የስዬ አብርሃ ነገር – ሳሙኤል ምናሴ

1 min read

ይህን ጽሁፍ እንድጽፍ የገፋፋኝ ሰሞኑን ስዬ አብርሃ ወያኔ በሚያስተዳድራቸው የመገናኛ ብዙሃን “ያዙኝ ልቀቁኝ” እያለ ዕብደት መጀመሩን ስሰማ ስለገረመኝ ነው። ስዬ ማለት ሽንፍላ ነው። ሽንፍላ ምንም ቢያጥቡት አይጠራም። ስዬም ያው ነው። ስዬ መልካም ያልሆኑ ብዙ መገለጫዎች ያሉት አሳዛኝ ፍጥረት ነው። ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ኢትዮጵያ ላጋጠማት ፈተና ከሚጠየቁ ሰዎች መካከል በመጀመሪያው ረድፍ ከሚሰለፉ ወንጀለኞች አንዱ ነው። ስዬ ዕብሪተኛም ነው። ዕብሪተኛ መሆኑን በምሳሌ ላስረዳ። የደርግ መንግሥት ወድቆ የሽግግር መንግሥቱ መከላከያ ምንስትር በነበረት ጊዜ “ጦርነት መስራት እንችልበታለን” በሚለው ዕብሪተኛ ንግግሩ ይታወቃል። እርግጥ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ ዳር ድንበሩንና ሉዓላዊነቱን ለማስከበር ጦርነት መስራት የሚችል ህዝብ መሆኑ ይታወቃል። ስዬ የተጠቀመበት አገላለጽ ግን እሱና መሰሎቹ ብቻ ጦርነት መስራት የሚችሉ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን ይህንን ማድረግ የማይችል “ደካማ” ወይም “ፈሪ” አድርጎ ለማሳየት ነበር። ለነገሩ አይፈረድበትም ምክንያቱም ስዬና መሰሎቹ የኢትዮጵያ ታሪክ ዕውቀታቸው የተንሸዋረረና የኢትዮጵያን ታሪክ በሚገባ አንብቦ ካለመረዳት የሚመነጭ ብዥታ ነው። መቼም ስዬ ከስህተቱ የሚማር አይደለም። ሰሞኑም ይሄው ዕብሪቱ አገርሽቶበት “ትግራይ የሚነሳው ጦርነት ተራ ጦርነት አይሆንም” እያለ ትግራይ ከመሸጉ ወንጀለኞች ጋር በመሰለፍና መከረኛውን የትግራይ ህዝብ እንደ ሰብዓዊ ጋሻ በመጠቀም ሊያስፈራራ ይሞክራል። እንደ ስዬ የመሳሰሉ በዘረፋ የተሰማሩ ወያኔዎች ከኢትዮጵያ ህዝብ የዘረፉትን ሃብት ለማስጠበቅ ሲሉ በትግራይ ህዝብ ስም መነገድ የሚያቆሙበት ቀን ቅርብ እንደሚሆን በትግራይ እየተፋፋመ ያለው አመጽ አመላካች ነው። መቼም ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ በ1990 ዓመተ ምህረት የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት በተቀሰቀሰበት ሰሞን የሻዕቢያ ሬዲዮ የወያኔን የውጊያ ብቃት አቅም በተመለከተ በተለይም ስለስዬ ፈሪነት አንድ ዘገባ ሰርቶ ነበር። እንደ የሻዕቢያ ሰዎች ከሆነ በትጥቅ ትግሉ ወቅት ሻዕብያና ወያኔ በጋራ ሆነው ከደርግ ጋር ውግያ ያካሂዳሉ። በውጊያው ደርግ የአውሮፕላን ድብደባ ያካሂዳል። በዚህ ወቅት ስዬ የሚመራውን ሰራዊት ጥሎ በመሸሽ አንድ ዋሻ ውስጥ ይገባል። እሱ የተደበቀበት ዋሻ እስካሁን ድረስ ሻዕቢያዎች “ምህባዕ ስዬ” ወይም “የስዬ መደበቂያ” እያሉ እንደሚጠሩት መዘገባቸውን አስታውሳለሁ። ለነገሩ በውግያ ወቅት ሰራዊትን ጥሎ በመሸሽ ረገድ የወያኔው ቀንደኛ መሪ መለስ ዜናዊም ተጠቃሽ ነው።

ስዬ ዕብሪተኛና ፈሪ ብቻ ሳይሆን ሙሰኛና ከሃዲም ነው። እንደሚታወቀው ስዬ ወያኔ ለሁለት ስትሰነጠቅ ከተሸናፊው ቡድን ነበር። ከተሸናፊው ቡድን ውስጥ በሙስና የታሰሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ። ስዬና ቢተው በላይ። ቢተው በደቡብ ህዝቦች ክልል የሞግዚት አስተዳዳሪ በነበረበት ጊዜ በፈጸመው ሙስና ነበር የታሰረው። ስዬ ደግሞ ራሱን ጨምሮ

