አንድን ሕዝብ በጅምላ መፈረጅ የብልህነት እጥረት ብቻ ሳይሆን ምናልባትም የዘረኝነት ሁሉ ዘረኝነት ነው – ወንድወሰን ተክሉ

1 min read
1

የአንድነት ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የተባለ ድርጅት መሪ አቶ ሲሳይ ደጉ “የትግራይ ሕዝብ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ አለበት” በማለት የሰጡትን አስተያየት በሆነ መፅሄት ላይ ታትሞ እየተነበበ መሆኑን አየሁ:;

ለምንድነው የትግራይ ሕዝብ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቅ ያለበት ለሚለው ጥያቄ ሰውዬው ማለትም አቶ ሲሳይ ደጉ ህወሃት በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ላደረሰው በደል ሕዝቡ ይቅርታ መጠየቅ አለበት ባይ ናቸው::

ለእኔ በአቶ ሲሳይና በህወሃት መስራቾች እነ አቶ ስብሃት ነጋ ሟቹ መለስ አባይ ፀኃዬና ወዘተ መካከል የስም ልዩነት እንጂ የስብእና እና የዘረኝነትን አቋም ልዩነት አላየሁባቸውም:;

ሁለቱም ማለትም የዛሬው አቶ ሲሳይ “የትግራይ ህዝብ ይቅርታ ይጠይቅ” ሲሉ በደፈናውና በጅምላ የፈረጁ ናቸው:::

ህወሃቶች ደግሞ በ1968ዓ ም ባወጡት ድርጅታዊ ፕሮግራማቸው ላይ አጠቃላዩን የአማራን ህዝብ ጠላታችን ነው በማለት የፈረጁና ያንንም የተገበሩ እኩያንና ሀሳበ ድኩማን ናቸው:::

ሁለቱ በምን ይለያያሉ??
አንደኛው መላውን የትግራይን ህዝብ ወንጀለኛ ሲያደረግ ሌላኛው ደግሞ መላውን የአማራን ህዝብ ጠላቴ ነው ብሎ ያደረጉ ናቸው:::

ለመሆኑ ከሕግ አንፃር ብቻ ሳይሆን ከሞራልና ከመርህ አንፃር አንድን ህዝብ በጅምላ ተጠያቂ ማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ አለን??

የሀገራችንን ጉዳይ ገታ አድርገን ወደ ዓለም አቀፍ ልምዶችና ክስተቶች ስናተኩር በአውሮፓ የሂትለሯን ጀርመን;የሞሶሎኒዋን ጣሊያንን በአፍሪካ የሁቱዎቹን ሩዋንዳንና የአልበሽሯን ሱዳንን ወዘተ አስቃቂ ጭፍጨፋን የፈፀሙ ስርዓቶችን ማየት የቻልን ሲሆን ስርአቶቹ ከተገረሰሱ በኃላ ለፈፀሙት Crime against Humanity እና የዘር ጭፍጨፋ ተጠያቂ የተደረጉትና ተጠያቂ የሆኑት የስርአቱ መሪና አመራሮች እንጂ ሰፊው የጀርመን ህዝብ ወይም የጣሊያን የሩዋንዳው ሁቱና ስፊው የሱዳን ህዝብ አይደለም:;;

ህወሃት 27ዓመት ለፈፀመችው ወንጀሎች ተጠያቂ መሆን የለባትምን??

ህወሃት ስንል እንደ ድርጅት ቢያንስ ከ500ሺህ እስከ 700ሺህ አባላትን ያካተተችውን ድርጅታዊ ተቋምን ማለታችን ሲሆን በዚህም ስሌት ለአሰቃቂው የህወሃት ወንጀሎች ሙሉ ተጠያቂ ሆኖ እምናገኘው ጀሌው ትእዛዝ ተቀባዩና ተከታዩ ሳይሆን የድርጅቱ አመራር ህግና ደንብ አውጪውና አፍላቂው ፕሮፖጋንዳና ቅስቀሳን እፍላቂውና ትእዛዝ ሰጪው መረጃ ወታደራዊ ክፍል የኢኮኖሚ ክፍሉን በዋናኝነት ይዘው ትእዛዝ ሲሰጡና ሲያስፈፅሙ የነበሩት በቁጥር ተጠያቂነት እርከን ላይ የሚገኙትን ተጠያቂ የሚሆኑ ሲሆን ከእነሱ ቀጥሎ ቡድርጅታዊ መዋቅር ውስጥ በሁለተኝነት ደረጃ ረድፍ ላይ የተሰለፉትን ኃላፊዎችን ተጠያቂ ማድረግ ይቻላል- ተጠያቂም አድርጎ ለፍርድ ማቅረብ ይገባል;:

