ለአንድ ተንቀሳቃሽ ስልክ 94 ሺህ ብር፤ ለአንድ ላፕቶፕ 152 ሺህ ብር ወጪ ሆኗል – የፌዴራል ዋና ኦዲተር

1 min read

በኦዲት ግኝት እንዲመለስ ከተጠየቀው 798 ሚሊዮን ብር የተመለሰው 124 ሚሊዮን ብቻ ነው
****************************

ባለበጀት መስሪያ ቤቶች በ2010 በጀት ዓመት የኦዲት ግኝት ለመንግስት መመለስ ከነበረባቸው 798 ሚሊዮን ብር የተመለሰው ጥቂቱ ብቻ መሆኑን የፌዴራል ዋና ኦዲተር አስታወቀ።

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ባለበጀት መስሪያ ቤቶች በየዓመቱ የሚያስመዘግቡት የኦዲት ግኝት አሳሳቢነት አሁንም ቀጥሏል ይላል።

ዋና ኦዲተር ገመቹ ዱቢሶ ለኢዜአ እንደተናገሩት ባለበጀት መስሪያ ቤቶች በመንግስት ላይ ከፍተኛ የበጀት ብክነት እያስከተሉ ነው።

ዋና ኦዲተር የፋይናንስ ህጋዊነትና የክዋኔ ኦዲት በማድረግ የገንዘብ አያያዝን በሁለት መንገድ ይመረምራል ያሉት አቶ ገመቹ፤ ከገንዘብ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ለበርካታ ዓመታት ከፍተኛ የኦዲት ግኝቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

የኦዲት ግኝት ከሚታይባቸው መካከል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከትንሽ እስከ ትልቅ ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ዋናዎቹ ናቸው ነው ያሉት።

አቶ ገመቹ እንደ ማሳያ የጠቀሱት በመስሪያ ቤታቸው የ2011 ዓ.ም የኦዲት ግኝት በባለ በጀት መስሪያ ቤቶች አሳማኝ ባልሆነ መልኩ የተከፈለ 798 ሚሊዮን ብር ተመላሽ እንዲደረግ መወሰኑን ነው።

መስሪያ ቤቱ እንዲህ ቢልም ከዚህ ውስጥ ለመንግስት ተመላሽ የሆነው ከ124 ሚሊዮን ብር የማይበልጥ ነው ይላሉ።

ሁኔታው ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱን አመላካች እንደሆነም ነው ያብራሩት።

በቅርቡ ለከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የስልክና ላፕቶፕ ኮምፒውተር ግዢ በተጋነነ ዋጋ መፈጸሙ ይታወሳል።

ለአንድ ተንቀሳቃሽ ስልክ /ሞባይል/ 94 ሺህ ብር፤ ለአንድ ላፕቶፕ 152 ሺህ ብር ወጪ መደረጉን የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲም “ህገወጥ” ብሎታል።

አቶ ገመቹም ጉዳዩ በኦዲት ግኝትም የሚያስጠይቅና እርምጃ የሚያስወስድ መሆኑን ተናግረው፤ “አሁንም እርምጃ መወሰድ አለበት ብዬ ነው የምጠብቀው” ብለዋል።

በተመሳሳይ ከሁለት ዓመት በፊት አንድ ተቋም የሞባይል ስልክ በ32 ሺህ ብር ገዝቶ በመገኘቱ ገንዘቡ ተመላሽ ይሁን መባሉን ያስታውሳሉ።

ከኦዲት ግኝት ጋር የተያያዘ ችግር ተባብሶ መቀጠሉ መንግስትን ገንዘብ እያሳጣ ከመሆኑ በላይ የፍትሃዊነት ጥያቄም እያስከተለ ነው ይላሉ ዋና ኦዲተሩ።

(ኢፕድ)

1 Comment

  1. Most of these purchases include lifetime warranties with free lifetime maintainance repairs so this money is money well spent by the government , we all need to remind ourselves that the Ethiopian government is entitled to give gifts to it’s citizens according to the Ethiopian Constitution so giving these gifts of laptops and telephones to whom the government chose to give is the government’s prerogative. It is not just to ask for the return of these highly essential tools the government had already provided to the hard working individuals whom the government deemed worthy of being offered these items.

    The $798 million birrs are all returned to the government periodically , deposited in various different bank accounts so with patience and determination the auditor can find out the truth , until then I urge you all to keep in mind that limiting the amounts of terms an Ethiopian Prime Minister serves as a Prime Minister can have many adverse unforseen effects in the future since interpreting the Ethiopian Constitution can take longer times than initially anticipated , that is why the majority of Ethiopian citizens living at home or abroad have currently joined forces to carry out the difficult tasks associated with thoroughly removing all ambiguities from the Constitution once and for all .

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.