የአብርሃ ደስታ በፌስቡክ ላይ የተለቀቁ ምርጥ የሳምንቱ ጽህፎች

1 min read

ከዉቅሮ የደረሰኝ መረጃ

Abrham Destaባለፈው ቅዳሜ ዓረና ፓርቲ በዉቅሮ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ማድረጉ ይታወሳል። ይህን ተከትሎ ህወሓቶች ትናንት እሁድ በዉቅሮ ሰለማዊ ሰልፍ መጥራታቸው ይታወቃል። ዛሬ ሰኞ ደግሞ ለዉቅሮ ህዝብ (በህወሓት ዘመን ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ) ፊኖ፣ ስንዴ፣ ሱኳርና ዘይት እንደጉድ እያደሉ ይገኛሉ።

በዉቅሮ ከተማ ለህዝብ ፊኖ ዱቄትና ዘይት ለህዝብ ሲታደል የማስታውሰው በደርግ ግዜ ነበር። ደርጎች የትግራይን ህዝብ ወንበዴዎችን እያገዘ ሲያስቸግራቸው በሆዱ ለመደለል ፊኖና የምግብ ዘይት ያድሉት ነበር። ግን አልተሳካላቸውም፤ ምክንያቱም ሰው (ምግብ ማግኘቱ ጥሩ ቢሆንም) ለዓላማ እንጂ ለሆዱ አይኖርም። የትግራይ ህዝብም በሆዱ አልተገዛም። የትግራይ ህዝብ ብዙ መስዋእት የከፈለበትን ትግል በግለሰቦች ተጠልፎ የነፃነት ዒላማው ስቶ ለስልጣን ቢውልም በምግብ ተሸውዶ ትግሉ አላቋረጠም።

ህወሓቶችም ከደርግ ጋር ተመሳሰሉብኝ። የዉቅሮ ህዝብ ከመቼ ጀምሮ ነው ፊኖና ዘይት የሚታደለው? ይህ የፈራ መንግስት ምልክት ነው። ግን ጥሩ ነው። ዓረና ትናንት በዉቅሮ ከተማ ስለተንቀሳቀስን ዛሬ ምግብ እየታደለ ነው።

እንቅስቃሲያችን እንዲህ ዉጤታማ ከሆነ ወደ ሁሉም የትግራይ ወረዳዎች በተመሳሳይ መልኩ መንቀሳቀስ አለብን ማለት ነው። ህዝቡ የፊኖ ዱቄትና የምግብ ዘይት (የደርግ ዓይነቱ) እንዲሰጠው።

 

ትንሽ ስለ ዳዊት ከበደ

ይድረስ የዳዊትና የአብርሃ ጉዳይ ለምታመሳስሉ

የአውራምባታይምስ ጋዜጣ ኢዲተር ዳዊት ከበደ ከስደት ኑሮ ወደ ሀገሩ ተመልሷል አሉ (ከፌስቡክ ሰማሁ)። ዳዊት ለስደት የተዳረገው በምን ምክንያት ነበር? በኢትዮዽያ ዉስጥ መስራት አስቸጋሪ ስለሆነበት ነው ? ወይስ የዉጭ ሀገር ህይወት ስላማረው ነው? ተገቢ መልስ ያስፈልገዋል። ላሁን ግን የተባለውና የሰማነው እንውሰድ። ዳዊት ከሀገሩ የተሰደደው የኢህአዴግ መንግስት አላሰራ ስላለው ነው።

መንግስት አላሰራ ሲለው ከሀገር መውጣቱ ተገቢ ሊሆን ይችላል። ያኔ የመንግስትን ዓፈና ፈርቶ ወጣ፤ አሁን ደግሞ በሆነ ምክንያት (ወደ ሀገሩ የተመለሰበት ትክክለኛ ምክንያት በትክክል ስለማላውቅ ነው) ወደ ሀገሩ ተመለሰ። ስለዚህ መሄዱም ትክክል ነው፣ መመለሱም ትክክል ነው። ምክንያቱም ይህ ጉዳይ የሚወሰነው በራሱ በዳዊት ነው። ከሀገር የወጣበትና ተመልሶ የገባበት የራሱ ምክንያት ይኖረዋል ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ ዳዊቶም እንኳን በደህና መጣህ።

ስለ ዳዊት ጉዳይ ለመፃፍ የተገደድኩበት ምክንያት “አብርሃ ደስታስ ከዳዊት ከበደ ምን ይማራል?” የሚል ሐሳብ ስለተነሳ ነው። ስለዚህ የዚህ ፅሑፍ ዋና ቁምነገር ስለ ዳዊት ከበደ ሳይሆን በተዘዋዋሪ ስለ አብርሃ ደስታ ነው።

ዳዊት ኢትዮዽያ ዉስጥ እያለ ገዢውን ፓርቲ የሚተቹ ፅሑፎች በማሳተም ይታወቃል። በንዲህ ዓይነት ፅሑፍ ከቅንጅት መሪዎች ጋር ለእስር ተዳርጎ እንደነበር የሚታወስ ነው። እንደሰማነው መንግስት ስጋት ስለፈጠረበት ከሀገር ወጣ። እስካሁን የሰራው ጥፋት የለም። ከሀገር ከወጣ በኋላ ዳያስፖራ ተቃዋሚዎች ሞቅ ያለ አቀባበል አደረጉለት። አሁንም ችግር የለውም። ምክንያቱም ኢህአዴግን ለሚተች ሰው አቀባበል ማድረግ ምን ይደንቃል?! ምክንያቱም እነሱም ተቃዋሚዎች ናቸው።

