/

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም ታሠሩ (የታሰሩትን 34 ሰዎች ስም ዝርዝር ይዘናል)

1 min read

Dr yakobዛሬ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3 ሰዓት ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ማህበር፣ ሰማያዊ ፓርቲ እና ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር በጋራ በመሆን “ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ክብር መስጠት የአባቶቻችን መስዋዕትነት ማራከስ ነው” በሚል የተጠራውን ሰልፍ አምባገኑ የኢህአዴግ መንግስት በርካታ የፌደራል ፖሊስ፣ የደህንነት አባላትን እና የአዲስ አበባ ፖሊሶችን በማሰማራት ሲበትን፣ የተቋማቱን ከፍተኛ አመራሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና በርካታ ወጣቶች ማሰሩ ታወቀ። አሁንም የታሳሪዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል የሚሉት የዜና ዘጋቢዎች የቀድሞውን የቅንጅት አመራር ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያምን ጨምሮ 34 ሰዎች መታሰራቸው በወጣው ስም ዝርዝር ላይ ተገልጿል፡፡ ትላንት እለት ለተቃውሞ ሰልፉ የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ ከነበሩት ውስጥ 2 የሰማያዊ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ አባላትን እንዲሁም የባለራዕይ ወጣቶች የስራ አስፈጻሚ አባላትን ጨምሮ 8 ሰዎችን በማሰር የተጀመረው ይህ የማሰር ተግባር ዛሬ ቀጥሎ የታሳሪዎቹ ቁጥር 34 ደርሷል።
ለጊዜው ስማቸው የታወቀና የታሰሩ ሰዎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው።
1. ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም
2. አቶ ታዲዎስ ታንቱ
3. አቶ ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ሊቀመንበር)
4. ስለሺ ፈይሳ (የሰማያዊ ም/ሊቀመንበር)
5. ይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ የህግ ጉዳይ ሀላፊ)
6. ሀና ዋለልኝ (የሰማያዊ የሴቶች ጉዳይ ሀላፊ)
7. ጌታነህ ባልቻ (የሰማያዊ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ)
8. ብርሀኑ ተክለያሬድ (የባለራዕይ ወጣቶች ተ/ምክትል ሊቀመንበር)
9. ያሬድ አማረ (የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ጸሀፊ)
10. ኤልሳቤጥ ወሰኔ
11. ሰለሞን ወዳጅ
12. ወይንሸት ንጉሴ
13. እየሩሳሌም ተስፋው
14. ለገሰ ማሞ
15. ትዕግስት ተገኝ
16. አማኑኤል ጊዲና
17. አለማየሁ ዘለቀ
18. አገኘሁ አሰገድ
19. ሻሚል ከድር
20. አሸብር ኪያር
21. ጌታቸው ሽፈራው
22. ግሩም አበራ
23. አቤል ሙሉ
24. ዩሀንስ ጌታቸው
25. ስማቸው ተበጀ
26. ፍቃዱ ወንዳፍራው
27. ባህረን እሸቱ
28. ሄኖክ መሀመድ
29. እንቢበል ሰርጓለም
30. አለማየሁ በቀለ
31. ዩናስ
32. የመኪናው ሹፌር
33. ዮዲት አገዘ
34. ጥላዬ ታረቀኝ

7 Comments

 1. The fascist woyane collaborating with the sons of fascist Grazianni to silence, torture, jail and murder Ethiopians is something to be expected. these fascist woyane thugs have shown time and again who they are and whose policy they are advancing. Anybody with the faintest Ethiopiawinet sentiment is atarget by the fascist woyane.

  It the fascist woyane had any feeling as an Ethiopian force, it would have staged a demonstration by itself against the building of a statue for the murderer Grazziani, who torched Ethiopians alive in their homes.

  Down with Grazziani and the fascist woyane.

