የመሃመድ አሊ ለጭቁኖች መቆምና እኛ!

Filed under: ስፖርት |

በቶማስ ሰብስቤ

የአለም ቁጥር አንድ ቦክሰኛው መሃመድ አሊ በስፖርት ፖለቲካ የሚጠራ ትልቅ ስብዕና ያለው ግለሰብ ነበር።

አሜሪካ በቬትነሃም ላይ የከፈተችውን ጦርነት በይፋ የተቃወመ ፣በእስላሞች ላይ የነበረው Islamophobia በአደባባይ ሲቃወም በስፖርት ፖለቲካ አይቻልም ብለው ቢተቹትም ሰፖርት ሰበዓዊ ፍጡር ላይ የሚደረግ የተኛውም ግፍ እንዳይቃወም ያላደረገው ጀግና መሆኑን አሳይቷል።

አሜሪካ በቬትነሃም ላይ የወሰደችውን ጦርንት በመተቸቱና ከጭቁኖች ጎን በመሰለፉ ሀገሪቷ ከስፖርት እንቅስቃሴው አግዳው እንደነበር ይታወሳል።እገዳው ግን ለህዝብ መቆሙን አላስቆመውም።

Muhammad Ali after first round knockout of Sonny Liston during World Heavyweight Title fight at St. Dominic’s Arena in Lewiston, Maine on 5/25/1965.
(Item # 1001)

መሃመድ አሊ በዝነኛው መድረክ ለጥቁሮችና ለተጨቆኑ መቆሙን ያሳየው ስፖርትና ፖለቲካ ለየቅል መሆኑን ሳያውቅ አይደለም።መሃመድን እንዲናገር ያደረገው ጭቆና ፣ ግፋና መከራው ከገደብ በላይ ሰላለፈ ነው።

በሀገራችንም ባለፉት አመታት የነፃነት ውስንንት ፣ ፍትህ ማጣትና እኩልነት በተለያዮ ህዝቦች መካካል መጥፋቱ ህዝቡ በየትኛውም አጋጣሚ ብሶቱን በአደባባይ እንዲያሳይ አድርጎታል።

የስፖርት ቦታዎችም እነዚህ ቦታዎች አንዱ ነው።በመጀመሪያ አጀማመሩ በሀገሩቱ ከተዘረጋው የዘር ፖለቲካ ጣጣ ካመጣው የጎሰኝነት ድጋፋ ጋር የተያያዘ ነበር፤ በአብነትም በብሄር መሰዳደብ ና መደባደብ ላይ ነበር መሰረት ያደረገው።

በቅርብ ጊዜያት ግን የገዥው መንግስት ላይ ያነጣጠረ ሆነዋል።ህውሃት ኢህአዴግን የዘረጋው ጭቆና ይቁምና በቃን ከሚባሉበት ቦታ ስፖርት ቀዳሚ ነው።

በክልል ክለቦች መካካል በሚደረጉ ጨዋታዎች የሚፈጠሩ ግጭቶች ዋና ማጠንጠኛው መንግስት መቃመውና በቃኝ ነው።

የትኛውም የስፖርት ደጋፊ የስፖርት ጨዋነት ቢያውቅም ፣ስፖርትና ፖለቲካ መለያየቱን ቢረዳም ጭቆናው መብዛቱ ልክ እንደ መሃመድ አሊ አድርጎታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.