ከተወሰነ ግዜ በኋላ ዳዊት ከዳያስፖራ ተቃዋሚዎች ተጣላ። ዳያስፖራው ዳዊትን ለማጥላላት ሞከረ። ዳዊትም ስለነሱ መጥፎነት ነገረን። ከዛ ዳዊት “ዓቋሜን እንደገና ለመፈተሽ ተገድጃለሁ” ብሎ ወደ ሌላኛው ጎራ አዘነበለ። ወደ ሀገሩ ገባ። “ዳዊት ከኢህአዴግ ጋር ታርቋል” የሚል ጥርጣሬ መጣ (ከተቃዋሚዎች)። “ከኢህአዴግ ጋር ታርቋል” የተባለበት ምክንያት የተቃዋሚ መሪዎች መተቸት ስለጀመረ ነው (ምክንያቱም ዳዊት ከኢህ አዴግ ሲታረቅ ወይ ሲፋታ አላየንም)። ቀጥሎም ዳዊት አቋሙ የቀየረበትና ወደ ሀገሩ ለመግባት የወሰነበት ምክንያት ዳያስፖራ ተቃዋሚዎች ብሄር ተኮር (የትግራይ ተወላጅ በመሆኑ) የሆነ የማጥላላት ዘመቻ ስለከፈቱበት ነው ተባለ (በትግራይ ተወላጆች)።

ብዙ የትግራይ ተወላጆች እንደሚገምቱት ዳዊት ከበደ ከሀገር ሲወጣ “የጀግና አቀባበል” ያደረጉለት ለራሳቸው ስለሚጠቅማቸው ነው። በኋላ እነሱን በአሉታ የሚነካ ሐሳብ ሲያነሳ ግን ብሄሩን ጠቅሰው ማጥላላት ጀመሩ። ስለዚህ እነሱ የሚያመኳሹት ሰው ለራሳቸው ዓላማ ለማሳካት የሚረዳቸው ሰው ብቻ ነው። ከተጠቁሙት በኋላ ያጥላሉታል ወዘተ ብለው ያስባሉ።

ከዚህ ተነስተው የአብርሃ ደስታ ነገር ከዳዊት ከበደ ጉዳይ ያገናኙና “አብርሃም ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ ይደርሰዋል” ብለው ያስባሉ። አብርሃ ደስታ ከዳዊት ከበደ መማር እንዳለበትም ይመክራሉ። በዚህ ጉዳይ አስተያየት ልስጥ።

በመጀምርያ ዳዊት ከበደ ጋዜጠኛ ነው። የኢህአዴግ መንግስት ለነፃ ጋዜጠኞች እንደማይመችና ብዙ ችግር እንደሚያደርስ እናውቃለን። ስለዚህ ዳዊት ከሀገሩ ሲሰደድ ምክንያት አለው። ዳያስፖራ ተቃዋሚዎችም ይህን የጋዜጠኞች የሀገር ዉስጥ ችግር ተረድተው ለዳዊት ጥሩ አቀባበል ማድረጋቸው ሊመሰገኑ ይገባል። ምክንያቱም ስደት ከባድ ነው፤ ወገኖቻችንን መተባበር አለብን።

ዳያስፖራ ተቃዋሚዎች የዘነጉት ነገር ግን አለ። ዳዊት ከበደ ጋዜጠኛ እንጂ የተቃዋሚ ፖለቲከኛ አይደለም። አንድ ጋዜጠኛ ያገኘውን መረጃ ቢጋለጥ ለህዝብ ይጠቅማል ብሎ ያመነበትን ማንኛውም ነገር ለህዝብ የማድረስ መብትም ግዴታም አለበት። ጋዜጠኛ ገዢውን ፓርቲ የሚተች ወይም የሚያወድስ ነገር ሊፅፍ ይችላል። አንድ ጋዜጠኛ ገዢውን ፓርቲ ስለነቀፈ የተቃዋሚዎች ደጋፊ ነው መባል የለበትም። ተቃዋሚዎች ስለነቀፈም የገዢው ፓርቲ ሰላይ ነው ማለት የለብንም። አንድ ገለልተኛ ጋዜጠኛ መወቀስ ያለበትን ይወቅሳል (ገዢውም ተቃዋሚውም)።

እኛን ሲያወድስ እውነተኛ ጋዜጠኛ፣ እኛን ሲተች ደግሞ ቅጥረኛ ሰላይ … የምንለው ከሆነ ስለ ጋዜጠኝነት ያለን ግንዛቤ ዝቅተኛ ነው ማለት ነው። ዳዊት ኢትዮዽያ ዉስጥ እያለ ብልሹ ያለውን የኢህአዴግን አሰራር ያጋልጥ ነበር። ዉጭ ሲሄድ ደግሞ ብልሹ ያለውን የዳያስፖራ ተቃዋሚዎችን አሰራር ቢያጋልጥ ምንድነው ችግሩ? ስለዚህ ጋዜጠኛ እስከሆነ ድረስ የፈለገውን የመፃፍ መብቱ ሊከበርለት ይገባል። በዳዊት ላይ የተፈፀመ የማጥላላት ዘመቻም ትክክል አይደለም።

ወደ ዳዊት ልመለስ። ዳዊት ጋዜጠኛ ነው ብለናል። ጋዜጠኛ ከሆነ ታድያ ለምን በዳያስፖራዎች የማጥላላት ዘመቻ ተሸበረ? ዳያስፖራዎች ሲነቅፉት ለምን ሌላኛው ጥግ ያዘ? ጋዜጠኛ ከሆነ ለምን “አቋሜን ለመፈተሽ ተገድጃለሁ” አለ? የትኛው አቋሙ ነው የሚፈትሸው? የፖለቲካ አቋም አለው ወይ ነበረው ማለት ነው? የአንድ ጋዜጠኛ አቋም የጋዜጠኝነት ሙያ ማክበር ነው መሆን ያለበት። ሌላ ሊፈተሽ ወይ ሊቀየር የሚችል አቋም ካለው እሱ ጋዜጠኛ ሳይሆን ፖለቲከኛ መሆን አለበት። ጋዜጠኛ ሁኖ ሳለ “አቋሜን ለመፈተሽ ተገድጃለሁ” ካለ “ጋዜጠኛነቱን አቆማለሁ” እያለን መሆን አለበት።