 2. ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያምና እዚህ ሥማቸው የተጠቀሰው ግለሰቦች እንዲሁም እውቅናን ያገኙ ጋዜጠኛና የፖለቲካ እስረኞችን ሳይጨምር ቁጥራቸው ያልታወቀ ንፁህ ዜጎቻችን በሀገሪቱ አራቱም አቅጣጫ ይሰቃያሉ። ለመሆኑ ይህ ሀገር የማነው ? እስከመቼስ ነው ይህ የሚቀጥለው? በእርግጥ እነዲሁ በመፃፍና በመግለጫ በማውጣት ጣት በመቀሰር ይፈታልን? የዚህ እሥር ጉዳይ የአክሱምን ሃውልት መልሶ የተከለ የኪስ ገንዘብ ለህወአት/ለኢፈርት ባለሀብቶችና ባለሥልጣናት የሠጠ ለልጆቻቸው የነፃ ትምህርት የሠጠ ጥንታዊ የወራሪና ባንዳ ተሳሰረ ውለታ ከኤአት ቅድምአያት አለው ፋሺስት ኢጣሊያንን ለመቃወም መውጣት በመልስ (ሃረካት)ራዕይ መቀለድ ነው።ገንጥል፣ አስገንጥል፣አበታብጥ፣አባላው፣ልዩነታችን ውበታችን አንድነት ጠላትነት!እያለ ሲለፍፍ ሸዋ ከንፈር ሲመጥ ኖሯል አሁን ጭራሽ የኢፈርት የበኩር ልጅ”የመለስ ፋውንዴሽን ተፈጥሯልና” እዚያ ትምህርት ቤት ገብተህ ያልተመረቅህ ሁሉ ከሀገር ትባረራለህ!!ሸዋን ንቃ በለው! እንቢኝ በለው!

 3. That is what we get when we let the children of Banda and bandas rule our country. If the governement was real Ethiopian they could organize the protest leave alone to side with Graziani. However, they divided us along ethnic lines like the Italians, they want to chear us by saying the Economy is growing, thus we don’t need liberty the same as Italians. Woyane odesn’t mean (not even close) Tigreans, these mafia group should be overthrown by the Ethiopians. The more they stay in power the more Ethiopia is getting damaged.

  Down with Graziani and Meles his folllower.

  Wedi-Mekelle

 4. ከዓመታት በፊት ስሙን ለጊዜው ስሙን የዘነጋሁት ጋዜጣ “ፋሺዝም በትግራይ” የሚል ዘገባ አውጥቶ በወያኔ ጎራ ያዙኝ ልቀቁኙ ከፍተኛ ጡዘት ላይ ደርሶ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ አሁን በይፋ “ፋሺዝም በኢትዮጵያ” ተንሰራፍቶ አየነው፡፡ ይህ ጉዳይ በእርግጥ ለኢትዮጵያውያን የማንቂያ ደወል ነው ባይ ነኝ፡፡

  እነዚህ ሰዎች የባዕዳን ጉዳይ አስፈጻሚዎች ስለመሆናቸው የሚተርክ ዘገባ በኢሳት የቀረበ ሲሆን ጣልያን ኢትዮጵያን የመግዛት ስልቷን የሚያትት ነበር፡፡ ከዚህ ፊልም አንጻር ወያኔ የሚያደርገውን በጥሞና ለተገነዘበው፣

  ጣልያን ኢትዮጵያን የመበታተንና የማተራመስ አጀንዳዋን ከምዕተ ዓመት በኋላም እንዳልተወችው ያሳያል፡፡ የክልል አደረጃጀቱ (ፌደራላዊ ሥርዓቱ) ቋንቋ ተኮር መሆኑ፣ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት እንዲነሳ መደረጉ፣ የሩዶልፎ ግራዚያኒን መታሰቢያ ሐውልት ለመቃወም የተደረገው ሰላማዊ የዜጎች የተቃውሞ ድምጽ የዑዓላዊ አገር መሪ ነኝ በሚል መንግሥት መደፍጠጡ፣ ሳሊኒ ኮንስትራቶሪ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ብቸኛው የተመሰከረለት የዓለም አዋቂ ተደርጎ የኢትዮጵያን የኃይል ጓዳ ተቆጣጣሪ መሆኑ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ እንደገና መጻፍ አለበት በሚል እንደገና ለመጻፍ የሚደረገውን ላይና ታች ለተመለከተ የጣልያን ሥውር እጅ ከመቶ ዓመታት በኋላም ኢትዮጵያ ለማተራመስ የጥፋትን ጥንስስ ከመጠንሰስ አልፎ እየተገኘ መሆኑን የሚያስረዳ ነው፡፡

  ይህ መንግሥት የቫቲካን ሥውር ደባ አስፈጻሚ ባንዳ አይደለም ብሎ መሟገትም ሆነ ኢትዮጵያን ችግር ከዐረቡ ዓለም ጋር ወይም ከግብጽ ጋር ማገናኘት ቆሞ የኢትዮጵያ ሕልውና መሠረታዊ ጠላት ቫቲካን መራሹ የጣልያን አስተዳደረ መሆኑ በጥብቅ ሊፈተሽ ይገባዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.