/

በጣሊያኑ የባህር አደጋ የሞቱት የኢትዮጵያውያን እና የኤርትራውያን ጉዳይ

1 min read

italyሰሞኑን ከሊቢያ ተነስተው በጣሊያን ባህር አቅራቢያ ባህር ውስጥ ጠልቀው ከሞቱት ወገኖች ውስጥ በተለያዩ ሚዲያዎች የኤርትራ ስደተኞች ብቻ እንደሞቱ እየተዘገበ ነው። ዘ-ሐበሻ ግን የኤርትራ ስደተኞች መባሉን አታምንብተም። የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሔኖክ ዓለማየሁ በሊቢያ ስደት ውስጥ ያሳለፈ በመሆኑና ወደጣሊያንም በባህር ለመሻገር ሞክሮ በእስር ምክንያት ሕይወቱ በመትረፉ ዛሬ የኤርትራ ስደተኞች ብቻ ሕይወታቸው እንዳለፈ ተደርጎ መወራቱን አይቀበለውም። በሊቢያ ቤንጋዚ፣ ትሪፖሊ፣ ኩፍራ፣ ኢጅዳቢያና ሌሎችም እስር ቤቶች በርካታ ከምስራቅ አፍሪካ ወደ ጣሊያን ለመሰደድ ሄደው የታሰሩ ሰዎች ከዘ-ሐበሻ አዘጋጅ ጋር የታሰሩ ነበሩ። እነዚህ ዜጎች በተለይም ኢትዮጵያውያኑ እስር ቤት ሲገቡ ዜግነታቸውን ‘ኤርትራዊ እንደሆኑ እንዲናገሩ” አሻጋሪዎች ይነግሯቸዋል። ምክንያታቸውም የሊቢያ መንግስት እስር ቤት ውስጥ ኢትዮጵያዊ ነኝ ያለን ወደ አዲስ አበባ ስለሚሸኘው፤ ኤርትራዊ ነኝ የሚል ግን ወደ አስመራ ስለማይላክ ሁሉም ኢትዮጵያዊም ኤርትራዊም “ኤርትራዊ ነኝ” ብሎ ነው የሚገልጸው። አሁንም የሆነው ያ ነው። ኤርትራዊያን ናቸው ከተባሉት ውስጥ አብዛኛው ኢትዮጵያውያንም ጭምር ናቸው በሚል ዘ-ሐበሻ ታምናለች።
የሞቱትን ነብሳቸውን ይማረው፡:

10 Comments

  1. yenante emnet yemotuten yasenesa yimesel . . . Tsinf atyazu. Eriterianem bihonu yegna lijoch nachew. Kezegnet befit sewunet yikedmal.

  2. @Ze-habesha,
    Why do you rush to conclude that the majority (I am not saying any one) of these are Ethiopian? We all know each of them have father, mother sister brother some where and it would be easy to know if anyone (let alone the majority) is Ethiopian when we start to hear about the mourning family members.

    Unprofessional to say the least!

  3. I agree with the Habesha comment. I have been working in Libya in 2011 and many Ethiopians claiming as Eritreans to be accepted by the UNHCR refugee’s agency as asylum seeker during registration. In any case it is so sad to hear this horrible tragedy. The Eritrean and the Ethiopian governments are responsible for such tragedy and massacre. Qacahw.

  4. Aye Yehabesha neger! Ze habesha had never slept to tell us that they are Ethiopians.To argue this check their ID or passport. Otherwise to judge by name is not sceintific but still Habesha methode.Any who ever is the victim we feel deep sorrow.And RIP. Ye Ze Habesha neger gin yaw Tire Habesha new.U should know that Flamini and Platini-despite sounds Italiano are French people.

  5. “ባጠቃላይ ቁጥራቸው 518 ሲሆን 7 ኢትዮጵያውያን 511 ኤርትራውያን ሲሆኑ 16 ልጆች እና ህጻናት ነበሩ” ምንጭ ከተራፊዎቹ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.