የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ክለብ የወንዶቹን፣ የዋናውን የተስፋ ቡድኑንና የታዳጊ ቡድኑን ማፍረሱን ይፋ አደረገ

Filed under: News Feature,ስፖርት |

ሃትሪክ የተሰኘው በሃገር ቤት የሚታተመው የስፖርት ጋዜጣ እንዳስነበበው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስፖርት ክለብ በኢትዮጵያ ሆቴል ዛሬ በጠራው ጋዜጣዊ መግለጫ የወንዶቹን የዋናውን የተስፋ ቡድኑንና የታዳጊ ቡድኑን ማፍረሱን የድርጅቱ ምክትልና የስፖርት ማህበሩ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ሰይፉ ቦጋለ ለመገናኛ ብዙሀን ሊያሳውቁ ችለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን የወንዶች ቡድኑን በዛሬው እለት ለማፍረስ በምክንያትነት ያቀረበው ቡድኑ ከሚመድበው በጀት አኳያ ባለፉት ስድስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የቡድኑ ውጤት ያሽቆለቆለና መሻሻልም ያላሳየ በመሆኑ ለመፍረሱ ምክንያት ሲሆን እንደዚሁም ከስር ያሉ ወጣት ተጨዋቾችንም የክለቡ ባለሙያዎች አሳድገው ለማጫወት ፍላጎት የሌላቸው በመሆኑና ልጆቹም ተቀምጠው የሚሰሩት ነገር ስለሌለ ተተኪው ቡድን ሊፈርስ እንደቻለ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች ዋናውንና የተስፋ ቡድኑን ማፍረሱን ይፋ ባደረገበት ቀን የሴቶች ቡድኑን ይዞ እንደሚወዳደር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች የዋናውን የተስፋውንና የታዳጊ ቡድኑ ማፍረሱን ካሳወቀ በኋላ ውሳኔው ብዙዎቹን አስደንግጧል፤ አሳዝኗልም።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2009 የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ በ30 ጨዋታዎች በ-11የግብ እዳ በ31 ነጥብ ወደታችኛው ሊግ መውረዱ እሚታወስ ነው፡፡

ቀድሞ አጠራር ኢትዮጵያ ባንኮች በአሁኑ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እሚጠራው ክለቡ ታሪካዊ ዳራውን እንመለከት
በቀድሞ አጠራሩ ኢትዮጵያ ባንኮች ስፖርት ክለብ በሰባት ባንኮች  ባለቤትነት የሚተዳደር የስፖርት ክለብ ነው፡፡ በእግር ኳሱ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እየተሳተፈ ሲሆን በጥሎ ማለፍ ሻምፒዮን ባመጣው ውጤት ሁለት ጊዜ በአፍሪካ ኮንፌዴርሽን ዋንጫ የመሣተፍ እድል አግኝቷል፡፡

የክለቡ ምስረታ
ኢትዮጵያ ባንኮች ስፖርት ክለብ የተመሰረተው በ 1975 ዓ/ም በአራት ባንኮች ባለቤትነት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ንግድ ባንክ፣ ልማት ባንክ እና ኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ናቸው፡፡ በወቅቱ በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ ባንኮች እነዚህ ብቻ ነበሩ በ 1995 ዓ/ም በአዲስ መልክ ሲጠናከር ሦስት የግል ባንኮች ድጋፍ በማድረግ ተቀላቀሉ፡፡ ወጋገን፣ ንብ እና አዋሽ ባንክ ናቸው እናም በአሁኑ ወቅት ሠባት ባንኮች በሚያዋጡት ገንዘብ የሚቀሳቀስ ስፖርት ክለብ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ባንኮች ከምስረታው በኃላ በኢትዮጵያ ሻምፒዮና ላይ ተሳትፏል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲጀመርም ከሊጉ መስራች ክለቦች አንዱ ነው፡፡ እስካሁን ወደ ታችኛው ዲቪዚዬን አልወረደም ዋንጫም አላነሳም ከ 1992-1994 በተከታታይ ለሦስት አመታት አራተኛ ደረጃን ያገኘበት ውጤት የሊጉ የተሻለው ሆኖ ተመዝግቦለታል፡፡
በጥሎ ማለፍ ደግሞ የተሻለ ሪከርድ አለው፡፡ በ 1996 ኢትዮጵያ ቡናን 1ለ0 በማሸነፍ የጥሎ ማለፍ ሻምፒዮን ሆነ፡፡ በአሸፊዎች አሸናፊ ዋንጫም የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን የነበረውን ሀዋሳ ከነማን ለማሸነፍ ሁለተኛ ዋንጫ አግኝቷል፡፡ በ 2001 ዓ/ም በጥሎ ማለፉ ለፍፃሜ ደርሶ በቅዱስ ጊዮርጊስ ተሸንፎ ዋንጫ ቢያጣም የሚያፅናናው ነገር አግኝቶ ነበር፡፡ ቅ/ጊዮርጊስ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን በመሆኑ በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ይሳተፍ ነበር፡፡ እናም በኮንፈዴሬሽን ዋንጫ የመሳተፍ እድሉ ለፍፃሜ ተፋላሚው ባንኮች ተሰጥቷል፡፡

ባንኮች በኢንተርናሽናል 

ኢትዮጵያ ባንኮች ሁለት ጊዜ በአፍሪካ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ የመሣተፍ እድል አግኝቷል፡፡ የመጀመሪያው 1998 [2005] ነው በመጀመሪያው ዙር ከኬንያው ሼሚልል ሹገር ጋር ቢገናኝም ተጋጣሚው ራሱን በማግለሉ ወደ መጀመሪያው ዙር ያልፋል በአንደኛው ዙር ከግብፅ ሞካውሉን ጋር የተገናኘ ሲሆን አዲስ አበባ ላይ ያለ ግብ ተለያይቶ ግብፅ ላይ 3 ለ 1 ተሸንፎ ከውድድሩ ተሰናብቷል፡፡ ሁለተኛው የተሳትፎ እድል ያገኘው በ 2002 ዓ/ም ነው፡፡ በቅድመ ማጣሪያው ከኬንያው ሊያፓርድ ጋር ተገናኘ ናይሮቢ ላይ 3 ለ 1 ተሸንፎ ቢመለስም አዲስ አበባ ላይ 3 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል፡፡ በአንደኛው ዙር ከግብፅ ሀራስ ኤልሀዱድ አልሃዲድ ጋር ተገናኘ፡፡ አዲስ አበባ ላይ አንድ አቻ ከተለያዩ በኃላ በአሌክሳንደሪያው የመልስ ጨዋታ ግን ያልታሰበ ሽንፈት ደረሰብ 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ተሸንፎ ከውድድሩ ውጭ ሆኗል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.