ኃይሌ ገብረሥላሴ አሰልጣኝ ቶሌራ ዲንቃን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የሰጠበት ደብዳቤ

Filed under: News Feature,ስፖርት,የዕለቱ ዜናዎች |


ኃይሌ ገብረሥላሴ አሰልጣኝ ቶሌራ ዲንቃን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የሰጠበት ደብዳቤ

One Response to ኃይሌ ገብረሥላሴ አሰልጣኝ ቶሌራ ዲንቃን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የሰጠበት ደብዳቤ

 1. ሲያሸንፉ ጉሮ ወሸባየ፤ ሲሸነፉ አይናችሁ ላፈር የምንላቸው ኢትዮጵያዊያን የረጅምና የቅርብ ርቀት ሩጫ ተወዳዳሪዎች ለሃገራችን ጥምረት በቀደሙት ዘመናትና አሁን በዘር በተከፋፈለችው ሃገራችን ለህዝባችን ተስፋና በዓለም ላይ ሃገራችን ስሟ እንዲጠራ ቋሚ ብርሃን ከሆኑት በጣት የሚቆጠሩ ስኬቶች ውስጥ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ። የወንድና የሴት አትለቲክስ ተወዳዳሪዎች ፍዳ እንደሃገራችን የአንገት ማተብ ትብታቡ ብዙ ነው። በተለይ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን አስረሽ ምቺው እኔ የምልሽን ፈጽሚ ያለዚያ እንዲያና ወዲህ ማለት አልፈቅድም የሚሉት አሰልጣኝ ተብየዎች በደል ለመፈጸማቸው ማስረጃ አለ።
  አሁን ደግሞ ይህ እኩይ ተግባር ማን ይነካኛል በሚል ዘይቤ አሰልጣኝን መደብደብ፤ መሳደብ፤ በድህነት የለፉ አትሌቶችን በሰበብ ከወድድር ማገድ፤ በእጅ አዙር በስጦታና በሌላ ድብብቆሽ መንገድ የማይገባ ነገርን በስውር መቀበል የተለመደ ባህሪ ሆኖአል። ከዚህ ባሻገር ሆድ የመድሃኒያለምን ከበሮ አክሎ አሰልጣኝ ተብሎ ሲመደብ ለተመልካችም አይበጅም እንኳን ለሰልጣኝ። ሴትና ወንድ አትሌቶቻችን የሃገር ሃብት እንጂ የግል እይታና የፓለቲካ የማራመጃ መድረኮች አይደሉም። ማሰብ ያቃተው የፓለቲካ ጫት ጢቢራውን ያዞረው የዲያስፓራ የረጅም ከዘራ ፓለቲከኛ የቀድሞውን ባንዲራ በመስጠት አትሌቱ (ዋ) ከወያኔ ጋር አተካራ ላለመግጠም ዛሬ በሃገሪቱ ምድር የሚውለበለበውን ባንዲራ መጠቀሟ እንደትልቅ በደል ተቆጥሮ ጥሩንባ ሲነፋበት መስማትና ማንበብ ልብን ያማል።
  ገንዘቤ ድባባን እንዲህ ቢሆን ታሸንፍ ነበር እንደዚህ ስለሆነ ነው ያላሸነፍሸው በማለት በየመድረኩ ወሬ የሚያናፍሱ ጋዜጠኞች ሳይሆኑ አላዛኝ ሞሾ አውጭዎች ናቸው። ገንዘቤ ሃገርዋን ለዘመናት በድንቅ የስራ ስኬትዋ ያስጠራች ምርጥ የሃገራችን ልጅ ናት። ማንም አትሌት በሁሉ ውድድር አያሸንፍም። ታሪክ የሚያመላክተው ያን ነው። ገንዘቤ በሚናፈሰው ወሬ ጭራሽ ማዘን የለባትም። ወሬን ለወረኞች መተው ነው። ይልቁን የሚያምሽን ነገር በአዋቂ በመታየት ወደፊት ለሚጠብቅሽ ውድድር ራስሽን ማዘጋጀት ይኖርብሻል። የጥቂቶች አፍራሽ ጡርንባ የኢትዮጵያን ህዝብ አይወክልም። ህዝባችን አንቺንና ሌሎችንም ይወዳል ያከብራል። ማሸነፍ ወይም አለመሸነፍሽ ይህን ከበሬታሽን ከህዝባችን ልብ ውስጥ ፈልቅቆ የሚያስወግድ ምድራዊ ሃይል የለም። ያልሆነ ወሬ ማናፈስ፤ በስብሰባ መካከል እኔን ምረጡኝ በማለት ሌላውን መሳደብ አልፎ ተርፎም አሰልጣኝን መደባደብ መወላገድ ነው። ይልቅስ በተጠቃለለ እይታ፤ በችሎታ፤ በፍቅርና በህብረት ዛሬም ወደፊትም ሃገራችንን በመልካም ነገር ለማስጠራት አብረን እንነሳ።

  Tesfa
  August 14, 2017 at 11:21 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.