ወንድሞቹና እህቱ እሱ ባመቻቸው መንገድ ሙስና ውስጥ በመዘፋቃቸው ነበር። የአዲስ አበባ ህዝብ ስዬ ሲከሰስ ከስዬ ጎን የቆመው ስዬ ሙሰኛ ባለመሆኑ አልነበረም። ይልቁንስ ለወያኔ ከነበረው ጥላቻ በመነሳትና ህዝቡ መለስ ዜናዊና ቡድኑ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ይዘውት በነበረው አቋም ባለመደሰቱ ነበር። ከዚህ በተጨማሪ እነ ዳኛ ብርቱኳን ሚደቅሳ ባስቻሉት ችሎት ማስረጃዎች በደንብ ተደራጅተው ሳይቀርቡ ለነስዬ ቅርበት ያላቸው የትግራይ ካድሬዎችና የመከላከያ አባላት አመጽ ከመቀስቀሳቸው በፊት ስዬን በማሰር አጀንዳው በፍርድ ቤት ውሳኔ መዝጋት የነመለስ ፍላጎት ነበር። ስለስዬ መታሰር ጥያቄ ለሚያነሱ የወያኔ ካድሬዎችና የመከላከያ አባላት ስዬን ያሰረው ፍርድ ቤ እንጂ እኛ አይደለንም። የፍርድ ቤትን ውሳኔ እኛ ማስቀየር አንችልም። ይህንን ብናደርግ ህገ መንግስቱንም መጣስ ነው የሚሆነው በሚል ጉዳዩን መዝጋት ነበር። ሆኖም በተጣደፈው የነ መለስ እርምጃ ምክንያት ለጊዜውም ቢሆን ነገሩን በውል ያልተገነዘቡ ሰዎች ስዬ ሙስና ያልፈጸመና የፖለቲካ እስረኛ አድርገው እንዲያዩት አድርጓል። ከነዳኛ ብርቱኳን ሚደቅሳ በኋላ የተሰየመው ችሎት ግን ዓቃቤ ህግ ማስረጃዎቹን ለማሰባሰብ ጊዜ በማግኘቱ ስዬም ሆነ ዘመዶቹ በህጉ መሰረት ተፈርዶባቸው ቅጣታቸውን ፈጽመው መውጣታቸው ይታወቃል። የስዬን ሙሰኝነት ለማረጋገጥ የተምቤንን ህዝብ ብቻ መጠየቅ በቂ ነው። ምንም ሃብት ያልነበራቸው የስዬ ወንድሞችና እህት በሃገሪቱ አሉ ከሚባሉ ባለሃብቶች ተርታ ለመሰለፍ በቅተዋል።

ከዚሁ ከፍርድ ቤት ጉዳይ ሳንወጣ ከላይ እንደጠቀስኩት እነ ዳኛ ብርቱኳን በወቅቱ ዓቃቤ ህግ ጥድፊያ ላይ ስለነበር በስዬ ላይ የተማሏ ሰነድ ባለማቅረቡ የመሃል ዳኛ ብርቱኳን ሚደቅሳና የግራና የቀኝ ዳኛ የነበሩት ጎሽይራድ ጸጋውና አዳነ (የአባቱን ስም አሁን የዘነጋሁት የትግራይ ተወላጅ) ስዬን በነጻ አሰናብተዉታል። እነዚህ ዳኞች ባስተላለፉት ወሳኔ በወቅቱ የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ሰብሳቢ በነበረው በረከት ስምዖን መሪነት በተደረገ ግምገማ በስዬ ምክንያት በረከት ከላይ የተጠቀሱትን ዳኞች “አቅሙን የማያውቅ ዳኛ” ብሎ እንደዘለፋቸው በሚገባ የሚታወቅ ነው። የአዳነን ሁኔታ ባላውቅም ብርቱኳን የደረሰባት እስርና መከራ የሚታወቅ ነው። ዳኛ ጎሽይራድ ጸጋው የደረሰበት መከራ ግን ብዙ ኢትዮጵያውያን በውሉ ያወቁት አልመሰለኝም። ጎሽይራድ ጸጋውና አዳነ ከመጀመሪያው ዕለት ጀምሮ የቀኝና የግራ ዳኞች በመሆን የስዬን ክስ ሲመለከቱ የነበሩ ዳኞች ናቸው። ጎሽይራድ የበረከት ስምዖን ተግሳጽና ዘለፋ ከሰማ ጀምሮ ወያኔ እንደልቡ በሚዘውረውና ነጻ ሆኖ ስራውን መስራት በማይችልበት ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኖ ላለመቀጠል የወሰነው ወዲያውኑ ነበር። ጎሽይራድ መልቀቂያ ጠይቆ ከዳኝነት ከተሰናበተ በኋላ የጥብቅና ቢሮ ከፍቶ ለጥቂት ቀናት እንደሰራ፤ እሱም እንደ ብርቱኳን ሚደቅሳ በነበረከት ስምዖን ትዕዛዝ ባልዋለበትና በልተሳተፈበት ከነ ብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ ጋር በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተሳትፈሃል በሚል ሰበብ ለ9 ዓመታት ታስሮ የካቲት 15 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ከእስር ተፈቷል። ስዬ ከሃዲ ነው የምለው ትላንት ህገ መንግስቱንና ህጉን የጣሱ ናቸው ይላቸው ከነበሩ ወያኔዎች ጋር ተሰልፎ በስንት መስዋዕትነት የመጣውን ለውጥ ለመቀልበስ የመቶ ሜትር ሯጮች በሚንደረደሩበት ፍጥነት በአፍጢሙ ሊደፋ እየተውተረተረ ያለውን ፋሽት ወያኔን ለመታደግ ደፋ

