባላት አይታችሁ ከማንኛውም ወገን በህይወታቸው ሆነ ንብረታቸው ላይ ሊሰነዘርባቸው ከሚችለው ጥቃት እንድትጠብቋቸው በታላቅትህትና እንጠይቃለን።
  የትግራይ ህዝብ እንደ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ በህወሓት ኣገዛዝ ተጨቁኖ የሚሰቃይ ህዝብ ነው።ስለሆነም የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ተቃዋሚ ነን እያላችሁ፣ህወሓትና የትግራይ ህዝብን አንድ ላይ ጨፍልቃችሁ የምታዩና በትግራይ ህዝብ ላይ ጥላቻ እያሰራጫችሁ ያላችሁ ወገኖች በእጅ አዙር የህወሓት ስራ በመስራት እኩይ የህወሓት መሪዎች ዓላማ እያሳካችሁ መሆናችሁን አውቃችሁ ይህ ድርጊታችሁ እንድታቆሙና ትግላችሁን የመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ጠላት በሆነው በህወሓት/ኢህአዴግ ላይ ብቻ እንድታካሄዱ በጥብቅ እናሳስባችሁ አለን።

  ፣በህዝቡ ላይ በህወሓት እየደረሰ ያለውን አፈና ለሌላው ኢትዮጵያዊ ማሳወቅ ያለባችሁ እናንተ የትግራይ ምሁራን መሆን እየተገባችሁ እስከ ዛሬ በጣት ከሚቆጠሩት ጥቂቶች ውጭ ብዙዎቻችሁ ዝምታን መምረጣችሁ በታሪክ የሚያስወቅስ ትልቅ ስህተትነው።አገር ቀውስ ውስጥ ገብታ መስቀለኛ መንገድ ላይ በምትገኝበት ባሁኑ ወቅት ዝምታ መፍትሄ ስለማይሆን በተለይ እናንተ በነጻው ዓለም የምትኖሩ የትግራይ ምሁራን
  all this is a fake statement . you are still tying to fool us . Is Oromo people the only tribe killed and wounded . tortured ? you show us your hatred to the amhara people . I am sure you are TPLF supporters . Go awayyyyy from us . Dont cheat us again and again . We have no more ears to listen to you .
  LELA BILA . AWKENACHIHUWAL .

  zenqul
  March 9, 2018 at 11:31 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.