እኔና ጥቁርነት በሚኒያፖሊስ አሜሪካ – በሱራፌል ወንድሙ

1 min read

ለስድስት ዓመታት የተማርኩባት ሚኒያፖሊስ ከተማ እሳት ፈጥራለች። እሳት ሆናለች። ወላፈኑ በመላ አሜሪካ ተሰራጭቱዋል። በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ። በጥቁሩ ጆርጅ ፍሎይድ አሰቃቂ ሞት። በነጩ ፖሊስ የማን አለብኝ ገዳይነት።

ነጩ ፖሊስ የጥቁሩ ጆርጅ አንገት ላይ ተንደላቆ የተንበረከከበት፥ ጆርጅ “ኧረ የትንፋሽ ያለህ! ኧረ በናትህ መሞቴ ነው! ኧረ ገደልከኝ” እያለ እስከሞት የተድፈጠፈጠበት ጎዳና እኔ በተለይ በመጨረሻዎቹ የሚኒያፖሊስ ዓመታቴ እኖርበት በነበረው ሰፈር አቅራቢያ ነው የሚገኘው። ቀጥሎም የተቀጣጠለው ዓመፅ አካባቢውን አጥለቅልቆታል።

ጆርጅ አንድ ሰው አይደለም። የጆርጅ ሞት የአያሌ ጥቁሮችን፥ የአያሌ ገፀ ብዙ ግፉአንን ይወክላል። በአሜሪካ የጥቁሮች ደም ደመ ከልብ ነው። በጥቁሮችና አሜሪካን ህንዶች እንዲሁም በተለያዩ ስደተኞች የተገነባችው አሜሪካ፤ ስደተኝነታቸውን በረሱና ሚሊዮኖችን ባፈናቀሉ፥ በባርነት በቀጠቀጡ የነጭ ስርዓት ፈጣሪዎች ፀፀትን የመደበቅና የስግብግቡን የካፒታሊዝም ስርዓት የመጠበቅ አባዜ ሃጢያቷን በፍትህ ከማጠብ ይልቅ በበለጠ ደም እያጨማለቀች መጓዝን መርጣለች። ደሞ የነፃነት ስብከቷ ይባስ።

እናም በጆርጅ ላይ የተፈፀመው ግድያ አስደንጋጭ ቢሆንም፥ ድንገት ደራሽ አይደለም። ስርዓታዊ ነው። የነጩ ፖሊስ ዘግናኝ ኢፍትሃዊነትም የሱና የግብረ አበሮቹ ብቻ አይደለም። ስርዓታዊ ነው። ችግሩም መልሱም ውስብስብ ነው ማለት ነው። መፍትሄውም የሁሉ ነገር መፍቻ እኔ ነኝ ከሚለው የሊበራል ምርጫ (ኢሌክሽን) እና ነፃ ገበያ ተብዬ (ሶ ኮልድ ፍሪ ማርኬት) ባሻገር ስርዓታዊና ተቁዋማዊ ብሎም እለታዊ ፍትህን ማስፈንን ይጠይቃል።

ጥቁር ነኝና ይሄ እጣ ፈንታ የኔም እንደሆነ አምናለሁ። ለዚያም ነው በሚኔሶታ የሚኒያፖሊስ ኑሮዬ ዘወትር በሰቀቀን እኖር የነበረው። ነጭ ፖሊስ የጥቁር ሰውነቴን፥ የጥቁር ህይወቴን እንዳይነጥቀኝ በስጋት ነበር የምኖረው። ስጋት የየዕለት የመንገድ ላይ አረማመድን ይቀይዳል። ወይም የተለየ ያደርገዋል። ዓይኔን ከሚያልፉ ፖሊሶች ዓይን ለመነጠል አደርግ የነበረው ጥረት፥ ጆሮዬን አለሁላችሁ በሚል ስም አለሁባችሁ እያለ መንፈስን ከሚበጠብጠው የፖሊስ መኪና ጩኸት እከልልበት የነበረው ጭንቅ፥ ፖሊሶች በአንድ በኩል ሲመጡ በዚያኛው መንገድ ተሻግሬ አሳብሬ እሄድ የነበረበት ጥብ መጥፎ ትዝታው አሁንም በሰውነቴ ውስጥ ተቀብሮ አለ።