ፖለቲከኛ መሆንም ችግር የለውም። ግን የጋዜጠኛ ፖለቲከኛ ሁኖ ሲሰራም ዳያስፖራዎች ከተጠራጠሩት በኋላ እንደገና ለመፈተሽ የፈለገው አቋሙ ምንድነው? ዳያስፖራዎች ባያጣጥሉትና ባይጠራጠሩት ኑሮ እንደገና የማይፈት ሸው አቋሙ ምንድነው? ዳዊት በዳያስፖራዎች መጠራጠርና ማጥላላት ከተከፋ አቋሙ ወይ ዓላማው እነዚህ ዳያስፖራ ተቃዋሚዎች ለማስደሰት ነበር ማለት ነው። ተቃዋሚዎች ወይ ደጋፎዎች ወይ ሌሎች ለማስደሰት ተብሎ የሚሰራ ማንኛውም ተግባር ዉጤቱ መከፋት ነው የሚሆነው።

ዳዊት ዳያስፖራ ተቃዋሚዎችን የማስደሰት አቋም ወይ ዓላማ ይዞ ባይንቀሳቀስ ኑሮ በእርግጠኝነት ዳያስፖራዎች በሰሩበት ነገር ይህን ያህል ባልተከፋ ነበር። ምክንያቱም ዓላማው ሌሎችን ማስደሰት ወይ ማስከፋት ባይሆን ኑሮ በሰዎች አስተያየት ወይ አመለካከት እንዲህ ዓይነት ሌላኛው ጥግ የሚያስይዝና አቋም የሚያስቀይር ተግባር ባልሰራ ነበር። አንድ ጋዜጠኛ ለእውነት በመቆም ትክክል ነው ብሎ ያመነበትን ነገር ለህዝብ ማድረስ አለበት። ከዛ ማንኛውም ዓይነት አስተያየት ሳይሸበር መቀበል አለበት። ስለዚህ ዳዊት በዳያስፖራዎች አስተያየት እንዲህ መሆኑ ስህተት ነው።

በዳያስፖራ ይሁን በገዢው ፓርቲ ወይም በሌላ ስህተት ሲኖር መተቸት አለብን። እኛ ሌሎችን ስንተች የሌሎችን ትችት በፀጋ መቀበል ይኖርብናል። የዓላማ አቋማችን በሰዎች አስተያየት የሚቀየር ወይ የሚፈተሽ መሆን የለበትም፣ አስተያየቱ ወይ ትችቱ አሳማኝና ተቀባይነት ያለው ካልሆነ በቀር። የሰዎች አስተያየት ትክክል መሆኑ ካመንበት በዛ መሰረት አቋማችንን እንደገና መፈተሽ እንችላለን። ሰዎች እኛን የሚተች አስተያየት ስለሰጡን ብቻ አቋማችን የምንቀይር ከሆነ ግን በትክክል እውነተኛ ዓቋም አልነበረንም ማለት ነው።

ዳያስፖራዎች ዳዊትን የተቹበት ምክንያት የትግራይ ተወላጅ ስለሆነ ነው የሚለው ክስ ግን አልተቀበልኩትም። ምክንያቱም ዳያስፖራዎች ሁሌ የሚጠቀሙት ስትራተጂ ማጥላላት ነው። ይሄ የማጥላላት ስትራተጂያቸው አልደግፈውም። ምክንያቱም ስህተት ነው። የዳያስፖራ የማጥላላት ሰለባ የሆነው ዳዊት ከበደ (የትግራይ ተወላጅ) ብቻ አይደለም። ጃዋር መሐመድ፣ ልደቱ አያሌውና ሌሎች ፖለቲከኞች የማጥላላት ዘመቻው ሰለባ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ስለሆኑ አይደለም።

የዳያስፖራዎች የማጥላላት ስትራተጂ ለሁሉም ነው። እኔው ራሴ ከጃዋር ጋር የማጥላላቱ ዘመቻ ሰለባ ነበርኩ። በጃዋር ላይ የተከፈተው የጥላቻ ዘመቻም በግልፅ ተቃውምያለሁ። ምክንያቱም የማጥላላት ዘመቻው ለሀገር አንድነት የሚጠቅም ሳይሆን የሚጎዳ ነው። ሰውን በመሳደብ አንድነትን ማፍረስ እንጂ መጠበቅ አይቻልም። ዳያስፖራዎች እኛ የማንደግፈው የማጥላላት ዘመቻ ስለሚከተሉ እኛ ኢህአዴግን መቃወም መተው አለብን በሚል ግን አልስማማም። ምክንያቱም እኛ ኢህአዴግን የምንቃወመው ለዳያስፖራዎች ለማገዝ (ወይ ላለማገዝ) ብለን ሳይሆን ለራሳችን ነፃነት ብለን ነው። ስለዚህ የኛ ትግል በዳያስፖራዎች የትግል ስትራተጂ የሚወሰን አይደለም።

በኔና በዳዊት ልዩነት አለ ብዬ አስባለሁ። እኔ ማንም ዳያስፖራ ወይ ሌላ ተቃዋሚ ወይ ገዢው ፓርቲ ለማስደሰት ወይ ለማስከፋት አልተነሳሁም። “ዳዊትስ መቼ ለዚህ ዓላማ ተነሳ?” ልትሉኝ ትችላላቹ። መልሴ ዳዊት እነሱን ለማስደሰት ባይነሳ ኑሮ በነሱ ነቀፌታ ባልተቆጣ ነበር ባይ ነኝ። እኔ እነሱን ለማስደሰት ወይ ለማናደድ ብዬ እስካልፃፍኩ ድረስ እነሱ በሚሰጡኝ አስተያየት አልሸበርም፣ አቋሜን እንደገና አልፈት ሽም። ምክንያቱም እኔ ኢህአዴግን ስቃወም ሰዎችን ከማስደሰትና ከማናደድ የዘለለ የራሴ ዓላማ አለኝ።

