የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሄራዊ ፓርቲ በአርበኛ ኮማንደር አበራ ጎባው እና በሌሎችም ጀግኖች መሰዋት የተሰማውን ሀዘን ገልፆ መግለጫ አወጣ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሄራዊ ፓርቲ

መግለጫ

የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሄራዊ ፓርቲ አባል የሆነው አርበኛ ኮማንደር አበራ ጎባው እና የሌሎችም ጀግኖቻችን ነብስ ይማርልን!!!

የወያኔን የዘር ማጥፋት እኩይ ተግባርና የህዝብ ጥያቄን ከመመለስ ይልቅ እንደ ሁለተኛ ዜጋ በመጨፍጨፉ ያማረረው ህዝባችን ከኢትዮጵያ ዳር እስከ ዳር መብቱን ለማስከበር በአንድነት የእንቢተኝነት ትግሉን ከወያኔ ጋር አንገት ላንገት መተናነቅ ከጀመረ ወራቶችን አስቆጥሯል ይህንን የሕዝባችንን እምቢተኝነት ተከትሎ የኢትዮጵያ ህዝብ ቤሄራዊ ፓርቲ ከህዝባችን ጎን በመቆም የወያኔን ግብዓተ መሬት በማፋጠን ላይ ታላቅ ተጋድሎ እያደረገ ነው። በቅርቡም በጀግንነት (በዶጋአው በርሃ) በሞት ለተለየን ኮማንደር አርበኛ አበራ ጎባው እንዲሁም በህዝባችን እንቢተኝነት ትግል ውስጥ በሞት ለተለዩን ሌሎችም ጀግናና አርበኛ ወገኖቻችን ሞተቃቸው ሀዘናችን ቢሆንም ትግላችን በይበልጥ አጠናከረው እንጂ አላሣፈረንም።

በዚህ አጋጣሚ ለሟች ቤተሠቦች ሁሉ እግዚአብሄር ሙሉ ፅናቱን ይስጣቹሁ እንላለን። የኢትዮጵያ ህዝብ ብሄራዊ ፓርቲ ከህዝባችን ጎን እንደተሠለፈ ሁሉ የኢትዮጵያ ህዝብም ከጎናችን ተሠልፎ ይህን ዘረኛ መንግስት በአስቸኳይ እንድናስወግድ ጥሪያችንን እናቀርባለን

ድል የኢትዮጵያ ህዝብ ነው!!
epnp-002

One Response to የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሄራዊ ፓርቲ በአርበኛ ኮማንደር አበራ ጎባው እና በሌሎችም ጀግኖች መሰዋት የተሰማውን ሀዘን ገልፆ መግለጫ አወጣ

  1. Wey gud!
    Yihem tebale? Ere ebakachihu beyemenderu parti ena dirjit maquaquam yiqum! Ethiopian yegedelat yedirjit bizat new

    Mechal Degu
    October 20, 2016 at 12:57 pm