Home » Archives by category » የዕለቱ ዜናዎች
ከሲዳማ ጥያቄ ጋር ተያይዞ ለሚደረግ የትኛውም አይነት ድርደር ከሲድማ ኤጄቶች የተሰጠ የአቋም መግለጫ!!

ከሲዳማ ጥያቄ ጋር ተያይዞ ለሚደረግ የትኛውም አይነት ድርደር ከሲድማ ኤጄቶች የተሰጠ የአቋም መግለጫ!!

የሲዳማ ህዝብ የራሱን ክልል መስርቶ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር ከፍተኛ የሆነ የህይወትና የአካል መስዋእትነት ሲከፍል መቆየቱ ይታወቃል። በዚህ ሂደት በተለያዩ ግዜያት የሲዳማ ህዝብ መብቱን ለማስከበርና ህገ መንግስቱ ገቢራዊ እንዲሆን የሚጠበቅበትን ህገ መንግስታዊ ሂደቶችን ጨርሶ ወሳኝ ደረጃ ከደረሰ በኋላ አላስፈላጊ መደለያዎችንና መደራደሪያዎችን በማቅረብ እንዲሁም ታጋዮችን ነጥሎ በመምታትና በማሸማቀቅ ጥያቄያችንን ለመቀልበስ አደገኛ ፖለቲካዊ ሴራ ሲዘራ እንደነበር ይታወሳል። አሁን […]

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕረስ ሴክሬተሪ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በኢትዮጵያና ቻይና መሪዎች ውይይት ዙሪያ የሰጡት ማብራሪያ

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕረስ ሴክሬተሪ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በኢትዮጵያና ቻይና መሪዎች ውይይት ዙሪያ የሰጡት ማብራሪያ። ሰላማዊት ካሳ ከቤጂንግ የጠ/ሚ ጽ/ ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በኢትዮጵያና ቻይና መሪዎች ውይይት ዙሪያ የሰጡት ማብራሪያ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕረስ ሴክሬተሪ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በኢትዮጵያና ቻይና መሪዎች ውይይት ዙሪያ የሰጡት ማብራሪያ።ሰላማዊት ካሳ ከቤጂንግ Posted by FBC […]

Continue reading …
“የቻይና ጅብ” ክፍል 5፡ “ጅቡቲ ተበልታለች፣ አፍሪካን (ኢትዮጵያ) እንዴት እንታደጋት?” የአሜሪካ ጦር አዛዥ

  ስዩም ተሾመ በቻይና ጅብ ተከታታይ ፅሁፍ አራተኛ ክፍል ቻይና ለጅቡቲ ወደብ 1 ቢሊዮን ዶላር ብድር በመስጠት በዕዳ ጫና ሲጥ… እንዳደረገቻት ገልጩያለሁ። የዕዳ ጫናው ጅቡቲን አስጨንቋት ወደላይ ያስመልሳት ጀምሯል። በዚህ ምክንያት ሉዓላዊ መሬቷን ለመጣ ሀገር ሁሉ የጦር ሰፈር እንዲገነባበት ማከራየት እያከራየች ነው። ይህን በመጠቀም ቻይና ከሀገሯው ውጪ የመጀመሪያውን የጦር ሰፈር በጅቡቲ አቋቁማለች። በዚህ አመት የየካቲት […]

Continue reading …
ኢትዮጵያ እሰከ ፈረንጆች 2018 ዓ.ም መጨረሻ የተጠራቀመ የብድር ወለድ ሙሉ በሙሉ እንደተሠረዘላት ቻይና አስታወቀች

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና የልዑካን ቡድናቸው ከቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ዥንፒንግ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል:: በውይይቱ ወቅት ፕሬዚዳንት ዥንፒንግ የጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድን አመራርና ያለፈውን አንድ ዓመት የኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት እንደሚያደንቁ ገልፀዋል። ሀገራቸው ለኢትዮጵያን ዕድገት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥም ገልፀዋል:: የቻይና መንግሥት የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክትን ጠቀሜታ ይረዳል ያሉት ፕሬዝዳንት ዥንፒንግ ለፕሮጀክቱ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መንግሥታቸው እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል:: ጠ/ሚር […]

