ግልፅ ደብዳቤ፡ ለክቡር የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፤ ዶክተር አብይ አህመድ

1 min read

ክቡር ጠቅላይ ሚኒሰተር ፤

እንደሚታወቀው ግብፅ በአባይ ጉዳይ ላይ የማይታይ እና የሚታይ ደባ ስትፈፅም እና ስታስፈፅም ቆይታለች፡፡ ይህም ሃገራችን ኢትዮጵያን ከሰላሟ እና ከልማቷ ሲያስተጓጉላት በርካታ ዘመናት ተቆጥረዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም በ2011 ሀዳሴ ግድብ ግንባታ ማስጀመሩን ተከትሎ ግብፅ ወደ ቆየችበት እኩይ ተግባሯ ማለትም ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ የውክልና ጦርነቶች በሃገራችን ላይ ማካሄዷን አጠናክራ ቀጥላለች፡፡ የኢትዮጵያ
የድርድር ቡድንም ጉዳዩ መልክ ይዞ ከስምምነት ላይ ለመድረስ የተቻለውን እያደረገ መሆኑንም እገነዘባለሁ፡፡

በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያን እና የግብፅን ወቅታዊ አቋምም ከሰማኋቸው በርካታ መግለጫዎች እና ቃለ-መጠይቆች ከሞላ-ጎደል ለማወቅ ችያለሁ፡፡ በኔ ግንዛቤም ኢትዮጵያ ድርድሩ የውሃ ሙሌትን እና እና አለቃቀቅን ብቻ የተመለከተ ብቻ እንዲሆን እና ሙሌቱም በ7 አመታት ጊዜ ውስጥ እንዲከናወን አቋም መያዟን እንዲሁም ግብፅ ሙሌቱ 20 አመታትን ፈጅቶ እንዲከናወን እና “ ከድርሻዋም “ እንዲጎድልባት እንደማትፈቅድ እና የአስዋን ግድብ ይዞታም በስምምነቱ እንዲካተት እንደምትፈልግ ተረድቻለሁ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ዲፕሎማቲከ ቁመና ከግብፅ የተሻለ ስለመሆኑ በርካታ የመንግስት ባለስልጣናት ሲገለፅ እና የግብፅን ዲፕሎማሲያዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ወቅታዊ ቁመና ሲያቃልሉ አድምጫለሁ፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ህዝቡም ይህንኑ የሚያንፀባርቅ ስነልቦና አዳብሯል፡፡ ሆኖም እውነታውን ልብ ላለ ወቅታዊው የግብፅ ቁመና የሚናቅ እና ቸል የሚባል አይደለም፡፡ ኢትዮጵያም ከዋሽንግተኑ ድርድር የወጣችበት ምክንያት ዲፕሎማሲያዊ ከመሆኑ ባሻገር በሃገር ውስጥ ከህዝቡ ጋር በቂ ምክክር አድርጎ ህዝቡ የሚደግፈውን ሁነኛ አቋም ለመያዝ በሚል እንደመሆኑ ይኽው የሚጠበቅ ሁኖ ሳለ ኢትዮጵያየተጀመረውን የውሃ ሙሌት ድርድር የተወሰኑ አንቀፆችን በማሻሻል ለግብፅ እና ሱዳን በድጋሚ አቅርባለች፡፡ ሆኖም አሁን እየተሄደበት ያለውን የድርድር መስመር በግብፅ የተቃኘ ወጥመድ በመሆኑ እና ለኢትዮጵያ ሁነኛ መፍትሄ የማያመጣ በመሆኑ እኔም እንደ አንድ ዜጋ ለጉዳዩ የተሻለ የመፍትሄ ሃሳብ ነው የምለውን ምክረ-ሃሳብ እንዳቀርብ ምክንያት ሁኖኛል፡፡ .>>>[ሙሉውን ደብዳቤ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]  >>>

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.