የ24 ዓመቷ ወጣት ንግስት ይርጋ ከአርበኞች ግንቦት 7 ተልእኮ ትቀበል ነበር የሚል ክስ ተመሰረተባት | የክሱን ቻርጅ በPDF ይዘናል

1 min read

የክሱ ቻርጅ በPDF

እነ ንግስት ይርጋ የቀረበባቸው ክስ ተነበበላቸው

እነ ንግስት ይርጋ ( ስድስት ሰዎች) በማእከላዊ ለአራት ወራት ጊዜ ከቆዩ በኋላ አቃቤ ህግ ክስ ታህሳስ 28 ቀን 2009 የሽብር ክስ መስርቶባቸዋል። የዛሬ ቀጠሮ የነበረው ክሱ በችሎት እንዲነበብላቸው ሲሆን የቀረበባቸው 18 ገፅ ክስ ተነቦላቸዋል። በሁሉም ተከሳሾች ላይ የቀረበው ክስ አንድ ሲሆን፤ በ1996 ዓም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32[1] (ሀ) እና (ለ)፣ አንቀፅ 38 እና በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀፅ 3 (4) እና (6) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ የተመሰረተ ክስ ነው። አርበኞች ግንቦት ሰባት ከተባለ ሽብርተኛ ቡድን ተልእኮ በመቀበል እና የሽብር ቡድኑ አባል በመሆን ሃገር ውስጥ ካሉ አባሎች እና አመራሮች እንዲሁም ውጪ ሃገር ከሚገኙ አባል እና አመራሮች ጋር በመፍጠር በስልክ እና በድህረ ገፅ ግንኙነት በመፍጠር በአማራ ክልል በተለያዩ ዞኖች እና ከተሞች አመፅ በመምራት፤ በአዲስ አበባ የሽብር ጥቃቶች እንዲፈፀሙ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ክሱ ይገልፃል።

በተጨማሪም ተከሳሾቹ መተማ ዙሪያ ባስነሱት አመፅ በመኖሪያ ቤት፣ በድርጅት፣ በመንግስትና በግለሰብ ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት በማድረስ ከ95,986,433 (ዘጠና አምስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሰላሳ ሶስት) ብር በላይ ንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ፣ በጎንደር ከተማ በሚገኙ ቀበሌዎች በመንግስት እና በህዝብ ተቋም ተሽከርካሪዎች ላይ ከ10,679,945 (አስር ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰባ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባምስት) ብር በላይ ንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ እንዲሁም በምእራብ ጎጃም በሚገኙ ከተሞች ከ95, 345, 363 (ዘጠና አምስት ሚሊዮን ሶስት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ስልሳ ሶስት) ብር በላይ የሚገመት ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸው በክሱ ተካቷል።

ክሱ ከተነበበላቸው በኋላ ተከሳሾች መቃወሚያ እንዳላቸው ተጠይቀው ፤ የ1ኛ ተከሳሽ ጠበቃ (አቶ ሄኖክ አክሊሉ) እና የ4ኛ ተከሳሽ ጠበቃ እንዳላቸው የክስ መቃወሚያ እንዳላቸው ተናግረዋል። የተቀሩት ተከሳሾችም ጠበቃቸው በዛሬው እለት ባይገኙም በክሱ ላይ ተቃውሞ እንዳላቸው እራሳቸው ተናግረዋል። ጠበቃቸው በዛሬው እለት ያልተገኙ ተከሳሾች ጠበቃቸው የሚመቻቸው ጥር 23 እንደሆነ እና ቀጠሮው በዛ ቀን እንዲሆንላቸው ዳኞችን ጠይቀዋል።
ተከሳሾቹ የቀረበባቸውን ክስ በአግባቡ መከራከር እንደሚፈልጉ ገልፀው ይህን ለማድረግ ግን ህገ መንግስቱ፣ ወንጀለ መቅጫ፣ ፀረ ሽብር አዋጅ እና ሌሎች አዋጆች ማረሚያ ቤት እንዲገቡላቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል። ዳኞችም ህጎቹን እና አዋጆቹን ማረሚያ ቤቱን እንዲጠይቁ ነግረዋቸዋል። ተከሳሾቹም ማረሚያ ቤቱ ከወረቀት እና ከእስክብሪቶ አቅም እንኳን ማግኘት እንደሚከለከሉ በመናገራቸው፤ በሚቀጥለው ቀጠሮ ከጠበቃዎቻቸው ጋር ተነጋግረው ይህን አቤቱታቸውን በፅሁፍ እንዲያቀርቡ ተነግሯቸዋል።