Continue reading …
ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው ከአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን በሰሜን ሸዋ ዞን በኤፍራታና ግድም ወረዳ ከአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ፡፡ በአካባቢው በያዝነው ወር መጀመሪያ ላይ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የሰው ህይወት መጥፋቱ እና ሀብትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ የሚታወስ ነው፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎች ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር በነበራቸው ውይይት ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር […]

Continue reading …
ኢትዮጵያን ከኤርትራ የሚያገናኙትየድንበር በሮች ተዘጉ ተባለ

ኢትዮጵያን ከኤርትራ ጋር የሚያገናኙት ሁሉም የድንበር በሮች ሙሉ በሙሉ መዘጋታቸውን የየአካባቢዎቹ ባለሥልጣናት እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ አረጋገጡ። የሁመራ-ኦማሃጀር ድንበር ባሳለፍነው ሳምንት የተዘጋ ሲሆን፤ ዛሬ ደግሞ የቡሬ-አሰብ ድንበር መዘጋቱን የአፋር ክልል የሕዝብ ግንኙነት እና ሚዲያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኦስማን እድሪስ ለቢቢሲ ተናግረዋል። የተቀሩት ሁለቱ ድንበሮች ከዚህ በፊት በተለያዩ ጊዜያት ዝግ መደረጋቸው ይታወሳል። ምንም እንኳ ድንበሮቹ ለመዘጋታቸው […]

Continue reading …
ምርጫ 2012ን እንደሚካሄድ ታሳቢ አድርጎ እየሰራ ነው

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ተጨማሪ ዝግጅትን ጠይቆታል በቀጣዩ ዓመት የሚካሄደውን ምርጫ 2012 ታሳቢ አድርጎ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ መጠየቂያ ደብዳቤ መግባቱንም ጠቅሶ፤ ለቦርዱ የመጀመሪያ ሥራው እንደመሆኑ ተጨማሪ ዝግጅትን እንደሚጠይቀው ገለጸ። የምርጫ ቦርድ የኮሙኒኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፤ ቦርዱ በየአምስት ዓመቱ የሚካሄደው ቀጣዩን ምርጫ […]

Continue reading …
የሕብር ሬዲዮ ሚያዚያ 13 ቀን 2011 ዓ.ም. ፕሮግራም

የማህበራዊ አክቲቪስቱ የጥላቻ ንግግር አስመልክቶ ስጋቱን እና የኦሮሞ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከስልጣን እነ ዶ/ር አብይን አስተዳደር ሊያነሱ መሆኑን ጨምሮ የተለያያዩ ጉዳዮችን አንስተን ተወያይተናል (ያድምጡት) የጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ አስተዳደር  በምጽዋ ወደብ ላይ የባህር ሐይል ቤዝ ሊቆረቁር ነው መባሉ ያስነሳው ሰሞነኛ  ተቃውሞ ና ድጋፍ ሲዳሰስ (ልዩ ጥንቅር) ኢትዮጵያን በብሄር ለመከፋፈል የሚፈልጉ አገሪቱን ለማፈርሰ የሚፈልጉ ጠላቶቻቸን ያቀዱትን እያስፈጸሙ መሆናቸውን […]

Continue reading …
በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎውን ተከትሎ በዱር እንስሳት ላይ ጉዳት አልደረሰም

