Home » Archives by category » ነፃ አስተያየቶች (Page 3)
የ “ESFNA” ቦርድ ህዉሃት/ኢህአዴግን እና የአግ7 መሪዎችን የማደራደር ሂደቱን ጥሩ አድርጎ አቀላጠፈዉ

ሸንቁጥ አየለ ============ ESFNA  ቦርድ  5 ሰዓታት የፈጀ ዉይይት አድርጎ “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተጋበዙ ከተቃዋሚ ድርጅቶችም ሰው ይጋበዝ:: እናም ተቃዋሚዎችም አንድ ሰው ወክለው ይቅረቡ” የሚለው የውሳኔ ሃሳብ አሳልፏል የሚል ዜና አሁን ዘሀሻ አስነበበን:: እኔም ይሄን አይነት ዉሳኔ እንደሚሆን ገምቼ ነበር:: የቦርዱ ዉሳኔ ልክ ብዙ የተደከመበት እንዲመስል ብዙ ተራገበ::ስሌቱ ግን ቀላል ነዉ::እነ ሌንጮ ለታ የጀመሩትን የማደራደር እቅድ […]

Continue reading …
“ዶክተር ኢንጅነር” ሳሙኤል ዘሚካኤልና ዶክተር ኢንጅነር አብዲ ኢሌ?

ከራጆ “ዶክተር ኢንጅነር” ሳሙኤል ዘሚካኤል ለምን ታሠሩ? ሕዝቡን በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ስላጃጃሉት ወይስ በዝህ ውሸታቸው የተታለሉላቸውን ባለሀብቶች ስለዘረፉ? በአንዱ ወይም በሁለቱም ጉዳይ ዘብጥያ ከወረዱ የአብዲ ኢሌን ጉዳይ መንግስት ለምንድነው ቸል ያለው? ከአብዲ ረጅም መጠሪያዎች በጥቅቱ ክቡር የዕድሜ ልክ የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት፤ ኣቦ (አባት)፤ ኣቦ መዓን (ተወዳጁ አባት)፤ ሼክ፤ አል ሐጅ፤ ጄኔራል፤ ዶክተር፤ ኢንጅነር አብዲ መሐሙድ […]

Continue reading …
“አንቺ ታቦኪያለሽ .. ይደፋብሻል” –  ከመኳንንት ታዬ(ደ.ፀ) 

ሃገር ሁልግዜም ሃገር ናት ።ሃገር ማለት አፈሩ ድንጋዩ ማለት አደለም እና  ህዝቡ በፅናት ለራሱ የሚጠቅመውን እየወደደ እና እየፈፀመ እንዲኖር ህግ ያስገድዳል ።አንድ ሃገር፤ ሃገር የምትሆነው ብዙ ህዝብ ስለተቆጠረባት ብሎም ስለኖረባት ብቻም አደለም።ሃገር ሃገር መሆን የምትችለው ወይም የምትሆነው  ህዝብ ህዝብ ሲሆን ነው ።ህዝብ የመሆኑ ነገር እንደምን ነው ቢሉ ፤ታሪካዊ እና ማህበራዊ እሴቶቻቸውን ጠብቆው በመኖር ላይ የጋራ […]

Continue reading …
ዶ/ር አብይ አህመድ ለፌዴሬሽኑ ያቀረቡት ጥያቄ እና ድምጸ ውሳኔው! (ዳዊት ከበደ ወየሳ)

ከአርባ አመታት በፊት በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያውያን፤ የመጀመሪያ ጠቅላላ ስብሰባቸውን ቦሰተን ከተማ ላይ ሲያደርጉ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ፤ የስብሰባውን አላማ አድንቀው ለተማሪዎቹ ደብዳቤ ልከውላቸው ነበር (ሙሉውን ደብዳቤ ከዚህ በፊት ለህትመት አብቅተነዋል)። በወቅቱ የነበሩት የተማሪዎቹ መሪዎች ግን፤ የቀዳማዊ ኃይለስላሴን መንግስት የሚቃወሙ በመሆናቸው፤ ይህንን የንጉሠ ነገሥቱን አክብሮት የተሞላበት ደብዳቤ ለመላው ተማሪ ሳያስነብቡ ቀሩ። ይልቁንም የወቅቱ ተማሪዎች ንጉሠ ነገሥታቸውን […]

