ሸክማችንን እንተጋገዝ፣ ውጣ ውረዳችንን እናቅል!

Filed under: News Feature,ስፖርት |

/በፈረሰኞቹ ገጽ/

መስከረም ወር ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ የጭንቅ ወር ነው ብንል የተሳሳትን አይመስለንም፡፡ በተለይም በኑሮ ውጣ ውረድ ለተዳከሙ እና በቁጠር በዛ ያሉ ልጆች ላሉበት ቤት ይህ ወር የጣር ወር ነው፡፡ በዚህች ድህነት በተጫናት አገር ውስጥ ጭንቀቱ ብዙ ነው፡፡ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ሩጫ የዕለት ጉርሱን ለማግኘት ነው፡፡ ከዚያ ከዘለለ አልባሳትን እና መሰል መሰረታዊ የኑሮ ፍላጎቶችን ለማሟላት ሩጫው የበዛ ነው፡፡ የአመት በዓል ወጪ፣ ለተማሪዎች ዩኒፎርም፣ የትምህርት መሳሪያዎች እና አልባሳትን ጨምሮ ወጪው እጅግ የበዛ ነው፡፡ አብዛኛው ህዝብ በድህነት ውስጥ በሚኖርባት እንደ ኢትዮጵያ ላለች አገር የእነዚህን ወጪዎች ክብደት ማስላት ከባድ አይመስለንም፡፡

በዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ ታልፎ ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት የመላክ እና የትምህርት ቁሳቁሶችን የማሟላት ግዴታዎች በወላጅ ትከሻ ላይ የወደቀ ነው፡፡ ሆኖም በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙ እንጂ ተገቢውን የትምህርት ቁሳቁስ ሳያሟሉ በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡

አቶ ኃይሉ በዛብህ በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኝ በአንድ የመንግስት ትምህርት ቤት ውስጥ የእንግሊዘኛ መምህር ናቸው፡፡ በተማሪዎች ላይ የሚታየውን የትምህርት ቁሳቁስ እጥረት አንስተን ማውራት ጀመርን፡፡ መምህሩ ስለ ትምህርት ቁሳቁስ ዕጥረቶች ሲያወሩ ምሬት ፊታቸው ላይ ይነበባል፡፡

«በመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ማስተማር ራሱን የቻለ የማህበረሰቡን የኑሮ ውጣ ውረዶች ለመረዳት ያስችላል፡፡ ማህበረሰባችን ከኑሮ ጫና እና ከኑሮ ጋር የሚያደርገውን ግብ ግብ ማሳያ ናቸው፡፡ በተለይም መስከረም ወር ላይ ያለውን ጫና መናገር ከባድ ነው፡፡ ተማሪዎች ዩኒፎርም አሟልተው በትምህርት ገበታቸው ላይ እንዲገኙ ህግ ስለሚያስገድድ ወላጆች ባለ በሌለ አቅማቸው ልጆቻቸውን ዩኒፎርም አልብሰው ይልካሉ፡፡ ሆኖም ከዚህ በዘለለ የትምህርት ቁሳቁሶች ላይ ያሉት ችግሮች ሸክሙ በመምህሮች ላይ ይወድቃል፡፡

እኔ በማስተምርበት ትምህርት ቤት ውስጥ በአንድ የ50 ሉክ ደብተር ላይ 4 የተለያዩ የትምህርት ዓይነቶችን የሚማሩ ተማሪዎች አሉ፡፡ እስኪርቢቶ እና መሰል የጽሕፈት መሳሪያዎችን አለመያዝና እና አለማሟለት የተለመዱ ናቸው፡፡ ለትምህርት አሰጣጥ ሂደት ግዴታ የሚያስፈልጉ የትምህርት ቁሳቁሶች ከሚሟሉት የሚጎድሉት፣ ከሚይዙት የማይዙት ይበልጣሉ፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን በምግብ ዕጥረት ምክንያት በመማሪያ ክፍል ውስጥ የሚወድቁ ተማሪዎች ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም፡፡