እንደዚያም ሆኜ አልቀረልኝም። በወቅቱ የንጥቂያ ወንጀል ተሞክሮበት ነበር በተባለበት አካባቢ አለመኖሬ እየታወቀ የዪኒቨርሲቲ ኦፍ ሚኔሶታ ፖሊስ ከ”ወንጀል ሙከራው ክስተት” በሁዋላ የዚያን ዕለት ምሽት ወደ ዛንዚባር (ለወርክሾፕ) ጉዞ የሚያስፈልገኝን መድሃኒት ከዩኒቨርሲቲው ክሊኒክ ለመውሰድ ስሄድ በካሜራ የተነሳውን ምስሌን ‘ተጠርጣሪው’ ብሎ ስልሳ ሺህ ለሚሆኑት የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተነው። በዚያ የተነሳ ከጉዞዬ ተመለስኩ። ያን ባላደርግ ዓለም አቀፍ ተሳዳጅ (ፉጂቲቭ) ነበር የምሆነው።

የዩኒቨርሲቲው ፖሊስ ከሚኒያፖሊስ ፖሊስ ጋር በጥብቅ የሚሰራ ነበርና ከኤርፖርት ስመለስ የት ሄጄ ልደር? ስንቀሳቀስ የሚኒያፖሊስ ፖሊስ ቢይዘኝስ? እንዴት ነው የምሆነው? እጄን ምኑ ጋር ነው የማደርግላቸው? ዝም ብለው ቢተኩሱብኝስ? ቢያስሩኝስ? እስከፈለጉት ዘመን ዘብጥያቸው ቢወረውሩኝስ? በሚል መባተት ውስጥ ነበርሁ።

ያ ስጋት እጥፍ ድርብ ሆኖ የመጣው ምስሌ ከዩኒቨርሲቲው አልፎ በበነጋው በፎክስ ቴሌቪዥን አማካይነት ለመላው ሚኔሶታ ሲሰራጭ ነው። ብዙ ታሪክ አለፈና እኔም በወዳጅ ዘመዶቼ፥ በጥቂት ቀናኢ መምህራኔ ያንን ክፉ አጋጣሚም፥ ዘመንም አለፍኩ። መጥፎ ትዝታውና የዛሬው ዓለም አቀፋዊ የዘረኝነት ስጋት አልፎ ባያልፍም።

ሆኖም የኔ ጥቁርነት የራሱ ዳራም አለው። የጥቁር አሜሪካኖቹም የተለየ ነው። ጥቁር አሜሪካዊ መሆን ዘለዓለም እንዲህ ባለ ስጋት ውስጥ መኖር ብቻ ሳይሆን፥ እነሱም ነጮቹም በሚጋሩት ከባሪያው ስርዓት እስከአሁኑ ኒዮሊበራል ኦርደር ድረስ በዘለቀው የማይፈታ ቅራኔ ምክንያት ሰውነታቸው በነጭ ፖሊስ የትም የሚቀጠቀጥ፥ የሚገደልና የሚጣል እንደሆነ አለ።

ጥቁር አሜሪካውያን ለዘመናት እንደተጨቆኑ፥ ለዘመናት እንደታገሉ አሉ። የነሱ ትግል ለብዙዎች ትሩፋትን ሰጥቶአል። ለኢትዮጵያውያን ጭምር። ጥቁሮች ስል የቆዳ ቀለማቸውን በመያዝ ብቻ ሳይሆን በቆዳ ቀለማቸው ምክንያት ከነጭ ጥቅማ ጥቅም ዓለም የተገለሉትን ቡኒና ቢጫ የሚባሉትንም ህዝቦች ሁሉ እንደማስብ ልብ በሉልኝ። እነዚህ ህዝቦች በተናጥልም በቅንጅትም እየታገሉ አሉ። ነገር ግን አገዛዙ ረቂቅ ነውና እራሱን ራቅ እያደረገ በተበዳዮቹ መካከል መርዝ እየረጨ እነሱን እያናጨ ህልውናውን ያስቀጥላል።

በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ አይነት ናቸውና ሁሉንም በአንድ ከረጢት ውስጥ መክተት ተገቢ አይደለም። እናም ገና ከ 1920ዎቹና 30ዎቹ አንስቶ ከተደረገው ፀረ ቅኝ አገዛዝና ፀረ ፋሽስት ትግል አንስቶ ኢትዮጵያውያንና ጥቁር አሜሪካውያን በትብብር ሰርተዋል። ጥቁር አሜሪካውያን ለኢትዮጵያ ለመዝመት ሰልፍ ይዘው ተመዝግበዋል፥ የህክምና እና ሌሎች ለጦርነቱ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ከመላ ሰሜን አሜሪካ ጥቁሮች አሰባስበው ለግሰዋል፥ ጥቂት ተዋጊዎችንም ልከዋል። ከዚያም በብላክ ፓንተር የነፃነት ንቅናቄና የሲቪል መብት ንቅናቄ ወቅት ኢትዮጵያውያን ከጥቁር አሜሪካውያን ጋር ሰርተዋል። አሁንም በተለይ ሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በማንነት ምስረታቸውም የተነሳ ከጥቁር አሜሪካውያን ጋር እንደ ኢትዮጵያዊ ጥቁር አሜሪካውያን አብረው ለነፃነት እየታገሉ ያሉ ብዙዎች ናቸው።

ሆኖም ግን ብዙዎች ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ምክንያቶች ውስብስብ የሆነውን የሃገሬው አሜሪካ ህንዳውያን፥ ጥቁር አሜሪካውያንና ሂስፓኒክ ህዝቦችን የታሪክና የኑሮ ሁኔታ (ጥቁሮችን እርስ በራሳቸው ለመከፋፈልና ለማባላት ሆን ተብሎ የሚሸረበውን ሴራ) ባለመረዳት ወደ መፍረድና ወደመናቅ መሄድ ይስተዋልባቸዋል። ከዚህም ባሻገር ሙሉ የአሜሪካ ዜግነት ተቀብለው ህይወታቸውን በአሜሪካ ለመኖር የወሰኑ ኢትዮጵያውያን የእነሱንም ሆነ የልጆቻቸውን ህይወት ሲያስጨንቅና ሲቀጥፍ ሊኖር ስለሚችለው ዘረኝነት በአደባባይ ሲናገሩ አለመታየታቸው ነገሩን ፍርጃም ባይሆን ውይይት ሊቀሰቅስ የሚገባው ጉዳይ ያደርገዋል።

ሞት ለዘረኝነት!

ሱራፌል ወንድሙ

3 Comments

 1. Since Ethiopia started fighting the proxy war in Somalia most Ethiopians considered themselves as the white police officers killing blacks in Africa . They forgot they are blacks since Ethiopians were given the status of a goon and a house negro by the white man. When I say white it means White Arabs and the West because Ethiopian ladies were house negroes for the white Arab and Ethiopian males were goons for the White man killing blacks in Somalia. Ethiopians in USA considered themselves as the chosen blacks (gooons and house negroes) who are given better status than the other blacks, their assumptions are quickly starting to change now because many Ethiopians in the white world are loosing their incomes in these times of CoronaVirus and are unable to find government welfare assistances or jobs generating enough incomes which they can survive on as the other non habesha black people are easily finding.

  Look how quickly with no hesitation the government of Ethiopia agreed to white house’s demands on the Abay issue. At the time Ethiopia handled the Abay negotiation in Washington DC in a manner as if it was another proxy war meeting with Ethiopia representing the police of Africa nation participating in a meeting to recieve orders from the police of the world to obey the orders given by the police of the world (USA) , because according to this proxy war fighting EPRDFites they thought whatever the police of the world (USA) says was supposed to be obeyed by Ethiopia or Ethiopia will risk the status of being the police of Africa.