Continue reading …
ስለ ድሬዳዋ ዝም አንልም! – በሓይላይ ብርሃነ

ስለ ድሬዳዋ የምንጮኽው ስለተወለድንባት ስለአድግንባት ወይም ስለ ኖርንባት ብቻ አይደለም:: ስለ ድሬዳዋ የሚገደን ከተቆረቆረችበት ጊዜ ጀምሮ አብሯት የኖረው የአብሮነት እሴት :የኢትዮጵያውያን ሁሉ የማንነት አሻራ: የፍቅር ከተማነቷ: ኗሪዎቿን ሁሉ ሳትለያይና በጎሳ በሃይማኖት ሳትነጣጥል አቅፋ ና ደግፋ የመያዝ ባህሏ እየተሸረሸረ በምአስመሳይነት እየተታካ ስለሆነ ጭምር ነው:: ተወልደህ አድገህ መኖር የማትችልባት ከተማ! ድሬዳዋ በአሁን ሰአት እንኳን በቅርብ ለሚመጡ ተወልደውና […]

Continue reading …
ፕ/ሃይሌ ላሬቦ ስለ ኦሮሞ ለማስተማር ምሁራዊና ሞራላዊ ልዕልና ያንሳቸዋል

ከመኮንን ተስፋዬ ፕ/ሃይሌ ላሬቦ በመገናኛ ብዙሓን እየቀረቡ ስለኢትዮጵያ ታሪክ ገለጻ ሲያደርጉ ኦሮሞን በተመለከተ የተናገሩት ወይም የጻፉት ብዙ የኦሮሞ ምሁራንና አክቲቪስቶች ቁጣቸውን አንዲገልጹ አስገድዷል። በአንጻሩም ሐቅ ተነገረ፤ ኦሮሞዎች/ብሄረተኞች  ልክ ልካቸው ተነገራቸው በማለት ድጋፋቸውንና ደስታቸውን የገለጹ አሉ። የመናገር መብት አላቸው ተዉአቸው ብለው የጻፉም አሉ።በዚህ ምክንያት የተነሳው አቧራ እኔም አይን ውስጥ ስለገባ ዝም ማለት አልቻልኩምና የሚከተለውን ጽፌ ለኢትዮ […]

Continue reading …
መስካሪ ያጣ ታሪክ፣ጠበቃ የሌለው አገር | ከእውነቱ ፈረደ

ለግለሰቦች የሥልጣን ማርኪያና መጠቀሚያ፣ጥላቻን መበቀያ ለማድረግ ሲሉ  የሰው ልጅ ህይወቱን የሰዋለት የኢትዮጵያ ታሪክ ተጣሞ ሲነገር፣ሲውረገረግና ጨርሶ እንዲጠፋ የውሸት ዘመቻ ሲደረግበት በዚህ ትውልድ በተደጋጋሚ አስተውለናል። የዛሬው የኤርትራ ወጣት ትውልድ ስለአገሩ ታሪክ ቢጠየቅ ኢትዮጵያዊ ነጻ ዜጋ እንደነበር መመስከር ያዳግተዋል።የጎሳ ፖለቲካ ውጤት የሆኑትም የእኛ ወጣቶች  ተመሳሳይ ችግር እንደሚገጥማቸው መገመት አያቅትም።እኔ ከዚህ ወይም ከዚያ ዘር ነኝ፤ቅድሚያ ማንነቴ ዘሬ ነው […]

Continue reading …
ታላቁን ሰውዬ ያልፈቱት ለምን ይሆን ?!

(ይድነቃቸው ከበደ) — አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ከእስር እንዲፈቱ የቀረበውን የምህረት ጥያቄ ፤ ፕሬዚዳንት ሙላቱ በመቀበል ፈርመው ወደ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እንደላኩ ፤ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ እንደገለጸው ከሆነ ” አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ጨምሮ 745 ታሳሪዎች በልዩ ሁኔታ በይቅርታ ከእስር እንዲፈቱ ተወስኖል” በማለት መግለጫ መስጠቱ የሚታወቅ ነው። ሆኖም ግን ይህ መረጃ ይፋ እስከሆነበት ሰዓት ድረስ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ […]

Continue reading …
የኢትዮጵያ ትግልና የአንዳርጋቸው ጽጌ ግንኙነት ለምን የቁርባን ግንኙነት ሆነ?!