የኔ ዓላማ ሰላምዊ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ማገዝ ነው። የሕግ የበላይነት የሚከበርባት ሀገር፣ ፍትህና እኩልነት የነገሰባት፣ ዜጎች በነፃነት የሚኖሩባት አንድነቷ የጠበቀች ሀገር ማየት እፈልጋለሁ። ስለዚህ መቃወሜን የማቆመው እነዚህ እሴቶች በተግባር ሲረጋገጡ እንጂ ዳያስፖራዎች እኔን ማጥላላት ሲጀምሩ አይደለም። ዳያስፖራዎች እኔን ማጥላላት ከጀመሩ የራሳቸው ጉዳይ ነው። እኔ ደግሞ የራሴ ጉዳይ አለኝ። ነፃነት ያስፈልገኛል። ከሁሉም (ከተቃዋሚዎችም ከኢህአዴግን) ነፃ መሆን አለብኝ።

ኢህአዴግን የምንቃወም ሌሎችን ለማስደሰት ከሆነ ዓላማችን ነፃነትን ማግኘት ሳይሆን ገዢውን (የሰው ጌታ) መቀየር ነው (To be free is not to change a slave master; In order for a slave be free, s/he has NO slave master)። አሁን ኢህአዴግን እቃወማለሁ። ሌሎች ኢህአዴግን የመሰሉ ሃይሎች ስልጣን ከያዙ ደግሞ ትግሌን እቀጥላለሁ። ስልጣን የሚይዘው አካል ማንም ይሁን ማን የዜጎች ነፃነት ካላረጋገጠ እቃወመዋለሁ። ስለዚህ ዓላማዬ ድርጅቶች ማገዝ ሳይሆን ነፃነትን ማግኘት ነው።

ስለዚህ አብርሃ ደስታ ከዳዊት ከበደ የሚማረው ነገር ቢኖር ሰው ሲቃወምም ሲደግፍም ትርጉም ላለው ዓላማ እንጂ ግለሰቦች ለማስደሰት ወይ ለማስከፋት መሆን እንደሌለበት ነው። ከዳዊት የምማረው ነገር በሌሎች አስተያየት መቆጣት እንደሌለብኝ ነው። ዓላማየ ሌሎች ድርጅቶችን ማስደሰት እስካልሆነ ድረስ ሌሎች ሰዎች በሚሰጡኝ አስተያየት አልሸበርም። ሁላችን የምንታገለው የግል ነፃነታችን በማግኘት ላይ ያነጣጠረ መሆን አለበት።

 

ከህወሓቶች የወጣ ሚስጢራዊ ደብዳቤ

ከህወሓቶች የወጣ ሚስጢራዊ ደብዳቤ ተቀበልኩ፤ ፊርማና ማህተም የሚመስል ነገር አለው (ማህተሙ በግልፅ አይታይም)። በፓርቲው መወሰድ ስላለባቸው ተግባራት ይጠቁማል። ግን ሆን ተብሎ ለስለላ የተሰራ ሊሆን ይችላል (ደብዳቤው ከሁለት ወር በፊት የተፃፈ ነው)። በደብዳቤው ከተጠቀሱት ነገሮች አንድ ልጥቀስ (ስለደብዳቤው እውነትነት ወይ ሰላይነት ለማረጋገጥ ይረዳልና)።

ኢያሱ ተስፋይ ስለ ተባለ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባል የተፃፈው … ድሮውም ታማኝ እንዳልሆነና ከህወሓት ከፍተኛ ሐላፊነት ወርዶ ወደ ዞን አስተዳደር መቀየር (ከመቐሌ መራቅ) እንዳለበት ያስቀምጣል።

ኢያሱ ተስፋይ የተምቤን ተወላጅ ሲሆን በአንድ ወቅት በማእከላዊ ስብሰባቸው ‘ለምንድነው የሐውዜን ጉዳይ መፍታት ያቃተን?’ ብሎ ጠይቆ ነበር። አሁን በነበረበት ሐላፊነት ነው ያለው ወይስ በደብዳቤው መሰረት ወደ ዞን አስተዳደር ቀይረው ከመቐለ ከተማ እንዲርቅ ሁነዋል???
እስቲ ይጣራ!

የዓረና የማእከላዊ ኮሚቴ አባል ቶርቸር ተደረገ

ጓዶች የዉቅሮ ስብሰባ ሪፖርት ሳላቀርብ ጠፋሁ። የውቅሮ ከተማ የዓረና ቅስቀሳና የህወሓቶች ምላሽ የሚገርም ነበር። እኛ በደንብ ቀሰቀስን። የዉቅሮ ህዝብ የህወሓትን አገዛዝ እንዳንገሸገሸው ተረዳን።

የኛ ቅስቀሳ ሲጠናቀቅ ህወሓቶች የራስቸው ቅስቀሳ ጀመሩ። ‘የመለስ ራእይ…’ እያሉ እንደተለመደው መዘመር ጀመሩ። (በሚቀጥለው ምርጫ የሚጠቀሙት ቅስቀሳ ‘የመለስ ራእይ’ የሚል መሆኑ ከወዲሁ ማወቅ ችለናል)። ወደ ማታ አከባቢም ቤት ለቤት እየተዘዋወሩ ህዝብ በዓረና ስብሰባ እንዳይሳተፍ፣ እያንዳንዱን ወላጅ ልጆቹ ወደ ስብሰባው እንዳይሄዱ መምከር እንዳለበት ካልሆነ ግን መንግስት እንደካደ ይቆጠርና በመንግስት እርምጃ እንደሚወሰድበት ያስፈራሩት ገቡ።