  Amongst the Ethiopian community in USA I noticed that most Ethiopians live their lives in denial about the fact that they are living in USA , they consider themselves as migrant workers or tourists on welfare visiting USA who are temporarily in USA , rather than actual residents of USA.

  Very few take the initiative to engage themselves actively in this type of issues , which is really not a good idea because especially now with the growing anti immigrant sentiments in USA , not involving in such issues is such a bad idea because it proves that immigrants do not care about what happens to vulnerable societies in USA or they donot care what happens to the people in USA which can get voters to vote against DV lottery and against other aids that goes to Ethiopia, keep in mind Ethiopia had been the second largest aid recipients from USA for decades until the Trump administration got to office . Now it is the European nation’s that are the highest getting aids from USA even Ethiopia tried to make the Trump administration change the amount of aid Ethiopia receives by sitting to negotiate about Abay in Washington DC then when negotiation hit a dead end PM Abiy Ahmed asked for debt cancellation.

  Freedom for Sidama !!

  Freedom for all blacks from goons !!

 2. Since Ethiopia started fighting the proxy war in Somalia most of the elte Ethiopians considered themselves as the white police officers killing blacks in Africa . They forgot they are blacks since Ethiopians were given the status of a goon and a house negro by the white man. When I say white it means both the White Arabs and the West because Ethiopian ladies were house negroes for the white Arab and Ethiopian males were goons for the White man killing blacks in Ethiopia , Somalia…

  Ethiopians in USA considered themselves as the chosen blacks (gooons and house negroes) who are given better status than the other blacks, their assumptions are quickly starting to change now because many Ethiopians in the white world are loosing their incomes in these times of CoronaVirus and are unable to find government welfare assistances or jobs generating enough incomes which they can survive on as the other non habesha black people are easily finding jobs or government assistance in the WHITE WORLD (Arab or in the west.)

  Look how quickly with no hesitation the government of Ethiopia agreed to white house’s demands in Washington DC on the Abay issue few months back. At the time Ethiopia handled the Abay negotiation in Washington DC in a manner as if it was another proxy war meeting with Ethiopia representing the police of Africa nation participating in a meeting to recieve orders from the police of the world to obey the orders given by the police of the world (USA) , because according to this proxy war fighting EPRDFites they thought whatever the police of the world (USA) says was supposed to be obeyed by Ethiopia or Ethiopia will risk the status of being the police of Africa.

  Amongst the Ethiopian community in USA I noticed that most Ethiopians live their lives in denial about the fact that they are living in USA , they consider themselves as migrant workers or tourists on welfare visiting USA who are temporarily in USA , rather than actual residents of USA.

  Very few take the initiative to engage themselves actively in this type of issues , which is really not a good idea because especially now with the growing anti immigrant sentiments in USA , not involving in such issues is such a bad idea because it proves that immigrants do not care about what happens to vulnerable societies in USA or they donot care what happens to the people in USA which can get voters to vote against DV lottery and against other aids that goes to Ethiopia, keep in mind Ethiopia had been the second largest aid recipients from USA for decades until the Trump administration got to office . Now it is the European nation’s that are the highest getting aids from USA even Ethiopia tried to make the Trump administration change the amount of aid Ethiopia receives by sitting to negotiate about Abay in Washington DC , then when negotiation hit a dead end PM Abiy Ahmed asked for debt cancellations !!!

 3. Who are these morons commentating above? Meaningless garbage! The article is written in Amharic not in the English language. Write in Amharic! To simply post and re-post unrelated gibberish refuse can only come from a mind that is untamed and skewed with the daily wind.

