/

የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ አባላት አሁንም ጋምቤላ ገብተው ህጻናትን ጠልፈው ወሰዱ | 11 ወገኖቻችንን ገድለዋል

1 min read

(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው 2008 ዓ.ም 200 የሚሆኑ ሕጻናትንና ከብቶችን ከጋምቤላ ዘርፈው የሄዱት የደቡብ ሱዳን የሙሌ ጎሳ አባላት አሁንም በደጋሚ በርካታ ወገኖችን በጋምቤላ በመግደል ተጨማሪ ህጻናትን ጠልፈው መሄዳቸው ተሰማ::

የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ አባላት ከትናንት በስቲያ እሁድ በጋምቤላ ወገኖቻችን ላይ ጥቃት በመፈጸም የገደሏቸው ሰዎች ቁጥር 11 የደረሰ ሲሆን ከዚህም በላይ ሊሆን ይችላል እየተባለ ነው:: እነዚሁ የሙርሌ ጎሳዎች ወደ 20 የሚጠጉ ህጻናትን ጠልፈው መሄዳቸውም ተሰምቷል::

ሕወሓት መራሹ መንግስት ባለፈው ዓመት በሙርሌ ጎሳ አባላት የተዘረፉትን ህጻናት የተወሰኑትን አስመለስኩ ቢል ከ50 በላይ ህጻናት እስካሁን የት እንደደረሱ እንደማይታወቅ በተደጋጋሚ ዘ-ሐበሻ መዘግቧ አይዘነጋም::

በሙርሌ ጎሳ አባላት ተጥልፈው የተወሰዱት ህጻናት የአኝዋክ ብሔረሰብ ልጆች ናቸው::

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.