ቅዳሜ ጠዋት (የስብሰባው ቀን) ሁሉም የዉቅሮ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች የስብሰባው አደራሽ በር ላይ ተገኝተው ወደ ስብሰባው የሚገባ ሰው መከልከል ጀመሩ። የነሱ መከልከል ያልበገረው ሰው ደግሞ ፎቶ ማንሳት ጀመሩ። የቀበሌ ሰራተኞች ህዝብ የቀበሌያቸው ሰው መቆጣጠር ያዙ።

ሲገርመን እኛ ደግሞ እነዚህ ህዝብ የሚቆጣጠሩ ሰዎች ፎቶ ማንሳት ጀመርን። (ካድሬዎቹ ፎቶ እንዳናነሳቸው ይፈሩ ነበር)። አንዱ ሲከለክል አይቼው ፎቶ አነሳሁት። ተናዶ ወደኔ እየሮጠ መጣ። ‘ለምን ያለፍቃዴ ፎቶ ታነሳኛለህ?’ አለኝ። ‘አንተስ ለምን ህዝብ ያለፍቃዱ በስበሰባ እንዳይሳተፍ ታደርጋለህ?’ አልኩት። ‘እኔኮ ፀጥታ የማስከብር ፖሊስ ነኝ’ ብሎ መታወቅያውን አሳየኝ። ይገርማል ። ስሙ ተክላይ ይባላል። የዉቅሮ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ነው። ‘ታድያ ፖሊስ ከሆንክ ለምን ፎቶ መነሳቱ አስፈራህ? ሕጋዊ ስራ እየሰራህ ከሆነ ለምን ትፈራለህ?’ አልኩት። ለመግባት የመጣ ሰው የኛ ንትርክ ለመስማት ከበበን። ፖሊስ አዛዡ (ሲቪል የለበሰ ነው) ‘ዞር በሉ’ ብሉ በተናቸው።

እንዲህ እንዲህ እያለ ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ሆነ (ስብሰባው መጀመር የነበረብት 2:30 ነበር)። እኛ በገቡ ሰዎች ስብሰባውን ለመጀመር ወደ አደራሹ ገባን። ከጭቅጭቁ በኋላ ዞምቢዎቹ ሰው በቀጥታ ከመከልከል ወደ በዝምታ መከታተልና በቪድዮ ካሜራ መቅረፅ ተሸጋገሩ።

ስበሰባው ተጀመረ። ህወሓቶች ገብተን ተሰብሳቢውን እንቀርፃለን አሉ። በስሰባው የነበሩ ‘ወጣቶች ህወሓቶች እኛን ለመጉዳት ነው የሚቀርፁት፤ ስለዚህ አስወጡልን’ አሉን። ፖሊስ እንዲወጡ አደረገ። ካድሬዎቹ ከፖሊስ ተጋጩ። ካድሬዎቹና የኛ ሦስት ሰዎች እየተከራከሩ ፖሊስ ጣብያ ዋሉ።

እንዲህ ሁኖ ሰብሰባው በሦስት ሰዓት ተጀምሮ በስምንት ሰዓት በጥሩ መንፈስ ተጠናቀቀ። የህዝብ ብዛት ግን አነስተኛ ነበር። በነበረው መንፈስ መሰረት በሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ጠብቀን ነበር (ካድሬዎቹ ባይከለክሉት ማለት ነው)። የመጣ ግን በመቶዎች የሚቆጠር ነበር። እንዲህ ሁኖም ጥሩ ነው። መልእክታችን በሁሉ ቦታ ደርሷል። ያልሰማ የለም ማለት ይቻላል።

ህወሓቶች ፈሪዎች ናቸው። አቶ ገብሩ አስራት ‘ኢህአዴጎች በግለሰብ አስተያየት የሚደነግጡ ናቸው’ ብሎ ነበር። እዉነት ነው። ህወሓቶች ደንግጠው የዉቅሮ ከተማ በየካቲት 11 እንኳ የማይደረግ ቅስቀሳ ጀምረዋል። ዛሬ እሁድ ህዝብ ለሰለማዊ ሰልፍ እንዲወጣ አስገድደው ሰልፍ ጠርተው ነበር። ሰለማዊ ሰልፍ አይፈቀድም እያሉ ራሳቸው ሰለማዊ ሰልፍ ይጠራሉ። በጣም መደንገጣቸው መበስበሳቸው ያሳያል።

ሰብሰባው አጠናቀን ወደ መቐለ ጉዞ ጀመርን። ስብሰባው ይመሩ ከነበሩ የዓረና አመራር አባላት አንዱ የዉቅሮ ከተማ (አጉላዕ) ተወላጅ የሆነና በ2002ዓም ዓረና ወክሎ የፓርላማ ተወዳዳሪ የነበረ መምህር ይልማ ኩኖም ነበር። እኛ ወደ መቐለ ጉዞ ስንጀምር እሱ ቤተሰቡ ለመጠየቅ ዉቅሮ ቀረ።

የህወሓት ፖሊሶች ተከታትለው ያዙት። ስልኩን ነጠቁት። በፖሊስ መኪና ወደ መቐለ ይዘዉት መጥተው ቶርቸው ሲፈፅሙበት አደሩ። አለን የሚሉት የመግረፍት እርምጃ ካደረሱበት በኋላ አሁን ለቀቁት። መምህር ይልማ ኩኖም የዓረና ፓርቲ የማእከላዊ ኮሚቴ አባልና የዉቅሮ ከተማ ተወዳዳሪያችን ነው። ለ24 ሰዓት ቶርቸር የሚፈፅሙ አምባገነኖች ያልታገልን ለማን ልንታገል ነው? የሚፈፅሙት ቶርቸር ደርጋዉያን ይፈፅሙት ከነበረ የከፋ ነው።

 

ዉቅሮ ነኝ ያለሁት!