መስቀሉ አየለ የአንዳርጋቸው አባት አቶ ጽጌ ስድስት እህትና ወንድሞቻቸውን አይናቸው እያየ ለጣሊያን ባደሩ ባንዳዎች እንደ አይሲስ በገጀራ ሲታረዱ እሳቸውና አንዲት እህታቸው ብቻ ነበሩ የተረፉት። እህቲቱ ባዩት ሁኔታ ልባቸው ከተሰበረበት አልጠገን ብሎ ከሰው ሳይነጋገሩ፣ በህጻንነታቸው መንኩሰው በዘጠና አመታቸው ሞቱ። አቶ ጽጌ ግን ሮጠው ከተደበቁበት ጫካ አርበኞቹን የሚመሩ አንድ የታወቁ ደጃዝማች አግኝተዋቸው ኖሮ ለአንድ ጉራጌ ገበሬ ደብዳቤ […]

Continue reading …
የአማራ ህዝብ መድህን ዴሞክራሲ ወይስ ብሔርተኝነት?

ከመሐመድ እድሪስ (በቅዳሜው የግዮን መጽሔት እትም ላይ የቀረበ እና ለውይይት ወደዚህ የመጣ ነፃ ሀሳብ)፡፡ በጨዋ ደንብ በሀሳብ ለሚወያይ ከወዲሁ ምስጋናዬን አቀርባለሁ እንደ መንደርደሪያ… ብሔርተኝነት (Nationalism) ከ12ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በዋናነት የትውልድ ቦታን ጠቋሚ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ይውል የነበረ ቃል ቢሆንም እስከ 18ኛው ክፍለዘመን ድረስ ግን ፖለቲካዊ ትርጉም የሚሰጠውና ለፖለቲካ ዓላማ ጥቅም ላይ የሚውል አልነበረም፡፡ […]

Continue reading …
“ማኅበራዊ ሚዲያ ሊያጠፋን ነው” ኃይሌ ገ/ሥላሤ – ነፃነት ዘለቀ

ነፃነት ዘለቀ (netsanetz28@gmail.com) “ማኅበራዊ ሚዲያ ሊያጠፋን ነው” ፣ “ጌጤ ያለችው በውስጧ የምታስበውን ነው። እንደዚህ ዓይነት ቦታዎች ስትሄድ የምትናገረው በወስጥህ ያለውን በመድገም ነው” “አጋንንት የለም፣ የት ነው ያለው? ጥንቆላ፣ መተት የለም፡፡ ስፖርት ላይ የለም ውሸት ነው፣ ወሬ የወለደው ነው” “ለገንዘብ፣ለፕሮፓጋንዳ፣ የራስን ተፈላጊነት ለማጉላት… ገንዘብ ለማግኘት የሚደረገው ስራ የፈጣሪ ስራ አይደለም። ይኼ የፈጣሪ ስራ ሳይሆን የአጋንንት ስራ ነው” ከፍ […]

Continue reading …
ውሉን የሳተ የትግል ጉዞ –  ከእውነቱ ፈረደ   

የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚቋቋሙበት አንዱና ዋነኛው ዓላማ የመንግሥትን ሥልጣን ለመጨበጥ ነው።የመንግሥቱን ሥልጣን የሚጨብጡበት መንገድ እንደ አገሩ የፖለቲካ ሥርዓት የተለያዬ ቢሆንም ተልእኮአቸውን ግን አይቀይረውም። አንድ የፖለቲካ ድርጅት የራሱ ህልውና መግለጫ የሚሆን ራዕይ ፣ርዕዩተዓለም(ፍልስፍና ወይም አይዶሎጂ)፣አማራጭ የፖሊሲ ሃሳብ መዋቅርና በመዋቅር የታቀፉ አባላት ፣አባላቱን ከሕዝቡ የሚያገናኝበት መረብና ለሕዝቡ የሚያቀርበው መርሃግብር(ፕሮግራም)አባላቱ የሚተዳደሩበት ደንብና መመሪያ ካለው ድርጅት ይባላል።ይኸው ድርጅት ለመንግሥት ሥልጣን […]

