በአዲስ አበባ የቅርብ ጊዜ የጅምላ መቃብር ተገኘ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

mekabir 1
mekabir
ሁኔ አቢሲኒያዊ ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ

ነገሩ የተከሰተው አርብ እና ቅዳሜ እለት ነው ከስድት ኪሎ ወደ ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የጃንሜዳ ጦር ካምፕ(በቀድሞ ስሙ ሦስተኛ ሻለቃ) ግቢ ውስጥ በትንሹ ወደ 6 የሚጠጉ አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተገኝተዋል! አስከሬኖቹ ሊገኙ የቻሉት ለመንገድ ስራ የጦር ካምፑ ግቢ አጥር ወደ ውስጥ ፈርሶ መቆፈር ነበረበት፡፡ በዚህ ሂደት ላይ ነው እንግዲህ በስካቫተር ሲቆፈር በመጀመሪያ ሁለት አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተንከባለሉ፡፡ በዚህ የተደናገጡት ሰራተኞች ለጊዜው ስራቸውን ያቋረጡ ሲሆን በበነጋው ቅዳሜ እለት ረፋዱ ላይ በሌላ አቅጣጫ ቁፋሮ ሲያደርጉ በዛም በኩል እንዲሁ በብርድ ልብስ የተጠቀለሉ አራት አስከሬኖች በተመሳሳይ ሁኔታ ከአፈሩ ዉስጥ ተገኙ፡፡ በዚህ መሃል ከጦር ካምፑ አካባቢ የተወሰኑ መኮንኖችና ከፍተኛ ማዕረግ(ጄነራሎች) በትከሻቸው ላይ ያለባቸው ሰዎች ወደ ቦታው በመምጣት ስራው እንዲቆም ትእዛዝ ያስተላለፉ ሲሆን በአካባቢው የነበረውንም ሰው ከቦታው አባረው በትነዋል፡፡

በስፋራው ተገኝተው ሁኔታውን ሲከታተሉ እና በስራው ላይም ተሳታፊ የነበሩ ለሰማያዊ ፓርቲ ቅርብ የነበሩ ሰዎች ፎቶ ለማንሳት ጥረት ቢያደርጉም በወታደሮቹ ተመናጭቀዉ ክልከላ ደርሶባቸዋል፡፡ እንደምንጮቻችን እና የምስል ማስረጃዎች ከሆነ አስከሬኖቹ የተጠቀለሉበት ብርድልብስ አንዳችም ሳይቀደድና ሳይበሰብስ ከነአዲስነቱ መገኘቱ ጅምላ ግድያው በቅርቡ የተፈፀመ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ጥርጣሬን አሳድሯል። በጉዳዩ ላይ ማጣራት ለማድረግ ሙከራ ያደረጉት ሰማያዊ ፓርቲ አባሎችንም ፊት እንደተነሳቸውና ለማናገርም ፈቃደኛ የሆነ ሰው አለማግኘታቸዉንም እንዳዉም ቦታውን ባስቸኳይ እንዲለቁ ከሀይለ ቃል ጋር መታዘዛቸውንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ከወታደሮቹ መሀከል የሆነ አንድ ስምና ሀላፊነቱ ለጊዜው ያልታወቀ ምናልባትም የግቢው አዛዥ ሊሆን የሚችል ሰው ይህ ግቢ ሶስት ስርዓቶችን ያገለገለ በመሆኑ የማናቸው እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም ሰዎች በመሆናቸው ክቡር ናቸውና አፈር አልብሷቸው ብሎ ትእዛዝ ሲሰጥ የሰሙ የአይን ምስክሮች ለምንጫችን ስለሁኔታው አስረድተዋል! በሁኔታው በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በእጅጉ ያዘኑና የተደናገጡ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላትና መንግስት ይህne ጉዳይ አጣርተው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አስተያየት ሲሰጡም ተደምጠዋል። በአሁኑ ሰዓት በስፍራው ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ አይታይም፡፡ አካባቢውም በቆርቆሮ ተከልሏል፡፡