ዉቅሮ ነኝ ያለሁት። ነገ ለሚካሄድ ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳችን ጨርሰን አልጋ የያዝንበት ሆቴል ዉስጥ አረፍ ብለናል። የዉቅሮ ህዝብ ለውጥ ፈላጊ ይመስላል፤ አይፈራም። በህዝቡ አቀባበል ተደስተናል።

ከምሽቱ 12:00 ሰዓት በኋላ ቅስቀሳ ማድረግ ስለማይፈቀድ አቁመናል። በቅስቀሳችን የተደናገጡ የከተማው አስተዳዳሪዎች ለብዙ ግዜ ስራ አጥ የነበሩ ወጣቶችና የኮብልስቶን ስራ ተከልክለው የነበሩ ሰራተኞች በማዘጋጃቤት ሰብሰብው የሚቀጥለው ሰኞ (ከቅዳሜ ስብሰባችን በኋላ) ለሁሉም ወጣቶች ስራ እንደሚፈጥሩላቸውና የኮብስቶን ስራ እንደሚጀምሩ ዛሬ ነግሯቸዋል። ዛሬ እንዲፈርስ ቀነ ገደብ ተይዞበት የነበሩ ቤቶችም አይፈርሱም ተብሏል (የዓረና ስብሰባ እስኪያልፍ ማለት ነው)።

ቤት የሚፈርሳቸውና ስራ ተከልክለው የነበሩ ሰዎች በዓረና ስብሰባ ካልተሳተፉ ከሰኞ ጀምሮ ሁሉም ነገር እንደሚደረግላቸው ተነግሯቸዋል።

አሁንም ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ እስካሁን (3:00 ሰዓት ) በትልቅ ስፒከር በመለስ ራእይ ቅስቀሳ እየተደረገ ነው። የመለስ ራእይ ለማሳካት ከሰኞ ዕለት ጀምሮ ለህዝብ የሚጠቅም ስራ እንደሚሰራ ቃል እየገቡ ነው። በመለስ መሬት ዃዂቶ (ቋቚማ) እንደማይበቁል እየዛቱ ነው። ዃዂቶ፣ ጉርዲ ወዘተ የሚሉ ስድቦችም እየተነገሩ ነው።

አልጋ የያዝንበት ሆቴል አጠገብ በስፒከር እየነገሩን ነው። ለህዝቡ ሳይሆን ለኛ ለመንገር የፈለጉ ይመስላሉ። ሆቴሉ በብዙ የደህንነትና የፀጥታ ሰዎች ተጥለቅልቋል። አብዛኝው የሆቴሉ አልጋ በነሱ ተይዟል።

መንግስት ይህን ያህል ይፈራል እንዴ? በጣም ነው የገረመኝ።

በእውነት ኢህአዴግ እንዲህ ፈሪ ከሆነ በሚቀጥለው ሀገራዊ ምርጫ ሙሉ በሙሉ የምናሸንፈው ይመስለኛል።

ከዓድዋ የተላከልኝ አስተያየት!

አንድ የፌስቡክ ወዳጄ በዉስጥ መስመር የላከልኝ እንዳለ ልለጥፈው ወድድኩ።

“የተከበርክ መምህር ኣብርሃም፣ ስለ ዓድዋ የፃፍከው ፅሁፍ አነበብኩኝ፡፡ በርግጥ አንድም ቀን ራሴን እንደተቀዋሚ ቆጥሬ አላውቅም፡፡ ይህ ማለት ግን ራሴን የማላውቅ ደጋፊ ነኝ ማለት አይደለም፡፡ በአድዋ ከተማ በአስተማሪነት ለአስራ አምስት አመታት ያክል አገልግያለሁ፡፡ ስለሆነም ነው አንተ በአድዋ ከተማ ተዘዋውሬ የሰማሁት የመልካም አስተዳደር እጦትና የነዋሪው ብሶት ብለህ የፃፍከውን ፅሁፍ ለማጣጣል የተነሳሁት፡፡ ውድ አብርሃም በርግጥ አንተ ያየሀው የመልካም አስተዳደር እጦት ይህ ብቻ ከሆነ፤ በጭራሽ አድዋ ከተማ አልመጣህም፡፡ ብትመጣ ኖሮ በከተማ ያየኸውን የጥቂት ግለሰቦች ችግር ብቻ ባላነሳህ ነበር፡፡ በአድዋ ከተማ የሚታየውን የመልካም አስተዳደር እጦትና ብሶት ለማየት በከተማው የሚገኙ መምህራንን ማነጋገር በቂህ ነበር፡፡ ሕወሓት በአባልነት የሚመለምላቸው የስራ ፍቅር የሌላቸው፣ ወሬ የሚያቀባብሉ፣ የሚያስተምሩትን የትምህርት ዓይነት በቅጡ ማሸነፍ የማይችሉ፣ ሀገራዊ ስሜት የሌላቸው፣ በአጠቃላይ የህዝቡንና የሃገሪቱን ሃብት በማባከን ተወዳዳሪ የሌላቸው ናቸው፡፡ አንተ ያላየኸው እኔ የማውቀውና እነሱም አፋቸውን ሞልተው የሚናገሩበት አንድ ነገር ልንገርህ፤ ትምህርት ቤት ማለት ከፖለቲካ፣ ሃይማኖትና ሌሎች የፀዳ ክልል ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ግን በትምህርት ቤት ውስጥ የፖለቲካ እምነታቸውን በውድ ሳይሆን በግድ እያስፋፉ ነው፡፡ ለምሳሌ በኛ ትምህርት ቤት ውስጥ /ንግስተ ሳባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/ ዲፓርትመንት ሄድ፣ የክለብ አስተባባሪ፣ ዩኒት መሪ፣ ወዘተ ለሕወሓት አባላት የሚሰጡ እንጂ በመማር ማስተማር ሂደቱ ንቁ ተሳትፎ ላለው አስተማሪ የሚሰጡ አይደሉም፡፡ በትምህርት ቤቱ የሚገኙ ተማሪዎች እድሜያቸው ከ18 በታች ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሳይፈልጉና ሳይነገራቸው የሕወሓት የአባልነት ክፍያ የሚከፍሉና እንደአባላት የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ዘንድሮ 2006 ዓ.ም የተማሪዎች የአባልነት ክፍያ ተማሪዎቹ ሳያውቁና ሳይነገራቸው ከትምህርት ቤት መመዝገቢያ ክፍያ ጋር እንዲከፍሉ ተደርጓል፡፡ በርካታ በመማር ማስተማር ሂደቱ ንቁ ተሳትፎ ያላቸው መምህራንም አባላት ባለመሆናቸው ምክንያት ይገለላሉ፡፡ ለምሳሌ ባለፈው አመት አራት አስተማሪዎች ለሕወሓት አባላት መልካም አስተያየት የላችሁም፣ አባላትን ትገመግማላችሁ ተብለው ከብሄራዊ ፈተና እንዲገለሉ ተደርጓል፡፡ እኔም ብሆን የሕወሓትን አባላት ታንቋሽሻለህ ተብየ በተዘዋዋሪ 2500 ብር ተቀጥቼ እየከፈልኩኝ ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፤ በአድዋ ከተማ በተለይ አስተዳደሩ አከባቢ የሚገኙ ሰዎች ህዝቡ አያስፈልጉንም እያለ ብሶቱን እያሰማ ግን መልካም ሰዎች ከአስተዳደሩ እንዲባረሩ እየተደረገ እነዚህ ህዝቡን ወደከፋ ብሶት የሚመሩ ሰዎች እንዲመሩ እየተደረገ ነው፡፡ የተሰራ ስራ ሳይኖር በሪፖርት ብቻ ከተማዋ ደህና እንደሆነች እየተደረገ ይነገራል፡፡ ኧረ ሁሉን ብታወራው ማለቂያ የለውም ባክህ፡፡ ምን ዋጋ አለው እናንተም እየጠነከራችሁ አይደለም፡፡ በርቱ!”