እኚህ ከዓመት ዓመት መፍትሄ ያጣንላቸው ችግሮች ናቸው፡፡ አንድ ተማሪዬን ደብተር ለምን የለህም ብዬ በጠየቅኩበት ወቅት «በዚህ ወር ለታላቅ ወንድሜ ነው የተገዛው፤ ለእኔ በሚቀጥለው ወር ነው የሚገዛልኝ» ያለኝም አስታውሳለሁ፡፡ ይህ ተማሪ የመጀመሪያውን ወር ደብተር ሳይኖረው ተምሮ አገባዷል፡፡ ሌላ አንድ ተማሪ ነጭ ሉኮች ተሰብስበው እንደ ደብተር ተሰርተው ተሰጥተውት ሁሉንም የትምህርት አይነቶች በተሰበሰቡት ወረቀቶች ላይ ይማራል፡፡ ለምን ብዬ ስጠይቀው የሠጠኝ መልስ ዛሬም ድረስ በአዕምሮዬ ውስጥ አለ፡፡ «አባቴ በአንድ ድርጅት ውስጥ የጥበቃ ሰራተኛ ነው፡፡ እነኚህን ወረቀቶች ከሚሰራበት መስሪያ ቤት ውስጥ ሰብስቦ አሳርቶ አምጥቶልኝ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ደብተር ግዛልኝ ብዬ ብጠይቀው መግዛት ስለማይችል ከትምህርቴም ሊያስቀረኝ ይችላል፡፡ ምክንያቱም ገንዘብ የለውም፡፡»

*

ሸክማችንን እንተጋገዝ፣ ውጣ ውረዳችንን እናቅል!

እንዲህ አይነት ችግሮችን ለመስማት ካልሰለቸን በስተቀር በየቅያሱ ሞልቷል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ አገራችን የችግር እጥረት የለባትም፡፡ ሆኖም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ አቅማችንን በፈቀደ መጠን በመማሪያ ቁሳቁሶች ላይ ያሉትን ችግሮች በመጠኑም ቢሆን ለመቅረፍ መንቀሳቀስ አለብን፡፡ ተማሪዎች ያለ ሰቀቀን እና ስጋት የሚማሩበትን መንገድ ማመቻቸት አለብን፡፡ ደብተር፣ እስኪርቢቶ፣ እርሳስ፣ መቅረጫ፣ ላጺስ፣ ቦርሳ፣ ማስመሪያ እና መሰል የትምህርት መማሪያ ቁቁሶችን መለገሰ ቀላል አይደለም፡፡ ለዚህም አማራጮችን እናስቀምጥ፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ባሳለፍነው በ2008 ዓ.ም መገባደጃ ላይ በዚህ መልካም ተግባር ላይ ተሳትፈው ነበር፡፡ ቁጥራቸው እጅግ በርካታ የሆኑ የትምህርት ማማሪያ ቁሳቁሶችን ከደጋፊዎች ሰብስበው አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች አድርሰዋል፡፡ ለትምህርት ቤቶች አስረክበዋል፡፡ ይህንን መልካም ስራ አሁንም ቀጥለውበታል፡፡ በተለያዩ አከባቢዎች ያሉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በዚህ የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ የማሰባሰብ በጎ ተግባር ላይ ተሳታፊ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡

ይህ ለመልካም ተግባር ቀና ልብ ያለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሊሳተፍበት የሚገባ በጎ ተግባር ነው፡፡ አንድ ዜጋ ያለችግር እንዲማር ማድረግ ለአገር አንድ ውለታ እንደመስራት ይቆጠራል ብለንም እናምናለን፡፡ በመሆኑም ከታች ባሉ አድራሻዎች በመጠቀም ማንኛውንም አይነት የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ በመስጠት የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ ዘንድ እንጠይቃለን፡፡

እስራኤል መርካቶ 0911633514
ወይኗ ሳሪስ 0920843104
ኤላ 7ኛ 0933673367
ኪራ ፈረንሳይ 0910655714
ነባ ገርጂ 0919349749
ማሲንጋ ኮተቤ 0911968274
ፍቅር ቡልጋሪያና ሜክሲኮ 0928412436
ሙሌ መርካቶ 0911851578
ወንድ ወሰን ጣሊያን ሰፈር 0913184363
መክሱድ ኮልፌ 0978696937
ሸዊት ጦር ሀይሎች 0947654422
መላኩ አውቶብስ ተራ ልኳንዳ 0921345178
ተዲ ቀበና 0913098992
ብሩኬ አብነት 0913037533
ምናሴ ሳሪስ ቃሊቲ 0926280264
ቡራ መገናኛ 09 12795338
ፍሰሀ ደጃችውቤ 0913838269
ተወልዴ ጨርቆስ 0913112739
እዩኤል 4ኪሎ 0935925291
ካስትሮ አየርጤና አለም ባንክ 0929193710
ቤቢ ስታዲየም 2 ቁጥር በር 0911574472

*

ማስታወሻ፡- መረጃው ለማህበራዊ ድረ ገጽ ተጠቂሚዎች ይደርስ ዘንድ ሼር በማድረግ ይተባበሩ፤ እናመሰግናለን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.