Continue reading …
ሜቴክና ኢፈርት

ዶ/ር አብይ ሜቴክን በተመለከተ ሹም ሽር አድርገዋል። ደመቀን አንስተው አምባቸውን ተክተዋል። ወ/ሮ አዜብንና አቶ አስመላሽ ወልደስላሴን በቦርድ አባልነት ሰይመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሜቴክና በኢፈርት ላይ የሚወስዷቸው እርምጃዎች ይጠበቁ ነበር። ህወሀት ኢትዮጵያን እንድጥገት ላም እያለበ፡ በአጥንቷ እንድትቀር ያደርጋት በእነዚህ ተቋማት አማካኝነት ነው። ዓይን ያወጣ ዘረፋ የሚከናወንባቸው እነዚህ ተቋማት ህወሀትን በኢኮኖሚ ጡንቻው እንዲፈረጥም በማድረግ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ መጠነ […]

Continue reading …
ከራሱ ሐሳብ የተጣላው ኃይሌ – ከካሳሁን ይልማ

አትሌት ኃይሌ በጌጤ ዋሚ መታመም ዙሪያ ጋዜጠኛ አበበ ጊደይ ሸገር ላይ ላቀረበለት ጥያቄዎች አስተያየት ሰጥቷል። ኃይሌ በመልሱ ያነሳቸውን ነጥቦች አንድባ’ንድ እንመልከት 1.”ሶሻል ሚዲያ ሊያጠፋን ነው – scoial media is social crisis” ይህን ያለው የጌጤን ቪዲዮ ማህበራዊ ድረገጽ ላይ ስለተመለከተው ነው። ይሁን እንጂ ቪዲዮው የተቀረጸው በአባ ግርማ የቪዲዮ/የሚዲያ ክፍል ለመሆኑ ከዚህ በፊት የሳቸውን ስራዎችን የተመለከተ በቀላሉ […]

Continue reading …
ግልጽ ደብዳቤ ለኢሃደግ ጠቅላይ ሚነስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ  – አራት ኪሎ ቤተ መንግስት ወይም ባሉበት  | ከለገሠ ወ/ሃና

ቀን /16/9/2010 ዓም ቁጥር 0001 ግልጽ ደብዳቤ ለኢሃደግ ጠቅላይ ሚነስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ አራት ኪሎ ቤተ መንግስት ወይም ባሉበት ከለገሠ ወ/ሃና ጉዳዩ የሚከተለው ነው በመጀመሪያ ለጤናዎ እንደምን አሉ ? ቤተሰብዎስ ሠላም ናቸው የቤተመንግሥት ኑሮስ እንዴት ነው ለመዱት ? ልጆችዎስ በደንብ እየተማሩ ነው ? ከሀገር ሀገር መንከራተቱስ አላደከመዎትም ? እኔ እግዜር ይመስገን ደህና ነኝ በእርስዎ መንግሥት […]

Continue reading …
መጨረሻዎች እንደመነሻዎች አያምሩም (ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይም አንብልኝ!)

ምሕረት ዘገዬ (mz23602@gmail.com) ከጠቅላላ ዕውቀት ግብይት ባለፈ ብልኅና አስተዋይ ትግሬዎች ይህን ወረቀት በተለዬ ትኩረት ቢያነቡልኝ ደስ ይለኛል፡፡ ሕወሓት በኢትዮጵያና ሕዝቧ ላይ ያደረሰውንና እያደረሰ ያለውን ተዘርዝሮ የማያልቅ ግፍና በደል የማያውቅ የትግራይ ማኅበረሰብ አባል ይኖራል ተብሎ አይገመትም፡፡ የዚህ ሁሉ ሰቆቃና ዋይታ የዞረ ድምር ምን ሊያከትል እንደሚችል ደግሞ – በአንዳንዶች ግንዛቤ ጥቂት እንደሆኑ ቢነገርም – ቢያንስ ጤናማ አስተሳሰብ […]