የተከበርክ ወዳጄ…
በነዚህ ነጥቦች ያላተኮርኩበት ምክንያት በሌላው የትግራይ አከባቢዎችም የተለመዱ በመሆናቸው ነው። ለሰጠኸኝ አስተያየት አመሰግናለሁ።

 

ለዉቅሮና አከባቢዋ ኗሪዎች!

ዓረና ትግራይ ፓርቲ ነገ ቅዳሜ ጥቅምት16, 2006 ዓም በሚሊንየም አዳራሽ (ዉቅሮ) ከጠዋቱ 2:30 በወቅታዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ከከተማው ህዝብ ጋር ይወያያል። የቻላቹ በህዝባዊ ስብሰባው እንድትገኙ ተጋብዛችኋል። ኑና እንወያይ፣ እንከራከር፣ እንጠያየቅ፣ እንገናኝ።

ጥረታችን ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም እንቅስቃሴያችን ሁሉ ትርፍ እንጂ ኪሳራ የለውም። ምክንያቱም ዓላማችን የኢህአዴግን መንግስት በሌላ ህዝባዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት መተካት መቻል ነው።

ከኢህአዴግ የተሻለ ዴሞክራሲ የሚያሰፍን፣ ልማትና ፍትሕ የሚያረጋግጥ፣ የዜጎች ነፃነት የሚያከብር መንግስት እንመሰርታለን ብለን ቆርጠን ተነስተናል። የምንመሰርተው መንግስት ከኢህአዴግ የተሻለ ባይሆንስ? አዎ!ስልጣን የምንይዝበት መንገድ ሰለማዊ እስከሆነ ድረስ ስልጣን ይዘን ከኢህአዴግ መንግስት ባንሻል እንኳ ለመጀመርያ ግዜ ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር እዉን ስለሚሆን ይህ (ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር) በራሱ በኢትዮዽያ የፖለቲካ ታሪክ ትልቅ አስተዋፅዖ ሁኖ ይመዘገባል። ስለዚህ ትግላችን ዋጋ አለው።

ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር እዉን ማድረጉ ባይሳካልንስ? ያው መንገዳችን ህዝብ በማስተማር የፖለቲካ ለውጥ ማምጣት እስከሆነ ድረስ ስልጣን መያዙ ላይ ባይሳካልንም ህዝብ ስለ ዴሞክራሲ ማስተማርና አማራጭ ሁኖ መቅረብ በራሱ ትልቅ የዴሞክራሲያዊነት አስተዋፅዖ ነው።

ስለዚህ ጥረታችን በማንኛው መልኩ ለሀገራችንና ህዝባችን ጠቃሚ ነው። ነገ በዉቅሮ ከተማ እንገናኝና እንነጋገር።

ነገ ጠዋት ዉቅሮ ነኝ።

It is so!!!

It is so!!!

 

 

10 Comments

 1. Well done dear Abraha Desta (Dagmawi Alula)’

  I have been following your comments lately and decided to encourage you to continue until the regime restricts your movement. The reason why I say this is because we Ethiopians specially those who genuinely advocate unity, peace, equality and justice to flourish, know that all these fundamental human rights and needs will not be possible in Ethiopia, as long as the present regime stays in power. We all know that the numerous cost of human life and the damage that has done to our generations by the regime’s hate politics and dividing our society along ethnic lines. It is not only backward and cruel as a policy but it is also it will never benefit any one the creators themselves.

  So little brother Abraha, keep your fight up for our common agenda as long as you can until freedom, equality, justice and we Ethiopians achieve peaceful transition of power. Where power will restore back to the people, by the people and for the people.

  As you rightly said it is not Dawit or other individuals who should not be our measurement to guide us to do or not to do the right thing. Yes as you said, it is the truth and the correct thing we believe in and we love doing just that which determines our action to go further until that is achieved.