ቀና ሲል ማየት ለካስ አንዳንድ ሰው ሂሊና የሚባል አልፈጠረለትም ያስብላል። ስለዚህ ስዬ የካደው ፍትህ እንዲከበር የታገሉ የፍትህ አካላትን ብቻ ሳይሆን በችግሩ ወቅት ከጎኑ የተሰለፈው የአዲስ አበባና መላው የኢትዮጵያ ህዝብን ጭምር ነው። እነ ብርትኳንና ባልደረቦቿ ከስዬ ሙገሳ ወይም ትሩፋት ለማግኘት ሳይሆን ለሙያቸውና ለህሊናቸው ያደሩ ሰዎች ስለሆኑ በህጉ መሠረት ብይን ሰጥተዋል። ስለስዬ አቋም መዋዥቅ ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ሰሞኑን ስንወያይ “ስዬም እንደ በቀለ ገርባ ወያኔ ምንም የፈጸምው በደል የለም ብሎ ነገ ሊመጣ ይችላል” ያለኝን ነገር እኔም እስማማበታለሁ። ስዬ በታሰረበት ጊዜ እስር ቤት ውስጥ ብዙ ኦሮምኛ ተናጋሪዎች ግርፋት እንደሚፈጸምባቸውና እሱ ማዕከላዊ ታስሮ በገባበት ሰሞን በአንዱ ሌሊት ግርፋት የተፈጸመበት የኦሮሚኛ ተናጋሪ ሲቃ እንደሰማ መግለጹን አስታውሳለሁ። አላልኩም ብሎ እንደማይመጣ ተስፋ አደርጋለሁ።

ስዬ ትግራይ ከመሸጉት ወንጀለኞች ጋር ግንባር የፈጠረበት ምክንያት ነገሩ ወዲህ ነው። ስዬ ለራሱ ያለው ግምት በጣም የተሳሳተና የተጋነነ ነው። ራሱን የተዋጣለት የጦር መሪና በሳል ፖለቲከኛ አድርጎ ያምናል። በሙስና ምክንያት ታስሮ ከወጣ በኋላ የኢትዮጵያን ህዝብ ቀልብ ለመሳብና ድጋፍ ለማግኘት የሚባክንበት ጊዜ ነበር። በውቅቱም አንድነት ፓርቲን በመቀላቀል በሃገር ውስጥና በአሜሪካ ያለውን የአንድነት ኃይል ልብ እማርካለሁ የሚል ቅዝት ነበረው። ይህ አካሄዱ ግን ብዙም ፍሬ ሊያፈራ ስላልቻለ ሌላ አዋጪ ገበያ መፈለግ ጀመረ። ከፓርቲው ለምን እንደወጣ ሳይነግረን እዚያው በሄደበት አሜሪካ የትምህርት እድል አገኘ። ከትምህርት በኋላም በተባበሩት መንግስታት ስር በምዕራብ አፍሪካዊቷ ላይቤሪያ አማካሪ ሆኖ በመስራት እንደነበር አውቃለሁ።አሁን ያለበትን ሁኔታ አላውቅም።