Continue reading …
ዶ/ር አበባ ፈቃድ አቋሟን ግልጽ አደረገች

(SBS Amharic) ዶ/ር አበባ ፈቃደ፤ ስለ የአውስትራሊያ ጉብኝታቸው አስባብ፣ ወቅታዊው የኢትዮጵያ ጉዳዮችንና የአማራውን የትግል እንቅስቃሴ ከስነ ልቦናዊ ዕይታ ጋር አሰናስላ ትናገራለች:: “እኔ በዘር አላምንም። የሰው ልጅ ዘር አንድ ነው። በአማራ ላይ የሚደረገው ጥቃት በኢትዮጵያ ላይ የሚደረግ ነው። የሁላችንም አጀንዳ ሊሆን ይገባዋል ብዬ ነው የማምነው።” – ዶ/ር አበባ ፈቃደ

Continue reading …
ሁለቱ ሲኖዶሶች ወዴት እየሄዱ ነው? – ሊቀካህናት ምሳሌ እንግዳ ያብራራሉ

ወዴት እየሄዱ ነው? – ሊቀካህናት ምሳሌ እንግዳ ያብራራሉ

Continue reading …
ፖለቲካ በፍልስፍና መነፅር ሲመረመር – ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

ግንቦት 23፣ 2018 መግቢያ አሁን ባለንበት በ21ኛው ክፍለ-ዘመን  በእኛ አገር ብቻ ሳይሆን ከብራዚል ጀምሮ እስከ አርጀንቲናና ሜክሲኮ እንዲሁም በጠቅላላው ከሰሃራ በታች በሚገኙ አገሮች ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ቀውስ ይታያል። እንዲሁም በሳይንስና በቴክኖሎጂ መጥቆ በሚገኘውና በካፒታሊስታዊ የስልተ-ምርት ክንውን  በሚደነገገው አሜሪካና እንዲሁም አውሮፓ ምድር ውስጥ እንደየሁኔታው ከፍተኛ የፓለቲካ አለመረጋጋት ይታያል። በተለይም የስድሳና የሰባ ዐመታት የፓርቲ አወቃቀርና የፖለቲካ ልምድ ባላቸው […]

Continue reading …
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለእምነት አባቶች የሰጡት እምነትን በስራ ትምህርት! –  ከፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን (ኢኦተቤ) ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመገናኘት በስደት ከሚኖረው ከዲያስፖራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አመራሮች ጋር ዕርቀ ሰላም እንዲያወርዱ በአጽንኦ ተማጽነዋል፡፡ ይህንንም በማስመልከት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንዲህ ብለዋል፡ “በኃይማኖት መሪዎች መካከል በተለያዩ  ምክንያቶች በርካታ ልዩነቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን  ሊፈቱ የማይችሉ ልዩነቶች አይደሉም፡፡ የቤተክርስቲያን መሪዎችን ያጋጠማቸው […]

Continue reading …
በርካታ ምሁራንና አክቲቪስቶች ለአቶ ለማ መገርሳ ደብዳቤ ጻፉ – በኦሮሚያ ኣማርኛ የሥራ ቋንቋ እንዲሆንና የሌሎች ማህበረሰባት መብት እንዲጠበቅ በመጠየቅ

በኦሮሞ ክልል ኦሮምኛ የማይናገሩ ኢትዮጵያውያን በብዛት በሚኖሩባቸው ዞኖችና ወረዳዎች፣ እንዲሁም በክልሉ ኣማርኛ የሥራ ቋንቋ እንዲሆን፣ ኦሮምኛም በግዕዝ ፊደል ትምህርት እንዲሰጥና የሌሎች ማህበረሰባትን መብታቸው ተረግጦ፣ ደህንነታቸው አደጋ ላይ ወድቆ፣ ከኦሮሞው ማህበረሰብ እኩል እንዳያታዩ ያደረጉ  የክልል መንግስቱ አሰራሮች፣ ፖሊሶዎችና ሕጎች እንዲሻሻሉ ጥሪ አቅርበዋል። ቋንቋ የመግባቢያ መሳሪያ እንደሆነ የገለጹት ምሁራኑ፣ ኦሮምኛ በአንድ አካባቢ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በሌላው ህየአገሪቷ […]