በክሱ ላይ ያላቸውን መቃወሚያ በፅሁፍ ለመቀበል ለጥር 23, 2009 ቀጠሮ ተሰጥቷል።
በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች የሚከተሉት ናቸው።
1ኛ ንግስት ይርጋ ተፈራ ( እድሜ 24, ሰሜን ጎንደር)
2ኛ አለምነህ ዋሴ ገ/ማርያም ( እድሜ 57, ሰሜን ጎንደር)
3ኛ ቴዎድሮስ ተላይ ቆሜ ( እድሜ 18, ሰሜን ጎንደር)
4ኛ አወቀ አባተ ገበየሁ ( እድሜ 31, አዲስ አበባ)
5ኛ በላይነህ አለምነህ አበጀ ( እድሜ 29, ባህር ዳር)
6ኛ ያሬድ ግርማ ሃይሌ ( እድሜ 46, አዲስ አበባ)

የክሱ ዝርዝር የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ማግኘት ይቻላል፡፡ የክሱ ቻርጅ በPDF

 

ምንጭ: የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት

4 Comments

 1. lib belu Ag7 yehin betemelekete

  andim mastebabeya alsetem !!

  be G7 sim weyane eyegedele selehone

  g7 le propaganda temechew !!

  be G7 sim sintu mote sintu tasere sintu tegerefe !!

  HO G7 yematwedewin Amara weyane fejelih

  congra !!!

  • እና በስምህ ሰው ይገደላልና ኣትታገል ነው!!!

   ወያኔ የሚለጥፍብህ ስም ያጣል?
   ኣርበኞች ግ. 7 ባይኖር ሻዕቢያ ይልሓል። ወይ ግብጥ ፥ ወይም ኦነግ፥ ኦብነግ ወዘተ ኣልያም እንዲሁ ያይንህ ቀለም ኣላማረኝም ይልሓል። ምን ታደርገዋልህ፥ ዓይንህን አውጥተህ ትጥላለህ።

   ሴሉ እውነት ይሄ ጠፍቶህ ነው ወይስ ወያኔ ኔህ?

 2. ወያኔ ምን ያህል ከፋፋይና ዘረኛ እንደሆነ ሁላችንም የምናውቀው ነው። አሁን በሃገራችን በወያኔ የሚሰራው ሴራ በጣሊያን ወረራ ጊዜ ያልተፈጸመ ግፍ ነው። ሆን ተብሎ ማሰብ የሚችሉ የአማራና የኦሮሞ ልጆችን ማሰር፤ ማፈን፤ መሰወር፤ መደብደብ የወያኔ የቀኑ ሙሉ ሥራ ነው። በመሰረቱ ሃገሪቱ ለአንድ ዘር ብቻ የተመቻቸች ሌላው እንዳይተነፍስባት በወያኔ የአጋዚ ጦርና በተወሳሰበው የስለላ መረባቸው አንድን ከአንድ በማጋጨት፤ አንድ እንዲያደርገን የቆሙ አድባራትንና ተቋማትን በእሳት የሚያጋይ ወስላታ ድርጅት ነው። ትግራይ ውስጥ ከሚደረጉ ቅስቀሳዎች በጥቂቱ ልጥቀስ። አሁን የጊዜአዊ አዋጅ ከታወጀ በህዋላ የትግራይ ክልል (የጠባቦች አጠራር) ለእኔ የትግራይ ክፍለሃገር የሚደረጉ የሬዲዮ፤ የቴለቪዝንና የስብሰባ ቅስቀሳዎችን ለተመለከተ ወያኔ በምንም አይነት ከጠባብ ብሄርተኛ አስተሳሰቡ የሚቀይረው አንዳች ነገር እንደለለ ያመለክታል። የሚዘፈነው ያዘው ጥለፈው፤ ያለፈና የበሰበሰ የበርሃ ጀግንነት፤ የትግራይን የበላይነትና ጠንካራነት፤ የጠለምትና ሌሎችን የሃገሪቱን ክፍል የትግራይ አካል ለማረግ የማወናበጃ ቅስቀሳ በስፋት ያናፍሰዋል። በመሃል ሃገር ለማታለል ከተቃዋሚ ጋር ድርድር፤ የሃገር አንድነትና ራእይ በማለት ወያኔ ያጭበረብራል። ህብረትና አንድነት የሚጀምረው ራሱን እንዲያገል ኢትዮጵያዊነቱን እንዲክድ ለዘመናት ከተለፈፈለት ከትግራይ ህዝብ ነው። ዛሬ ለዘመናት ከኖሩበት የተለያዪ የሃገሪቱ ክፍል እየተለቀሙ ወደ ትግራይ ወያኔ የወሰዳቸው የትግራይ ተወላጆች ለራዲዮና ለቴሌቪዝን ጣቢያዎች የሚሰጡት ቃለምልልስ ወያኔ ህዝባችንን ለመከፋፈል ከሚጠቀምበት አንድ ዘዴ ነው። አሁን ከግንቦት 7 ጋር ስትሰሩ ያዝናቹሁ እያለ በአማራው ክልል የሚያፍናቸው ወጣቶች ወንጀላቸው ለእውነት መቆሟቸው ብቻ ነው።
  ወያኔ ወስላታ ነው። እራሱ መረጃ አዘጋጅቶ በፍተሻ የተገኘ ነው በማለት ሰውን ይወነጅላል። የብዙ ሰዎች ደም ከመቃብር ማዶ ይጣራል። ከትግራይ በረሃ እስከ አዲስ አበባው ስልጣናቸው የወያኔ ባለስልጣኖችና ካድሬዎች እጃቸው በሰው ደም የተለወሰ ልብ የሌላቸው ለራስ አዳሪ ናቸው። መቀሌ ዩንቨርስቲ የሆነ አንድ ነገር ልበልና ይብቃኝ። አዲስ ተማሪዎች በድልድላቸው መሰረት ከየስፍራው እየገቡ ነው። የምኝታ (ዶርም) ድልድል ላይ አንድ የወያኔ ካድሬ ይቆምና ከኦሮሚያ የመጣሁችሁ ሴቶችና ወንዶች ለየብቻ እዚህ ተሰለፉ፤ ከአማራ ከደቡብ ህዝቦችም ለብቻ ተሰለፉ አለና ሁሉም በየዘሩ ጥላ ሥር ተሰለፈ። ከዛም ወንድ ተማሪዎች አማራ ከአማራ፤ አሮሞ ከኦሮሞ ሁሉም በየዘሩ ዶርም ተሰጣቸው። ማታ ራት ላይ ሁሉም በየዘሩ ሲበላ ማየት መፈጠርን ያስጠላል። ያ ነው የወያኔ የብሄርና የብሄረሰቦች መብት ማለት። ገና በልጅነቷ ንግሥት ይርጋንና ሌሎችንም ጨለማ ቤት ያስቆለፈባቸው አንዲት ሃገር አንድ ህዝብ የወያኔ አገዛዝ በቃኝ በማለታቸው እንጂ ከግንቦት ሰባት ጋር አንዳችም ግንኙነት የላቸውም። ወያኔ ሲመቸው የጸረ ሽብር፤ የጸረ ሙስና የተቃዋሚ አባል በማለት ለእሥራትና ለሞት የሚዳርጋቸው እነማን እንደሆነ አንባቢ ሊያስተውል ይገባል። ዘራፊው በሙስና አዘቅት ውስጥ የሚዋኘው ራሱ አሳሪውና ገራፊው ወያኔና በዙሪያው ያሉ እበላ ባይ ካድሬዎቹ ናቸው። የንግሥት ይርጋንና የሌሎችን የክስ ዝርዝር ስመለከት አንድ ነገር ትዝ አለኝ። ለካ ለእንጀራም ደም ማፍሰስ፤ መዋሽት ማሰር መግረፍ መግደል ሙያ ይሆናል። አይ ወያኔ ክሱ የውሽትና እሳት ውስጥ ሊጣል የሚገባው ልፋጭ ቆሻሻ ነው።