ሚያዝያ 15/2011 በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎውን ተከትሎ በዱር እንስሳት ላይ ጉዳት አለመድረሱን የፓርኩ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የእሳት ቃጠሎውን ተከትሎ በዱር እንስሳት ላይ ጉዳት አለመድረሱን የፓርኩ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ በፓርኩ ብዝሃ ሕይወት ላይ የደረሰውን ጉዳት ለማካካስ በመጪው ክረምት በ25 ሄክታር የደን መሬት ላይ አገር በቀል ችግኞችን ለመትከል እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አበባው አዛናው ለኢዜአ እንደተናገሩት ፓርኩ ቃጠሎውን ተከትሎ በባለሙያዎች ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት በፓርኩ ሁለት ጊዜ በተከሰተው የእሳት ቃጠሎ 1ሺህ 40 ሄክታር የተፈጥሮ ሀብት ቢጎዳም፤ በዱር እንስሳቱ ላይ ጉዳት አልደረሰም። ቃጠሎውን ተከትሎ ከፌዴራልና ከክልል የተውጣጡ ባለሙያዎች ያካሄዱት ጥናት በፓርኩ ውስጥ በሚገኙ ዋልያ፣ ቀይ ቀበሮ፣ ጭላዳ ዝንጀሮና የምኒልክ ድኩላ ላይ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ተረጋግጧል ብለዋል፡፡ ቀይ ቀበሮ ለምግብነት የሚያውላቸው አይጦችም በቃጠሎው ጉዳት ይደርስባቸዋል ተብሎ ሰፊ ግምት እንደነበር የተናገሩት ኃላፊው፣ እሳቱን መቆጣጠር ከተቻለ ወዲህ ግን በርካታ አይጦች እንዳልሞቱ  መረጋገጡን ተናግረዋል፡፡ በቃጠሎው ግጭ ከተባለው የመኖሪያ አካባቢያቸው ተሰደው የነበሩ በርካታ ቀይ ቀበሮዎችም ወደ ነባሩ መኖሪያቸው በመመለስ ምግብ ፍለጋ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡ በቃጠሎው ጉዳት የደረሰበትን የፓርኩን ብዝሃ ህይወት መልሶ እንዲያገግም በመጪው ክረምት በ25 ሄክታር የደን ቦታ ከ15ሺህ በላይ ሀገር በቀል ችግኞች ለመትከል ዝግጅት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ ለፓርኩ ሥነምህዳር ተስማሚ ናቸው የተባሉ ውጨና፣ አምጃ፣ ኮሶ፣ ወይራና የግራር ዛፍ አገር በቀል ዝርያዎችም ፓርኩ ባቋቋማቸው የችግኝ ጣቢያዎች በመፈላት ላይ ናቸው ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ዝናብ መጣል ጀምሯል ያሉት አቶ አበባው፣ በሬዲዮ መገናኛ የታገዘ ጥብቅ የጥበቃ ሥርዓት በመዘርጋት በፓርኩ ስካውቶችና በኅብረተሰቡ ተሳትፎ ጥበቃ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዓለም የተፈጥሮ ቅርስነት በተመዘገበው ፓርክ ከ900 በላይ ዋልያዎች፣ 120 ቀይ ቀበሮዎችና ከ7ሺህ በላይ ጭላዳ ዝንጀሮዎች እንደሚገኙ ከፓርኩ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ በፓርኩ ዳግም ተቀስቅሶ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ የነበረውን የእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ረገድ የእስራኤል የእሳት ማጥፊያ ብርጌድ አባላትና የኬንያው ሄሊኮፕተር አብራሪ ርብርብ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

Continue reading …
ያለመኖሪያ ፈቃድ በሳኡዲ አረቢያ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ

ያለመኖሪያ ፈቃድ በሳኡዲ አረቢያ ይኖሩ የነበሩ 850 ኢትዮጵያዊያን ባሳለፍነው ሳምንት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። ተመላሾቹ በሁለት ዙር ወደ አገራቸው የገቡ ሲሆኑ 445 የሚሆኑት አርብ ሚያዚያ 11 ቀን 2011 ዓ.ም የገቡ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ 405 ደግሞ ሚያዚያ 13 2011 ዓ.ም ወደ አገራቸው መመለሳቸው ተገልጿል። ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት በራሳቸው ፈቃድ ሲሆን ቀይ ባህርን አቋርጠው በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሳኡዲ […]

Continue reading …
የኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን በሙሉ ወደ ቀያቸው ለመመለስ እንደሚሰራ ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለፁ

የኦሮሞና የአማራ ወንድማማች ህዝቦችን ግንኙነት የሚያጠናክር መድረክ በአምቦ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ሽመልስ ማፈናቀል የኋላ ቀርነት ነው፤ ይህ እንዳይደገም እንሰራለን ብለዋል፡፡ ቀደም ሲል በባህር ዳር የተዘራው ዘር ፀረ-ዴሞክራሲን ፈንግሎ ጥሎአል፤ ዛሬ በአምቦ ላይ የሚዘራው የአንድነት ዘር መቀራረብ እና ሰላም የሚረጋገጥበት ይሆናል ነው ያሉት አቶ ሽመልስ፡፡ በመድረኩ የቀድሞው የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ […]

Continue reading …
‹የአብዲሳ አጋ ልጅ›በሙአዘ ጥበባት  – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ከወራት በፊት አቶ ፍጹም አረጋ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ኃላፊ እያለ ለሥራ ጉዳይ ወደ ቢሮው ሄጄ ነበር፡፡ አንድ ረዘም ደልደል ያለ፣ ፈገግታ ከፊቱ የማይጠፋ ሰው አገኘሁ፡፡ ከዚያ በፊት በአካል አግኝቼው አላውቅም፡፡ እርሱ ግን እንደሚያውቀኝ ነገረኝ፡፡ በተደጋጋሚ ስሄድ እዚያው ቢሮ በሥራ ተጠምዶ አግኝቼዋለሁ፡፡ ከመቀራረብ ብዛት ተግባባን፡፡ ከተግባባን ላይቀር ብለን ስለ ሀገሪቱ ሁኔታ ማውራት ቀጠልን፡፡ በተለይም ስለ ኢትዮጵያ […]

Continue reading …
ኢትዮጵያዊው የኡጋንዳ አየር ኃይል ፊታውራሪ

ለዓመታት የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በጦር አውሮፕላን አብራሪነት አገልግለዋል። ሌተናንት ኮሎኔል ጌታሁን ካሳ በፈፀሟቸው ጀብዶች እና በወታደራዊ ስነምግባራቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ትልቅ የጀግንነት ሽልማት አግኝተዋል። ከእናት አገራቸው ብቻም ሳይሆን ሌተናንት ኮሎኔል ጌታሁን ከጎረቤት አገር ኡጋንዳ መንግሥትም ትልቅ ወታደራዊ ሽልማት የተበረከተላቸው የሁለት አገር ጀግና ናቸው። • የካቢኔው ሽግሽግ ምን ያመላክታል? የአየር ኃይሏ ፊታውራሪ በመሆን ለዓመታት ያገለገሏትና ከጥቂት ቀናት በፊት […]

Continue reading …
የአራት ኪሎዎቹን መንትያ ሕንፃዎች ለቤተ ክርስቲያን መመለሱን የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ፤“ተከራዮች ባሉበት ይቀጥላሉ”

ሐራ ዘተዋሕዶ ለመኖሪያና ለንግድ የተከራዩ ኹለት ባለ12 ፎቅና ኹለት መለስተኛ ሕንፃዎች ናቸው፤ በመኖሪያነት የሚጠቀሙበትም ኾነ በንግድ የተሠማሩት ተከራዮች ባሉበት ይቀጥላሉ፤ በልዩ ፖሊቲካዊ ውሳኔ እንዲመለሱላት መወሰኑን፣ የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፤ እንዲመለሱላት፣ ያለፉትና ያሉት ቅዱሳን ፓትርያርኮች በተደጋጋሚ ሲጻጻፉ ኖረዋል፤ በአቡነ ቴዎፍሎስ አመራር፣ እስከ 10ኛ ፎቅ ከገነባች በኋላ ነበር በደርግ የተነጠቀችው፤ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው 10ሺሕ ቤቶች አንዱ ኾኖ ቆይቷል፤ *** ከተወረሱባት ቤቶችና ሕንፃዎች […]