  ወዳጄ ሱራፌል ወንድሙ – ችግሩ ያለው በዓለም ዙሪያ ነው። ነጩ ዓለም ራሱን ከፈጣሪ ጋር አወዳድሮ በቆዳው ቀለም ብቻ እኔን ስሙ ማለቱን ታሪክ ያሳየናል። ዛሬ ያለቅጥ የሚደነፋው የአሜሪካ ፕሬዚደንት አሜሪካን አሜሪካ ያደረጉት መጤዎች እንደሆኑና እሱም ከዚያው ዝርያ እንደመነጨ አይረዳም። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ አሜሪካና ራሺያ የተቀራመቱት የጀርመንን መሬት አይደለም። የጀርመን ሳይንቲስቶችን እንጂ። እንዲያ ባይሆን ኑሮ በምድርም ሆነ በጠፈር ዛሬ ያሉበት ነገር ላይ ሊደርሱ ባልቻሉም ነበር። በአንድ የትምህርት ተቋም ላይ እኔ የደረሰብኝን አንድ ነገር ላካፍል። የኬሚስትሪ ሌክቸር አልቆ ወደ ላቦራቶሪ ከመግባታችን በፊት ከረዳት መምህሯ ጋር የምናረገው ነገር በመኖሩ አንዲት ጠበብ ወዳለች ክፍል ገብተን የእርሷን መግባት እንጠባበቃለን። ሜሪም ገባችና በአይኗ ሁሉን ካየች በህዋላ እኔን (Are you sure you are in the right class) በማለት ጥያቄ መሰል ነገር ከማጣጣል እይታ ጋር አቀረበችልኝ። እኔም አዎ በማለት ነገሩን አሳልፌ ከዚያ በህዋላ ተከባብረን የትምህርት ጊዜው አለቀና ውጤት ሲመጣ እንዲህ አይነት የጥቁር ተማሪ ያለ አይመስለኝም ነበር በማለት መናገሯን የክፍል ጓደኞቼ እስከዛሬ ያወሩታል። ጥቁሩ ተማሪ እኔ ብቻ ነበርኩ በዚያ ጊዜ! ጥቁሩ ህዝብ ራሱን ካላከበረ ሌላው ሊያከብረው አይችልም። በአፍሪቃ፤ በእስያ፤ በአረብ ሃገር ጥቁር ህዝብ ከጫካ እንደ ወጣ እንስሳ እንደሚያሳድድቱ አይኔ አይቷል። ይህ ሲባል የእኛ የማጭበርበር፤ ለህግ ያለማደር፤ እርስ በርስ መገዳደል የለም እያልኩ አይደለም።
  Black Like Me by John Howard Griffin ላነበበና የJames Baldwin ስራዎች አገላብጦ ላየ የጥቁር መከራ ትላንት የመነጨ ሳይሆን ታሪክ ጋር የነበረ ዛሬም ያለ ነው። አሁን በአሜሪካ ገንፍሎ የምናየው ጉዳይ የልጁ ሞት መነሻ ይሁን እንጂ የብዙ በደሎች ክምር ውጤት ነው። በሥራ ቦታ፤ በቤት (በሰፈር)፤ በባንክ፤ በትምህርት ቤት፤ በእለት ተእለት የኑሮ ጉዳይ በጥቁሮች ላይ የሚደረገው ተጽኖ ሰማይ ጠቀስ ነው። ታዲያ የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች እንዲሉ ነው እንጂ የእኛስ ሃገር እዚህ ከሚደርሰው ግፍና መከራ እኛው በእኛው ላይ እናደርስ የለም። በወያኔ ጊዜ የተሰራው ግፍ አሁን ደግሞ መልኩን ቀይሮ ህዝባችንን እያጫረሰው አይደለንም? እሳት የሚያቀብሉን አረቦችና ነጩ ዓለም አሁን ደግሞ አፍሪቃን የቅኝ ግዛቷ አርጋ የያዘቸው ቻይና በጥቁር ላይ ያላቸው ጥላቻ ከምድር ላይ ንሮ ሰማይ ነክቷል። ግን ማን ሰሚ አለ? ውንድምና እህቱን ገድሎ በሚፎክር የፓለቲካ ከብት መካከል ዓለማዊ እይታ ለጥቁሮች ህዝብ አንድነትና ነጻነት መታገል ስፍራ የለውም። ሁሌ የመንደርና የጎጥ ጫወታ። እንደ ልጆች ያደረ እንጀራ ቁርስርስ ጫዋታ ፍርስርስ። ብዙ ጉድ አለ። ግን ጊዜና ወረቀት አይበቃም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.