እንደሚታወቀው የጠቅላይ ምንስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ መንግሥት ወደ ስልጣን ሲመጣ ከውጭ የነበሩ ተቃዋሚዎችም ሆኑ ወያኔን ሲታገሉ የነበሩ ሰዎች ወደ ሃገር ውስጥ ገብተዋል። ለአንዳንዶችም የመንግሥት ባለሥልጣናት ኤርፖርት ድረስ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል። ስዬ የጠበቀውም እንደነ ዶ/ር አረጋዊ በርሀና ግደይ ዘርዓ ጽዮን መንግሥት ጥሪ እንዲያደርግለትና በአጀብ እንዲቀበለው ብሎም “ ስዬ እባክህን ናና አማክረን” እንዲለው ነበር የጠበቀው። ስዬ የዶ/ር ዓብይ መንግሥት ጥሪ ከነገ ዛሬ ይመጣል ብሎ በተሰፋ ቢጠብቅም ጥሪው የውሃ ሽታ ሆኖ ቀረ። በነአረጋዊና ግደይ የቤተ መንግሥት እንግዳኝነትም አንጀቱ አረረ። ምክንያቱም አረጋዊና ግደይ ከህወሃት መሪነት እንዲነሱና ከትግራይ ለቀው እንዲወጡ ከመለስ ዜናው ጋር ሆነ ሲያሴር እንደነበር ስለህወሃት የተጸፉ መጻህፍት ማየት ነው። አረጋዊ የወያኔ ወታደራዊ ክንፍ ኃላፊ በነበረት ጊዜ ስዬ ምክትሉ ነበር። ስዬ የአረጋዊን ቦታ ለመያዝ ሲቋምጥ መለስ ደግሞ ከአረጋዊና ከግደይ በኩል ይነሳ በነበረ የርዕዮተ ዓለም ልዩነት ደስተኛ አልነበረም ሳይሆን ሊያጠፋቸው ቆርጦ የተነሳበት ወቅት ነበር። መለስ የስዬን ፍላጎት ጠንቅቆ ያውቅ ስለነበር ለጋራ የስልጣን መደላድል ሲሉ መለስና ስዬ ግንባር ፈጥረው አረጋዊንና

ግደይን ከፈጠርዋት ህወሃት እስከነአካቴው አሰናበቱዋቸው። ስዬ ሲባንን አዲስ አበባ ላይ አረጋዊና ግደይ ቤተ መንግሥት ሲወጡና ሲገቡ የድሮ አሳሪዎቹ ደግሞ መቀሌ ሆቴል ውስጥ ተከርቸም ገብተው አገኛቸው። ጻድቃን ገብረትንሳኤና አበበ ተክለ ሃይማኖት የስዬ ወዳጆች መሆናቸው ይታወቃል። ሁለቱ የወያኔ ጄኔራሎች ህወሃት ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ጻድቃን ከመለስና ከስዬ ጋር ተለጥፎ የሚኖር በራሱ የማይተማመን ሰው ነበር። አበበ ደግሞ በጻድቃን በኩል ተንጠላጥሎ የመለስና የስዬ አሸርጋጅ እንደነበር ማንም ታጋይ የሚያውቀው ነው። ጻድቃንና አበበ ሁለቱም ራሳቸውን ችለው የሚቆሙ ሰዎች አይደሉም። ከሥልጣን ከተባረሩ ጀምሮ እስከ ህልፈተ መለስ ዜናዊ ድረስ አንድም ቀን ትንፍሽ ብለው የማያውቁ ቦቅቧቋዎች ናቸው። መቀሌ የመሸገው ወንጀለኛው ቡድን በጻድቃንና በአበበ በኩል አድርጎ ስዬ አብርሃን ወደነ ስብሃት ነጋ ካምፕ እንዲመጣ አድርጓል። በወያኔ ስሌት እነ ስዬን የመሳሰሉ አኩራፊዎች በማሰባሰብ ሌላውን የትግራይ ወጣትና ሊሂቅ በዙሪያችን አሰባስበን የመጣብንን የለውጥ ማዕበል እንቀለብሳለን ነው። ለውጡን መቀልበስ የሚለው የሌሊት ቅዥት ቢሆንም የስዬ ውሳኔ ግን አንድ የአእምሮ መታወክ ያለበት ሰው ድንገት ተነስቶ እየተንቀለቀለ ካለ እሳት በደመ ነብስ ዘሎ እንደገባ ዓይነት ሆኖ ይሰማኛል።

 

2 Comments

  1. Seye does not belong to the core of the TPLF thugs since he is not from Adwa, Shire and Axum areas of Tigray. The TPLF thugs who are in charge are mainly from Adwa and have family interconnections.
    When Seye ran as a candidate for the Andinet party in Tigray, the TPLF thugs accused him of treason and siding with the sworn in enemies of the Tigray people, the Amharas. Seye himself is anti-Amhara
    like any othe high profile TPLF and fascist Tigray ethno-nationalist figures but this accusation of joining the enemies of Tiray (the Amharas) was tactical and is a typical TPLF deception.

  2. The former board chairman of Ethiopian Airlines Seye Abraha need to be held accountable for the crimes he committed at Ethiopian Airlines after Seye ABRAHA brought ethnic politics inside Ethiopian Airlines’s workforce.

    የአየር መንገዱ የጣሪያ ስር ጉድ!
    ክፍል 1 , ክፍል 2 & ክፍል 3

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.