ተጨማሪ ብርድልብሱ ደብረ ብርሃን ሲሆን ዲዛይኑ በኢህአዲግ ዘመን በቅርብ የተጀመረው ነው።

7 Responses to በአዲስ አበባ የቅርብ ጊዜ የጅምላ መቃብር ተገኘ

 1. የወያኔው መሪ አቶ መለስ ቀጣፊዋን ዓለም እሳቸውም እንደ ቀጠፉ ከተለዪን ወዲህ ከስድሣ በላይ ጄኔራሎች የተሾሙላት ኢትዮጵያ ማፈን፤ መግደል፤ማሰር፤ ክሥራ ማባረር፤ በዘር በጎሳ መከፋፈል፤ የሃገር ድንበርን ቆርሶ መሸጥ በወያኔ ዘመን እንደ መሪ መመሪያ ሆኖ ተወስዶአል። አሁን በድንገት የተሸሸጉበት የሞት መቃብር ብቅ ብለው እንዲህ ሆነናል ያሉን ሙታን የወያኔ ሰለባዎች ለመሆናቸው ምሥክር አያሻም። ቢሆንማ በሳይንስ ተመርምሮ የሞታቸው ጉዳይ ተረጋግጦ ቤተሰብ ይረዳ ነበር። አፋኝ አገዛዝ የሚያፍነው ህያዋንን ብቻ ሳይሆን አፈር የበላቸውንም ነው። እነማን ይሆኑ? ለምን ተረሸኑ? ጊዜ ይፍታው!

  Avatar for Tesfa

  Tesfa
  December 31, 2013 at 1:35 pm
  Reply

 2. Dear Zehabesha,
  This is a serious crime and the only reasonable step to call on UN and US to paticipate in the investigation. You should rush to accuse anyone. Many past cases still remain unresolved. Thanks!

  Avatar for Truth

  Truth
  December 31, 2013 at 10:44 pm
  Reply

 3. askerenochu lebse alba nachew woe ?

  Avatar for ayalew

  ayalew
  December 31, 2013 at 11:32 pm
  Reply

 4. ተጨማሪ ብርድልብሱ ደብረ ብርሃን ሲሆን ዲዛይኑ በኢህአዲግ ዘመን በቅርብ የተጀመረው ነው።not true debre berhan blanket factory existed before this regime. Telling a lie and accusing without a proof doest help the dead or those alive. unfortunately human life is not very dear to us in Africa very very sad

  Avatar for Tazabi

  Tazabi
  December 31, 2013 at 11:40 pm
  Reply

 5. ምናልባት ይጣራ የግለሰቦች ወንጀልስ ቢሆን የሚል ከመኀላችሁ የለ ይህን የመሰለ ወሬ ተገኝቶ ያው የፈረደበት ወያኔ ገደለ ብላችሁ ደምድማችሁ ንገሩና ። የኔ ችግር ሁሌ በሆነው ባልሆነው የተጣላውን የሚያወግዝ ተሳስቶ እውነትም ቢነግረኝ አላምነውም።

  Avatar for tesfaye g

  tesfaye g
  January 1, 2014 at 7:38 pm
  Reply

 6. ምናልባት ይጣራ የግለሰቦች ወንጀልስ ቢሆን የሚል ከመኀላችሁ የለ ይህን የመሰለ ወሬ ተገኝቶ ያው የፈረደበት ወያኔ ገደለ ብላችሁ ደምድማችሁ ንገሩና ። የኔ ችግር ሁሌ በሆነው ባልሆነው የተጣላውን የሚያወግዝ ተሳስቶ እውነትም ቢነግረኝ አላምነውም።ችግሩ ETV ስለ ገነት ያወራል ተቃዋሚዎች ስለ ገሐነም ትነግሩናላችሁ እውነት ደግሞ መሐል ላይ ቆማ ግራ ገብቷታል።

  Avatar for tesfaye g

  tesfaye g
  January 1, 2014 at 7:51 pm
  Reply

 7. አንጀት ይበላል – ልብ ያቃጥላል! ኦፍፍፍፍፍፍ….

  Avatar for ተከለ

  ተከለ
  January 18, 2014 at 9:16 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.