ቄሮ በኦሮሚያ ክልል የጠራውን የአምስት ቀን አድማ ግቡን ስለመታ በሦስተኛው ቀን አቋርጫለሁ አለ | ከቄሮ የተላለፈውን አስቸኳይ መግለጫ ይዘናል

1 min read

ኦሮሚያ ውስጥ እየተካሄደ ባለው በቤት ውስጥ መቀመጥና የግብይት አድማ በተመለከተ ከቄሮው አስተባባሪዎች የተሰጠ መግለጫ
ነሃሴ 25, 2017

አስቸኳይ!

በመላ ኦሮሚያ በኦሮሞ ቄሮ የተጠራውና እንደታቀደው በነሃሴ 23, 2017 የጀመረው የቤት ውስጥ መቀመጥና የግብይት ማቋረጥ አድማ ለሶስተኛ ቀን የቀጠለ ሲሆን በእቅዱ መሰረት እስከ ነሃሴ 27 እንደሚቀጥል የሚጠበቅ ነው። ይሄ አድማ በተያዘለት እቅድ መሰረት ተጀምሮ እየሄደ ያለ ሲሆን ባንዳንድ ቦታዎች እንዳውም በዋዜማው አመሻሽ ላይ ቀደም ብሎ ጀምሮ ነበር። ላለፉት ሶስት ቀናት በትልልቅም ሆነ በትንንሽ ከተሞች የንግድ እንቅስቃሴው ቆሟል። ወደ ዋና ከተማዋ ፊንፊኔ የሚገቡትም ሆነ የሚወጡት የትራንስፖርት ግልጋሎቶች ተቋርጠዋል። የኢኮኖሚ ማዕከላትን የሚያገናኙ ዋና ዋና የንግድና ትራንስፖርት መስመሮችም ተዘግተዋል። የከተማ ውስጥ እንዲሁም ከተሞችን የሚያገናኙ የትራንስፖርት ግልጋሎቶች ተቋርጠዋል በኦሮሚያ። ባጭር ባለፉት ሶስት ቀናት ኦሮሚያ እንቅስቃሴ አልባ ሆኖ ሰንብቷል።

አወዳይ ከተማ

ይሄ አድማ የተጠራው በጥቅምት 2016 የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተነሳ ባጭር ጊዜ ውስጥ መሆኑ ያለ ምክኒያት አልነበረም። የኦሮሞን ተቃውሞና አመጽ ባስቸኳይ አዋጁ አኮላሽቼዋለው በሚል ስርዓቱ የሚነዛውን ፕሮፓጋንዳ ለመናድና ለማጋለጥም ጭምር ሆኖ፣ በጥልቀት በታሰበበት ሁኔታና ለሚቀጥለው አዲስ የትግል ምዕራፍ ይረዳን ዘንድ በስትራቴጂና በሰከነ መልኩ ሃይላችንን በማሰባሰብ ትግሉን ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግረን እንደምናስቀጥለው በተጨባጭ ለማረጋገጥም ጭምር ነው። ስለሆንም የተጠራው አድማ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳት በኋላ ብዙም ሳይቆይ በአዲስ ስልትና በተለየ መንገድ መቀጠሉን በተጨባጭ ለማረጋገጥም ነው።

የአድማው ዘመቻ የሚለኩ (measurable) አላማዎች የነበሩት ነው። የመጀመሪያው፣ የኦሮሞ ትግል የራስን እድል በራስ መወሰን (self-determination) የሚለውን ወሳኝ ግብ ሳይመታ ሊቀለበስ እንደማይችል ለስርዓቱም ሆነ ለሌሎች ግልጽ መልዕክት ለማስተለለፍ ነው። ሁለተኛው የኢኮኖሚ እድገት አምጥቻለው በሚል ስርዓቱ ያልተገባ ቅቡልነት (undeserved legitimacy) ለማግኘት የሚያደርገውን ከንቱ ጥረት የሰዎችን የየእለት ኑሮ በማይጎዳ መልኩ ኢኮኖሚው እንዲቀዘቅዝ በማድረግ ስርዓቱ እንዲዳከምና እንዲንኮታኮት ማድረግ ነው። ሶስተኛውና ሌለኛው ወሳኝ ምክኒያት ደግሞ የኦሮሞ ህዝብ በአንድነት፣ በአንድ ጊዜና በሚፈልገው ጊዜ እንደሚነሳ ማሳየት፤ በዚሁም የኦሮሞ ብሄርተኝነትን ህዝባዊ መሰረት ለማራጋገጥ ነው። አራተኛው የተቃውሞ አድማው መልዕክት የኦሮሞ ትግል ከእምቢተኝነት (resistance) ወደ ተቀናጀ የድል ምዕራፍ (final victory) መሸጋገሩን ለማመላከት ነው።

