አትሌት ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ የክብር ዶክትሬት አገኙ

Filed under: News Feature,ስፖርት,የዕለቱ ዜናዎች |

ከሰለሞን ገብረ መድህን

ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ ለአንጋፋው አትሌት ሻለቃ ባሻ ዋሚ ቢራቱ በአትሌቲክሱ ዘርፍ ላበረከቱት ጉልህ አስተዋፅፆ የክብር ዶክትሬት ሰጠ።

የክብር ዶክትሬቱን ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ለማ መገርሳ እጅ ተቀብለዋል።

ዋሚ ቢራቱ በተወዳደሩባቸው የማራቶንና የረጅም ርቀት ሩጫዎች 80 ሜዳልያ ማግኘት ችለዋል ከዚህ ውስጥ 30 ወርቅ ሲሆን፥ 40 የብር እንዲሁም 10 የነሃስ ሜዳልያዎችን አሸንፈዋል።

አበበ ቢቂላ በሮም ላይ በባዶ እግሩ ማራቶንን ሲዘንጥባት ጨርሶም ዱብዱብ ሲሰራ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ጨምሮ ህዝቡ አጃኢብ ሲልለት ነበር ግን ሚዲያዎቹን እጃቸውን በአፋቸው ያስጫናቸው ጉዳይ ለጠየቁት የሰጠው መልስ ነበር በባዶ እግሩ ሮጦ ባሸናፊነት ወርቁን ያጠለቀው አበበ ቢቂላ ‹‹እኔ የዓለም አንደኛ የኢትዮጵያ ግን ሁለተኛ ነኝ፡፡ አንደኛው በመታመሙ አልመጣም፤›› በማለት የዋሚ ቢራቱን ታላቅ ሯጭነት መመስከሩ በወቅቱ ተመዝግቧል፡፡ ከርሱም የባስ ትንታግ አለ ማለት ነው ሲሉ ገርሟቸዋል ያን ጀግና ለማየት የጓጉም ይመስለኛል አበበ እንዲህ የተናገረላቸው ጀግና ሻምበል ባሻ ዋሚ ቢራቱ ናቸው!!

በወቅቱ የነበሩት ሲውድናዊው አሰልጣኝ ለሮሙ ኦሎምፒክ የተመረጡት አትሌት ዋሚን ነበር በቢሾፍቱ የነበራቸውን ስልጠና ጨርሰው ሲመለሱ አትሌት ዋሚ ታመሙ መሄድ እንደማይችሉም ተነገራቸው በዚህ አጋጣሚ ነበር አበበ ቢቂላ የተጠራው የታሪክ ባለቤትም የሆነው!

አንጋፋው የብስክሌት ተወዳዳሪ ገረመው ደንቦባም ይህን ያረጋግጣል “በኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ውድድር ላይ ማንም ሰው ተከትሎት አይገባም ነበር… ቁመናው፣ ጥንካሬው፣ ብርታቱ፣ ሁሉ ነገሩ ለሩጫ የተፈጠረ ነው… የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቀውንና እንዲህ በአድናቆት የሚመለከተውን ሩጫ በሚገባ ያስተዋወቀ ዋሚ ነው… በየቀኑ ከሱሉልታ አዲስ አበባ ጠዋትና ማታ ይሮጥ ነበር…. “

በ1909 በሱሉልታ የተወለዱት ሻምበል ባሻ ዋሚ ቢራቱ 100ኛ ዓመት ላይ ይገኛሉ!
እረጅም እድሜ ለ ሻምበል ባሻ ዋሚ ቢራቱ!

አቶ ዲንቁ ደያስ ለታላቁ ሰው የሚመጥን ክብር በመስጠትዎ ክብር ይገባዎታል!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.