Continue reading …
እውነት ለፍርድ በር ላይ ደርሳለች!!! –  ከተማ ዋቅጅራ

ለግዜአዊ ጥቅም ቤትህን በእንቧይ ካብ አትገንባ። ለፖለቲካ ትርፍ ብለህ ለህዝብ እና ለልጆችህ የውሸት ታሪክ አታስተምረው። የእምቧይ ካብ ሳይቆይ ይፈርሳልና። የውሸት ታሪክም ውሎ አድሮ ይገለጣልና ያኔ ለህዝብ እና ለልጆችህ የምትመልሰው ታጣለህ። ማጣት ብቻ ሳይሆን ህዝብህንም ልጆችህንም የውርደት ካባ እንዲለብሱ ከማድረግ ባሻገር ተሸማቀውና በሁሉ ነገር ተጠልተው እንዲኖሩም መፍረድም ጭምር ነውና። ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ በተለያየ መድረክ ላይ የሚናገሩት […]

Continue reading …
ጠ/ሚ አብይና የእስካሁን ጉዟቸው – በቀለ ደገፋ

ቀለ ደገፋ (bekeledegefa5@gmail.com) ግንቦት 2010 ዓ.ም. ዶ/ር  አብይ  የጠቅላይ  ሚኒስትርነት  ስራቸውን  ከጀመሩ  ሰባት  ያህል  ሳምንታት  ተቆጥረዋል።  ወደ ስልጣን የመጡበት መንገድ ከተለመደው እጅግ የተለየ መሆኑ እንኳን ለወገን ለባዳም  ግልፅ  ነው።  ወያኔ  እንደከዚህ በፊቱ  በአምሳሉ  ጠፍጥፎ  ያወጣቸው፤  አልያም  ህዝብ ይሆኑኛል ብሎ በድምፁ የመረጣቸው ሹም አይደሉም። አብይ በገዛ ቤታቸው ውስጥ በተፈጠረ ፍትጊያ መሀል የተከሰቱ ናቸው። አመጣጣቸው በፓርቲያቸው ውስጥ […]

Continue reading …
ስለ ኢሮብ ህዝብ ያገባኛል !

ከአምዶም ገብረሥላሴ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ስዎች ከኢሮብ ማህበረሰብ ከ ዓመታት በፊት በሸዓብያ ተጠልፈው ተወስደው እስካሁን ህልውናቸው ያልታወቀ ዜጎቻችን ናቸው። የዶ/ር ዓብይ ኣሕመድ መንግስት ከ1990 ዓ/ም ጀምሮ ብየዓመቱ በሻዕብያ ታጢቂዎች እየታፈኑ እየተወሰዱ ህልውናቸው የማይታወቁ ዜጎቻችን ሁኔታ እንዲያረጋግጡልን እንጠይቃለን። በሻዕብያ ከባዳ እስከ ሑመራ ድረስ ተጠልፈው የተወሰዱ ዜጎቻችን ህልውና ኣጣርተው እንዲመለሱ እንዲያደርጉልን እንጠይቃለን። 1 ዓብዱ ወ/ዮሃንስ ተስፉ፣ ወንድ፣ […]

Continue reading …
ሰብዓዊ መብቶችና ያገራችን ሁኔታ | ባይሳ  ዋቅ-ወያ

መግቢያ በህብረተሰብ ታሪክ ውስጥ ስለ ሰብዓዊ መብቶች የመከበር አስፈላጊነት በግልጽ መወራትና መጻፍ የተጀመረው በቅርብ ጊዜ ይሁን እንጂ፣ የሰው ልጅ በተፈጥሮው ጭቆናን የማይቀበል ግን ደግሞ በአቅም ማነስ ብቻ ለጉልበታሙ ይገዛ ነበር እንጂ፣ እንደ ሰው ማንም ከማን እንደማይበልጥና በተፈጥሮም ከአካልና የአዕምሮ ብስለት መበላለጥ ሌላ፣ ሰው በሰውነቱ እኩል እንደሆነ ሁሉም ያምናል። ለምሳሌ በተለምዶ የሴት ልጅ እንደ ወንዶች ቀስትና […]