እናም የቄሮው የተቀናጀ አድማ ዛሬ በ3ኛው ቀን እነዚህን ግቦች መምታቱን ገምግመን ተገንዝበናል። የአድማው ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ በጎረቤት ሃገር ከተሞች ጭምር ሳይቀር መታይቱን ገምግመናል። ስለሆነም የአድማው ውጤት በሶስተኛው ቀን አጥጋቢና በ5ኛው ቀን ይጠበቅ ከነበረው ውጤትም በላይ ሆኖ በመገኘቱ፣ በዚሁ በ3ኛው ቀን በተደረገው ግምገማ መርሃ ግብሩን መከለስ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ መሰረት ከላይ እንደተገለጸው ከታለመው አንጻር ጊዜው ሳይጠናቀቅ በቂና አጥጋቢ ውጤት የተገኘ በመሆኑ ምክኒያት ዛሬ አድማው ከተጀመረ በ3ኛው ቀን እንዲያበቃ የቄሮ አስተባባሪዎች ወስነዋል። ስለሆነም የቤት ውስጥ መቀመጥና የግብይት አድማው ከዛሬ ነሃሴ 25, 2017 አመሻሽ ጀምሮ ያበቃል ማለት ነው።

ይሄን ዘምቻ ዛሬ ላይ ስናቆም ለጨቋኙ ስርዓትም ሆነ የኦሮሞን ህዝብ ትግል በማጠልሸት ጊዜአቸውን ሲያጠፉ ለሚዉሉት ሁላ ግን መልዕክት አለን። ይኻውም የዚህ ትውልድ የኦሮሞ ብሄርተኞች የህዝብ ጠላቶችን ድርጊት በሚመጥንና ብሎም ጠላቶቹን በሚያንኮታኩት መልኩ የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስዱ መታወቅ አለበት። የፖለቲካ መሪዎቻችን የሆኑትን እነ ዶ/ር መረራ ጉዲናና በቀለ ገርባ እንዲሁም ሌሎችን በደባባይ ለማዋረድና ለማሸማቀቅ በስርዓቱ አገልጋዮች እየተደረገ ያለው ብልግና ትልቅ ንዴትና ቁጭት እንደፈጠርብን ለመግለጽ እንፈልጋለን። በተጨማሪም በምስራቅም ሆነ በምዕራብ፤ በደቡብም ሆነ በሰሜን ወይም በመሃል ባለው የኦሮሞ ሃገርና መሬት ላይ የሚደረግ ማንኛውንም ወረራ እንደማንታገስ በድጋሚ እናረጋግጣለን።

ህወሃት መራሹ መንግስት የታጠቁ ነፍሰ ገዳይ ልዩ ፖሊስ አሰማርቶ የምስራቁን የኦሮሚያ አካባቢዎች እንዲወር የሚያደርገውን አደገኛ አካሄድ እንደማንታገሰው በድጋሚ እናስገነዝባለን። ስርዓቱ የኦሮሞ የቢዝነስ ሰዎችን ለማክሰር እንዲሁም በጥቃቅንና አነስተኛ ስራዎች ላይ የተሰማሩትንና ውጤታማ እየሆኑ ያሉ የኦሮሞ ልጆችን ለማክሰም የሚያደርገውን መሰሪ ጥረትም እንደማንታገስ መግለጽ እንወዳለን።

በመጨረሻም፣
የኦሮሞ ህዝብ ይሄንን ስኬታማ የአድማ ማድረግ ዘመቻ ነባሮቹን የኦሮም ህዝብ ፍላጎቶችና ጥያቄዎች ለማሳካት ይበልጥ ያለንን ጽናት የገለጽንበት አንድ አጋጣሚ መሆኑን ማወቅ አለበት። የኦሮሞ ትግል ህዝቡ የራሱን ሃብት ራሱ መቆጣጣአር እስኪችል፣ እንዲሁም የወልና የግል ማንነቱን ሙሉ በሙሉ ማስከበር እስኪችል ድረስ በጽናት የሚቀጥል መሆኑን ማስታወቅ እንፈልጋለን። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ተቃውሞ በማድረጋቸው ብቻ የተገደሉት ውድ የኦሮሞ ልጆች የሞቱት የትግራዩ ነጽ አውጪ ቡድን ለራሱ ግልጋሎት ብሎ ጠፍጥፎ የሰራቸው ጀሌዎች በውሸት ትርክት የኦሮሞ ብሄርተኝነት ወራሽ መስለው በመቅረብ የኦሮሚያን አስተዳደር መልሰው በመቀጣጠር ወያኔ ስር ለማስገባት አለመሆኑ መታወቅ አለበት። የኦሮሞ ትግል ግቡን የሚመታው ህዝቡ ራሱ በመረጣቸው መሪዎቹ አማካይነት መተዳደር ሲጀመርና ፊንፊኔን ጨምሮ ሁሉም የኦሮሚያ አካባቢዎች ከህዝቡ በወጣ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ስር ሲዋቀሩ ነው። ኦሮሚያ ውስጥ ኢንቬስት ማድረግ የሚፈልጉ ባለሃብቶችም ኢንቨስትሜንታቸው ህጋዊ፣ ከሙስና የጸዳና የባላገሩን ኑሮ በማያመሰቃቅል መልኩ ከሆነ ሁላችንም እንደምናበረታታቸውም መግለጽ እንፈልጋለን። እኛ ቄሮዎች ለስርዓቱ ያደሩ ሊህቃንና ሙሰኞች የቁቤ ቅደም ተከተል ለማዛባት ያደረጉትን ከንቱ ጥረት እንደምናወግዝና በቅርቡ በኦሮሞ ምሁራን ጥናት መሰረት ይሄን መሰሪ አካሄድ ለመቀልበስ የተላለፈውን ውሳኔ እንደምንደግፍ እንገልጻለን።
የኦሮሞ የመብትና የሃገር ባለቤትነት ትግል በላቀ ቁርጠኝነትና ጽናት እንዲሁም ቅልጥፍና ይቀጥላል።