 3. ጀግናዋ ንግሥት ይርጋ የምርመራ የሰጠችው ቃል በGestapo የሰቆቃ ምርመራ ከሚገኘው ጋር ልዩነት የለውም። ወያኔ በትግስት ላይ የፈጸመው ሰቆቃ ይቅር በወጣት ሴት ልጅ ላይ፥ በእንሰሳ ላይም ሊፈጸም የሚገባ ኣልነበረም። ጅግናዋ ግርፋቱን፥ ድብደባውን፥ ስድቡን፥ ሁሉ የምትችል ነች፥ ግን ወያኔ መንፈስ የሚያዝል ኬሚካል በመጠቀም የሚፈጽመው ግብረስጋዊ ሰቆቃ ማንኛውንም ሰብዓዊ ፍጡር ይሰብራል። ንግሥትን በዚህ ጭቃኔ ካልሆነ ሊሰብሩዋት ኣይችሉም። ለነገሩ እነስብሓት/ድብረጺዮንና ኣባይ በአማራ ልጆች ላይ ያለውን ጥላቻ የሚያስተነፍሰው ንጹሕ አማሮችን በማሰቃየት፥ በማሳደድ፥በማዋከብ፥ በማክሰር፥ በማስፈራራት፥ በመደደብ፥ ንብረታቸውን በመዝረፍ፥ ሴቶችን በመድፈርና በጭካኔ በመግደል ነው።

  በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን የወያኔን የሰቆቃ ምርመራና በተለይም በወጣት ሴቶች ላይ የሚያካሂደውን ግብረስጋዊ ሰቆቃ፥ መካን እንዲሁኑ የሚወጋቸው መድሓኒት፥ ክእስር ከወጡ በኋላም ፈዝዘው እንዲቀሩ የሚያደርግ ኬሚካል መጠቀሙን ማጋለጥ ያስፈልጋል።

  ብርታት በእስር ለሚገኙ ጀግኖች!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.