Continue reading …
እኔን ስቀሏት! – ወለላዬ ከስዊድን

“እኔ”፣ “የእኔ” ማለትን ውገሯት፣  ጣር ፍዳ ሞቷን አሳዩአት፣ መቀጣጫ አድርጋችሁ ስቀሏት፣ አርቃችሁ ቆፍራችሁ ቅበሯት። በእኔ መቃብር ላይ “እኛ” በቅሎ ይገኝ ይሁነን መዳኛ እኛነት ስትለመልም ትወልዳለች ሕዝበ ሰላም አገር ምድሩ ያብባል በአንድነት አንድ ይሆናል ፍዳ መዓቱ ይጥፋል ሞትም በሕይወት ይሞታል እናም “እኔ” ማለትን እንናቅ ጉያዋ ስር አንወሸቅ ከጀርባዋ አንደበቅ “እኔ” ናት እኛነትን የበላችው ጠባብነትን የዘራችው ወንጀል […]

Continue reading …
አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው ተሾሙ

የጨፌ ኦሮሚያ ዛሬ ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባ አቶ ሽመልስ አብዲሳን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝደንት አድርጎ ሾሟል፡፡ ጨፌው አቶ ሽመለስ አብዲሳን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ የመረጠው የቀድሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ ነው፡፡ አቶ ሽመልስ የፕሬዝዳንቱን ስራ ደርበው እንደሚሰሩ […]

Continue reading …
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሦስት ሚኒስትሮችን ሹመት አፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሦስት ሚኒስትሮችን ሹመት አፀደቀ

Continue reading …
በአዋሽ ኬላ 3 ሺህ 910 የክላሽ ጥይት በጉምሩክ የፍተሻ ሰራተኞች ተያዘ

መነሻውን ከሀረር መስመር ያደረገ 3 ሺህ 910 የክላሽ ጥይት በጉምሩክ የፍተሻ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ጥይቱ በትላንትናው ዕለት ምሽት 2፡00 አዋሽ ኬላ በጉምሩክ የፍተሻ ሰራተኞች ነው በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡ ጥይቶቹ የተያዙት በተሽከርካሪው ላይ በተሰራለት ድብቅ ቦታ ሲሆን የጉምሩክ ተቆጣጣሪዎቹ ያላቸውን ልምድ እና ብቃት በመጠቀም በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል፡፡ ሚያዝያ 8/2011 ዓ.ም በተመሳሳይ […]

Continue reading …
ባየር ሙኒክ ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ስማቸው ያረፈበትን ማልያ አበረከተ

የጀርመኑ ባየር ሙኒክ እግር ኳስ ክለብ ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ስማቸው ያረፈበት የክለቡን ማልያ በስጦታነት አበርክቷል። የባቫሪያን ግዛት ሚኒስትር – ፕሬዚዳንት ማርከስ ሶደርም ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፥ ከጀርባው 1 ቁጥር የተጻፈበትንና የፕሬዚዳንቷ ስም ያረፈበትን ማልያ አበርክተውላቸዋል። የጀርመኑ እግር ኳስ ክለብ ባየር ሙኒክ በአዲስ አበባ የእግር ኳስ አካዳሚ መክፈቱን አስታወቀ፡፡ በዚህ አካዳሚ በመደበኛነት ከባየር ሙኒክ ክለብ አሰልጣኞች እየመጡ ተጨዋቾንንና […]

Continue reading …
‹‹የተወሰደው እርምጃ አግባብነት የሌለው ነው››-የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት

አብዱልቃድር መስጂድ ላይ የተወሰደው እርምጃ አግባብነት የሌለው ነው ሲሉ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ አብዱላዚዝ ወጉ ገለጹ። የከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ ትናንት በአብዱልቃድር መስጂድ የተፈጠረው ችግር ከከተማ አስተዳደሩ እውቅና ውጭ ነው ብሏል። ትናንት ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት አካባቢ በአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሚገኘው አብዱልቃድር መስጂድ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሰዎች ላይ ለሶላት ሲጠቀሙበት […]

Continue reading …
Page 1 of 518123Next ›Last »