በዓለም ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ በሆኑ ሰዎች ስም

1 min read

የኢትዮጵያ የጣሊያንና የጀርመን ተመራማሪዎች እስከ 100 ዓመታት የቆዩትን ናሙናዎች ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ 22 የአፍሮትሮፒካል ክልል ሀገራት ተሰብስበዉ በዓለም ላይ ካሉት አስሩ ትላልቅ ሙዚየምዎች አንዱ በሆነዉ በጀርመን ‘ሚዩኒክ የተፈጥሮ ቅርስ ቤተ መዘክር’ የተነበሩ የአፍሪካ ሌብዶፕትራ ብዝሀ ህይወት (African Moths and Butterflies Biodiversity) ናሙናዎች ላይ ባደጉት የዘረመል (DNA Barcoding) ምርምር ለሳይንስ አዲስ የሆኑ 10 ዝርያዎችን 2 ንዑስ ዝርያዎችን ያስመዘገቡ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ ሁለቱ በላቲን ሳይንሳዊ ስማቸዉ በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና በዘርፉ በርካታ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር፤ ተመራማሪና አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ኢማና ጌቱ ስም ኦርባሚያ አብይ (Orbamia abiyi Hausmann and Tujuba 2020) እና (Orbamia emanai Hausmann and Tujuba 2020) በሚል ሰይሟቸዋል፡፡

ለሳይንስ አዳዲስ ዝርያዎችን በዓለም ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ በሆኑ ሰዎች ስም መሰየም የተለመደ ሲሆን ከዚህ ቀደም በቀድሞዉ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ 14 የተለያዩ ዝርያዎች፤ 3ኛዉ አሜሪካ ፕሬዘዳንት ቶማስ ጀፈርሰን (1 ዝርያ)   ፤ በዶናልድ ትራምፕ (4 ዝርያ)፤  በ26ኛ አሜርካ ፕሬዘዳንት ቶዶር ሮስቬልት (1)፤ በ ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናያን (1) በአዶልፍ ሂትለርን (1) ወዘተ መሰየማቸዉ ይታወቃል፡፡

https://en.wikipedia.org/wiki/List_of_organisms_named_after_famous_people#List

ይህም በዘርፉ ግንባር ቀደም በሆነዉ ጆርናል (Zookeys) በትላንት የታተመ ሲሆን ሙሉ እትመቱን በዚህ ማስፈንጠሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡ doi: 10.3897/zookeys.929.50391 በተጨማሪም በካናዳ የሚገኘዉ የዓለም የዘረመል የመረጃ ቋት (BOLD Systems- The barcode of life data system) መመልከት ይቻላል፡፡

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.