የትግራይ የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሚያ የአዋጅ ረቂቅ ምን ይዟል?

1 min read

የትግራይ ክልል ምክር ቤት የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሚያ የአዋጅ ረቂቅ እና የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምርጫ እና የምርጫ ሥነ ምግባር የአዋጅ ረቂቅ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ለመሆኑ የአዋጅ ረቂቆቹ ምን ይዘዋል? የዶይቼ ቬለው ሚሊዮን ኃይለስላሴ ተመልክቷቸዋል።

DW

1. ED6355B3_2_dwdownload     

መደበኛ ጉባኤውን እያካሔደ የሚገኘው የትግራይ ክልል ምክር ቤት በመጪው ሳምንት የመጀመሪያ ቀናት በክልሉ እና በኢትዮጵያ ፖለቲካ መሠረታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሁለት የአዋጅ ረቂቆችን ይመለከታል። የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሚያ የአዋጅ ረቂቅ እና የምርጫ እና የምርጫ ሥነ ምግባር የአዋጅ ረቂቅ ናቸው።

የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሚያ እና ሥልጣን እና ተግባሩን ለመወሰን የተሰናዳው የአዋጅ ረቂቅ 33 አንቀፆች እንዳሉት የዶይቼ ቬለው ሚሊዮን ኃይለስላሴ ዘግቧል።  በ27 ገፆች የተሰናዳው የምርጫ ኮሚሽን የማቋቋሚያ የአዋጅ ረቂቅ ከጸደቀ ክልላዊ፣ አካባቢያዊ ምርጫዎች፤ ሕዝበ ውሳኔ አስፈላጊ ሲሆን የድጋሚ ምርጫ የማካሔድ ሥልጣን የሚሰጠው ተቋምን ይመሰርታል። የፖለቲካ ፓርቲዎችን መመዝገብ፣ ምዝገባ የማካሔድ፤ እንቅስቃሴያቸውንም የመከታተል፤ የምርጫ ውጤት የማሳወቅ እንዲሁም የመሰረዝ ኃላፊነት ይኖረዋል።

ረቂቅ አዋጁ ከጸደቀ የሚቋቋመው የምርጫ አስፈፃሚ ተቋም ኮሚሽነር እና ምክትል ኮሚሽነርን ጨምሮ አምስት አባላት ያሉት አመራር ይኖረዋል። የተቋሙ ተጠሪነት ለትግራይ ክልል ምክር ቤት ይሆናል። የኮሚሽኑ በጀት በክልሉ መንግሥት ይሸፈናል።

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምርጫ እና የምርጫ ሥነ ምግባር የአዋጅ ረቂቅ 127 አንቀፆች አሉት። የምርጫ ሕጎች፣ የተወዳዳሪ ፓርቲዎች እና የግለሰቦች ሥነ ምግባርን ጨምሮ በርካታ ዝርዝር ጉዳዮች የያዘ ነው።

በሁለቱ ሰነዶች ላይ ህወሓት፣ ባይቶና፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ እና የትግራይ ነፃነት ፓርቲ ተወያይተውባቸዋል። አረና እና የትግራይ ዴሞክራሲያዎ ፓርቲ ሰነዶቹ እንዳልደረሷቸው በተደረገው ውይይትም እንዳልተፉ ሚሊዮን ዘግቧል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ በሁለቱ ረቂቆች ላይ ያዘጃገውን ዝርዝር ዘገባ የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

እሸቴ በቀለ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.