ነገር ግን የህወሃት ቁንጮ አመራሮች ለፈፀሙት ወንጀል አይደለም አጠቃላዩን የትግራይን ህዝብ ተጠያቂ ለምድረግ ይቅርና አጠቃላዩን የህወሃትን አባላትና ጀሌዎችንም እንኳን ተጠያቂ ማድረግ በሕግም ሆነ በሞራል ፈፅሞ የሚቻል እይደለም – ፈፅሞም ተገቢ አይደለም:::

እውነት ነው አጠቃላይ ህወሃቶች የትግራይ ህዝብ ተወላጅ ናቸው ግን ሰፊው የትግራይ ህዝብ በሙሉ ህወሃት ነው ብሎ ማሰብ ዘረኝነትና በጥላቻ የመታወር ውጤት ብቻ እንደሆነ ነው የምናየው::

እናም የዚህ የአቶ ሲሳይ ደጉ የተባለ ሰው “የትግራይ ህዝብ በሙሉ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ አለበት ” የሚለውን አመለካከት ግንጭአልፋ የሆነና የለየለት የዘረኝነት አቋም እንደሆነ ነው እምረዳው ::: ሆኖም የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን የሰውዬውን አባባል ጉንጭ አልፋ shallow የሆነ ብሎት እንደሚረዳው አምናለሁና አሳሳቢነቱ ይህን ያህል ሆኖ አልታየኝም::

ጎበዝ ይህ ሁሉ የህገራችን ፖለቲካዊ ችግር የተፈጠረው ትናንትን መሰረት ባደረገና በጅምላ ፍረጃ የተፈጠረብን መሆኑን እያየን ዛሬም በእኛ ዘመን ይህንን ኃላቀርና ፊውዳላዊ የሆነን ህዝብን በጅምላ የመፈረጅ አመለካክትን ልናስተጋባ ይገባልን??

እኛ ዲጂታል ነን!!!
ዲጂታልነት የሚገባው ይገበዋል- ጅምላነትን አናምንም!!!

1 Comment

  1. ስንት ቁም ነገር ያለዉ ጽሁፍ ተጽፎ ተራ ሲጠብቅ ያንተን እንዴት እንዳወጡልህ ማሰብ ይከብዳል። ህወአት የአማራ ህዝብ ያለዉ እንደ አረጋዊ በርሄና የጥልያን አገልጋይ ልጆች በነጻነት ትግሉ ላይ የአማራዉን ከፍተኛ ተጋድሎ አባቶቻቸዉ ስለነገሯቸዉ ተሸማቅቆ መኖር ስላሳፈራቸዉና አባቶቻቸዉ ከጥልያን ጋር የፈጠሩላቸዉ ትስስር ክፍተ በመሆኑ ከዛ በሚያገኙት ምክር ነዉ።
    አቶ ሲሳይ ግን ጥፍራቸዉ የተነቀለባቸዉን፤ በጅምላ የተገደሉትን የኢትዮጵያ ወጣቶች በአይናቸዉ ስላዩ፤አጋቸዉ በነዚህ እርኩሶች ተገንጥሎ የባህር በራችን በመዘጋቱ፤ የኢትዮጵያ ንብረት ተዘርፎ ለትግሬ በመከፋፈሉ፤ባህላችን ያልሆነ አስነዋሪ ነገር ልጆቻቸዉ ስላመጡብንና ብንጽፈዉ የማያልቅ በደል ስለ ተፈጸመብን ነዉ። ምኑን ምኑን አገናኝተኸዉ ነዉ የአረጋዊን አባባል ከአቶ ሲሳይ አባባል ጋር ልታዛምደዉ የሞከረከዉ? አንዳንድ ቦታ ስምህን አየዋለሁ ብእርህ ከደረቀ እረፍት አድርገህ ሀሳብ አሰባስብ ያለበለዚያ ሃሳብ ያልሆነ ሀሳብ ወደ ድር ጥንጥኑ አትላክ። ወይ ጽሁፍህን ወደ ትግራይ ኦን ላየን ላከዉ ምንም አይሰጡህም ግን በርታ ማለታቸዉ አይቀርም።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.