Continue reading …
ግንቦት 20 ሲመጣ የሚታወሱኝ ሁነቶች

ከብሩክ አበጋዝ ግንቦት 20 ቀን ሲመጣ ሁልጊዜም የሚታወሱኝ እነዚያ በልጅነት ዘመኔ ያየኋቸው ፀጉራቸውን አንጨብርረው አፋቸው የሚያስተጋባ የኢህአዴግ ታጋዮች ናቸው። በዚያን ወቅት አያቴ “አየሁ ብያ” ትለኝና “አቤት” ስላት “ከደርግና ከኢህአዴግ ማን ይሻላል?” ብላ ትጠይቀኛለች፤ እኔ ሁለቱንም ምን እንደሆነ ለይቼ ስለማላውቅ ከአፌ የመጣልኝን እናገራለሁ፤ ታዲያ ይህን ጥያቄ በተለያየ ቀን ነው ደጋግማ የምትጠይቀኝ። አሁን ድረስ የሚገርመኝ “ኢህአዴግ” ብዬ […]

Continue reading …
ዶ/ር ዘላለም እሸቴ፤ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ለአገር ዕድገትና ስኬት እንደምን ርዕያቸውንና ዕውቀታቸውን ማጋራት እንዳለባቸው ግለ አተያይቸውን ያጋራሉ

ዶ/ር ዘላለም እሸቴ፤ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ለአገር ዕድገትና ስኬት እንደምን ርዕያቸውንና ዕውቀታቸውን ማጋራት እንዳለባቸው ግለ አተያይቸውን ያጋራሉ።

Continue reading …
የህዝባችን መፈናቀል እና በግፍ መገደል አንገብጋቢነት |  በፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ (ፕሮፌሰር)

በሀረር ክፍለሀገር ቁጥራቸው ወደ ዐንድ ሚሊዎን የሚጠጋ ኦሮሞዎች እና በሺህ የሚቆጠሩ ሱማሌዎች፣ እንዲሁም በሞያሌ ሻኪሾ እና ጉጂ ክልል አያሌ ለፍቶ አዳሪ ኢትዮጵያውያን ከትውልድና መኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። በርካታ ዜጎችም በግፍ ተገድለዋል። አብዲ ኢሌ የተባለ አምባገነን ጂጂጋ ላይ ከትሞ ሱማሌ ኢትዮጵያውያንን አየፈለጠና እየቆረጠ ያለልጓም ይፈነጫል። ህዝቡ ኡኡ! ቢልም የህዝቡን የስቃይ ድምፅ የሚሰማው አጥቶእል። ፍዳው የበዛበት አማራም በቤንሻንጉል ጉሙዝ […]

Continue reading …
ዶክተር አብይን እጠይቃለሁ! መጠየቅ ግዴታቸው ነው! የመጠየቅ/የመቃወም እንጅ የመደገፍ ግዴታ የለብኝም!

ከጌታቸው ሽፈራው ዶክተር አብይ ብዙውን ማስጨብጨብ ቀጥለዋል። መልካም ይሁንላቸው። መደገፍ ሀጥያት አይደለም። አይፈረድምም። ደግሞ ክፉ ክፉውን ብቻ ሲናገሩ የኖሩትን እነ መለስን እንጅ በቅርብ በጎ ሰው ያላየ ሕዝብ ለአብይ ድጋፍ ቢሰጥ አይደንቅም። የአንዳንዶቹ ግን ስሜቱ በዝቷል! ~ነውሩ ግን፣ ገና ጥሩ የሚናገሩት አብይ ስልጣን ላይ ናቸውና ጥያቄም ተቃውሞም አያሰሙ የሚል ሰሞነኛ ወቀሳ ነው። “አዲስ እረኛ ከብት አያስተኛ” […]

Continue reading …
ረሃብ… ጊዜ ይሰጣል?! – ጋዜጠኛ ወብሸት ታየ

ሰሞኑን በማሕበራዊ ሚዲያው ከሚቀርቡና ትኩረት ከሳቡ ጉዳዮች አንዱ የብሔር ማንነትን አማክሎ፤ በዜጎቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለው ከማፈናቀል አንስቶ የማንኛውንም ሰብአዊ ፍጡር ልብ በሐዘን የሚሰብር የአካል ጉዳትና የሕይወት መጥፋት መከሰት ነው። ማዘን፣ መቆጨትና ሁኔታውን ማጋለጥ፤ ከዚያ ባለፈም ተጎጂ ወገኖቻችንን ቢያንስ ካሉበት ነባራዊ ችግር ለመታደግ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ አክብሮት የሚቸረው ነው። በተለይ ሳይማር ያስተማረ፣ ከጉድለቱ አካፍሎ ለቸገረው የደረሰ፣ […]

Continue reading …