የኮቪድ-19 (የኮሮና ቫይረስ በሽታ) አስመልክቶ የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ

1 min read

• ከጥር 15/2012 ጀምሮ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ብቻ 125,850 በላይ የሚሆኑ መንገደኞች በሙቀት ልየታው ያለፉ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 3,538 በሽታውን ሪፖረት ካደረጉ ሃገራት የመጡ ናቸው፡፡ እንዲሁም 465 የሚሆኑት ደግሞ ባሉበት ቦታ ሆነው የጤና ክትትል አየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ነገር ግን እስካሁን በለው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺን አልተከሰተም፡፡

• ከጥር 15/2012 ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ 51 ጭምጭምታዎች ለኢንስቲትዩቱ የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Emergency Operation Center) ደርሰው በሁሉም ጥቆማዎች ላይ ማጣራት ተደርጓል፡፡

• ከነዚህም ጥቆማዎች 16ቱ የበሽታውን ምልክቶችን በማሳየታቸው እና የቻይና ጉዞ ታሪክ ስላላቸው በተለያየ ጊዜ በለይቶ ማቆያ ማእከል እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም 16ንም የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው በመረጋገጡ ወደ ሕብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል፡፡

• ለኮሮና ቫይረስ መከላከል የሚያገለግሉ የተለያዩ ግብዓቶች ለጋንዲ ጠቅላላ ሆስፒታል እንዲደርስ ተደርጓል፡፡

• የየካ ኮተቤ ሆስፒታል እና የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ባለሙያዎች ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል የትግበራ ልምምድ አድርገዋል፡፡

• የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ቅድመ ዝግጅትና ምላሽ እቅድ ባላድርሻ አካላትን በማሳተፍ ተዘጋጅቶ ተጠናቋል፡፡

• ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ቁልፍ መልዕክቶች በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች ከመዘጋጀታቸውም በላይ በሃገር ውስጥ በሚገኙ በተለያዩ ቋንቋዎች እና በውጪ ቋንቋዎች እየተተረጎሙ ይገኛሉ፡፡

• ለግንዛቤ ማስጨበጫና የስራ መተግበሪያ ቅጾች ተዘጋጅተው ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርሱ ተደርጓል፡፡

• ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ለተውጣጡ 45 በላይ ለሚሆኑ ባለሙያዎች ስለ ኮሮና ቫይረስ (COVID-19) የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ተግባቦት( communication) ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ጥንቃቄ መደረግ ያለባቸው ጉዳዮች

• የኮሮና ቫይረስ ከታየባቸው ሀገራት የመጡ መንገደኞች ወይም በዚህ ቫይረስ ከተያዙ ግለሰቦች ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ላይ የበሽታው ምልክቶች (ትኩሳት፤ ሳል፤ የትንፋሽ መቆራረጥ፣ የመተንፈስ ችግር) ከታዩ፣ ማንኛውም የህብረተሰቡ አካል በአስቸኳይ በ8335 ነጻ የስልክ መስመር ላይ በመደወል ሪፖርት እንዲያደርግ እናሳስባለን፡፡

• የበሽታው ምልክት የታየባቸው ሰዎች በሚያስነጥሱበት እና በሚያስሉበት ወቅት አፍና አፍንጫቸውን በሶፍት ወይም በክንድእንዲሸፍኑ፣ የተጠቀሙበትን ሶፍት መክደኛ በለው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ወስጥ በመጣል የበሽታውን ስርጭት በጋራ እንከላከል፡፡

• እጃቸውን በሳሙናና በንጹህ ውሃ በመታጠብ የኮሮና /COVID የቫይረስ እና ሌሎችንም መሰል በሽታዎች ስርጭት እንዲከላከሉ እንመክራለን፡፡

• በተጨማሪም ህብረተሰቡ በሀገራችን እስካአሁን በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠ ሰው አለመኖሩን አውቆ ሳይዘናጋ የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል፡፡

የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት

(ኢ.ፕ.ድ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.