ድል ለኦሮሞ ህዝብ
ኦሮሞ ቄሮ

8 Comments

 1. JAWAR cancelled the protest before the protest ended miserably, he knows a lot of businesses will be opening tomorrow and he forced to take this drastic measure before the protest ended embarrassingly

 2. ትርጉም የሌለው የጥቅት የኦሮሞ ፓለቲከኞች ግቡን ሳይመታ እንዲኮላሽ የተደረገ እቅድ ነው!
  ይህ ሆን ተብሎ ትግሉ እንዲኮላሽ መደረጉንና ለአምስት ቀን የተጠራውን ዘመቻ ምንም ዓይነት ግብ ሳይኖረው የተወሰኑ እስረኞችን እንኳን አገዛዙን በማስጨነቅ ሳይፈቱ በድንገት እንዲቆም በአንድ ወገን የተቀለበሰ አሳዛኝ ትግል ነው!
  ከዚያ ውጭ የመግለጫው መንፈስ ሁሉ ኢትዬጵያዊነት የለውም መላው አገሪቱ ህዝቦች ትግሉን ተቀላቅለው አገራዊ ትግል ሆኖ እንዳይቀጥልም ሚና አለው ምክንያቱም የራስን ዕድል በራስ መወሰን የሚል ጠባብነትን እንጂ ይህንን ስርዕልት በማስወገድ ዲሞክራሲያዊት ኢትዬጵያን ስለመመስረት የሚገልፅ ነገር በመግለጫው ውስጥ የለም ” ኢትዬጵያ የሚል ሃረግ ፈጽሞም የለበትም ስለሆነም ትግሉ አራዊ መናበብ እንዳይኖርና የኦሮሞን ህዝብ ትግል የሚጠልፍና ወደ ድልም ፈጽሞ የማይወስድ ወይም በቄሮዎች ስም በእነ ጅዋርና መሰሎቹ እየተነዳ ያለ ትግል ነው! ለማንኛውም የሚገርም ዓይነት ከብዥታ የፀዳ እቅድና ግብ የሌለው ትግል ነው።

 3. ቄሮ ብትለው ቆርቆሮ ብትለው ምንም ትርጉም የሌለው ድሃውን የህብረተሰብ ክፍል የሚጎዳ የህጻን እርምጃ ነው የተወሰደው። የጎዱት የራሳቸውን ቤተሰብና ነጋዴ ጎረቤቶቻቸውን መሆኑን አይተው ይሆናል አቋርጠናል ያሉት። አሜሪካ ያለችግር ተቀምጦ ሃገር ቤት ያሉትን ወገኖቻችንን ወደ እሳት የሚልከው ጃዋር የተባለው ህጻን ስለ ጉራጌዎች የተናገረውን ሰምተናል። ጉራጌን አስጨፍጭፈህ ኦሮሞን ነጻ ልታወጣ ነው?የዚህ የጂኖሳይድ ቅስቀሳህ በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ተመዝግቦልሃል። አፍሪካ ውስጥ ሌላ ጂኖሳይድ እንድታስነሳ አይፈቀድልህም። ጉራጌን ከማስጨፍጨፍህ በፊት ባለህበት ተጨፈጨፋለህ!!

 4. kero 2 ayinet new ende? andu Jawar weyanew yemimeraw lelaw ewnetegnochu ye Oromo lijoch yemimerut ? yahunu adma yeJawar new? be Oromo lijoch dem keberebet yihe achiberbari yezihen sew maninent minew mawek tesanen yasazinal

 5. It seems like our Qerro brother have missed the point once again. the urgency of the time and the mischievous nature of the regime calls for total unity… without which the freedom effort won’t progress.

  Jawars word about the Gurrages was as damaging as Finfinnes issue. Addis Ababa is everybody’s home. No one ethnic group can claim it. there are over 15 million trans-ethnic people to protect it with their blood and bones. No fake history can change that… be you Oromo woyanne or Tigre woyanne.

  Woyanne can be conquered by one thing………unity, only unity, nothing but unity…

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.