  I will keep in touch,

  Thank you,

  Keep writing,

  Best regards,

  Fikirte

 2. From- GETACHEW REDA (Editor Ethiopian Semay)

  ብዙ የተበሻቀጠ የባንዳ ትምህርት አስተማሪ እና ተቀባይ ተማሪ እንደ ጉንዳን ተራብቷል። ከትግራይ እስከ ምስራቅ ከደቡብ እስከ ምዕራብ በግንጣለ ስራ እና በዘር ማጥፋት ተግባር የተሳተፉ የድርጀት መሪዎች እና ግለሰቦች በሕብረተሰቡ ዘንድ ምንም ዓይነት ቅዋሜ እንዳይደርሳቸው የሚቀሰቅሱ ወጣቶች በብዛት እየተፈለፈሉ ነው። ለዚህ ማስረጃ የሚሆነን በወያኔ ዘመን የተወለዱ ወይንም ህጻናት የነበሩ ወጣቶች ዛሬ አድገው ባደጉበት የተመረዘ የፖለቲካ ትምህርት በመዋኘት ግንጠላም ሆነ የዘር ማጥፋት ቅስቀሳ የሚያስተምሩ እንደ እነ ጃዋር መሐመድ የመሳሰሉት አደገኛ ‘የሰው አንስሳት’፤ ከትግራይ ከመቀሌ ‘አብርሃ ደስታ’ እያለ ራሱን የሚጠራ ወጣት ‘ተራቢ’ እና የዓረና ድርጅት አባል ‘በፌስ ቡክ’ እና ዘሐበሻ በተባለው ድረገጽ የሚያሰራጨው የነቀዘ ቅስቀሳው ‘ለጃዋር መሐመድ’ (ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ሶማሊያ! ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ኦሮሚያ! ፈካሪ) ድጋፍና ቅስቀሳ በተደጋጋሚ (ለሦስተኛው ጊዜ ነው) ድጋፍ እየሰጠ አንደ እሱ የመሳሰሉ የተበከሉ አገራዊነት በቅጡ ያልተረዳቸው “ግማሽ ሊጥ” ወጣቶችን በማጃጃል (የሳብቨርሲቭ) የግዝገዛው ተዋናይ እየሆኑ የመጡበት ወቅት ስለሆነ የአንድነት ሃይሉ፤ በተለይ ምሁራን እዚህን “ግማሽ ሊጥ” የሆኑ ወጣቶች የጥቃቱ ዘመቻ (የሳብቨርሲቭ ወኪሎች) እየሆኑ የግዝገዛው ሱታፌአቸውን ከማስፋፋታቸው በፊት፡ መቋቋም የሚችል አዲስ ትውልድ ማስተማር ለነገ የማይባል አጣዳፊ የቤት ስራችን ነው።

  በጃዋር መሐመድ የሚመራው “ኢትዮጵያ አውት ኦፍ ኦሮሚያ፤ እና “የክርስትያን አንገት የቆረጣ አብዮት” የኦነግ ፕርንሲፕል ዘመቻ ደጋፊ ሆኖ “እፍ እፍ” በሉት እያለን ያለው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲው መምህር ወጣቱ አብርሃ ደስታ ምክንያት በመርህ ደረጃ ምንም የሚለያቸው ነገር የለም። የአብርሃ ደስታ ዓረና ፓርቲ የሚመራው ቀደም ብለን አንደምናውቀው ዓረና እያለ ራሱን የሚጠራ “Group -B- WeYane” ከ6 አመት ዝምታ በሗላ ‘አንቀጽ 39’ ይዞ ‘ዓረና ትግራይ…’ ብሎ ወደ ፖለቲካው መድረክ በመውጣት ከመለስ ጋር የተጣሉት (Group B Tegaru ብየ የጠሯሗቸው) ከመለስ ቡድን (Group A Weyane) ጋር ‘የተቃቃሩት’ በውስጥ እና በውጭ አገር የሚኖሩ አያሌ ትግሬዎችን እና ሌሎች ጥቂት ውዥምብራም ኢትዮጵያዊያን ሲደገፍ ኦነግ እና ወያኔ የተከተሉት አንቀጽ 39 እስከ መገንጠል የሚለው መርህ ይዞ አንደመጣ መርሳት የለብንም። ስለሆነም የዚህ ወጣት ‘ግማሽ ሊጥነት’ እና ‘ወጣሁ ወጣሁ’ ባይነት መሰረት አለው ማለት ነው።ይህ ወጣት ‘እኛን ሲከስስ” (ጃዋርን ማጥላላት) የሚለው አማርኛ ነበር የተጠቀመው። ማጥላላት ትርጉሙ የገባው አይመስለኝም። እባካችሁ አማርኛ ምታውቁ ሰዎች “የማጥላላት” ትርጉሙን ንገሩት።

  የተኩላ ቀይ ወጥ፤ የእባብ ቅቅል ስጋ ሰርተው ሊያበሏችሁ ከሚመክሩ “ቦሶሮ ፖለቲከኞች” ተጠንቀቁ። ጃዋርን በመጥፎ ስም የሚነሳ ስላልሆነ ጃዋርን በመጥፎ ስም አታንሱት እያለን ነው። ለምን? የሚለው ሲመልስ “ካሁን በፊት በጃዋር መሪዎች አንገታቸው በማቸት ስለ ተቀሉ አማራዎች ፤ቀሳውስት እና መነኰሳት አያገባችሁም። ጃዋር ከኦሮሚያ ውጡ ቢላችሁም “እሺ ብላችሁ” መውጣት ብቻ ነው! እሱን ገዳዮቻችሁን ‘እፍ እፍ’ ካላላችሁ ወደ ወሎ፤ ወደ ጎኝደር፤ ወደ ሸዋ፤ ወደ ጞጃም ወደ መሬታችሁ መሄዳችሁ ነው። እንዳትባረሩ፤ እንዳትቀሉ ዛሬም አትናገሩ አትተንፍሱ፤ አፋችሁ ክደኑ! እያለን ነው የወያኔው ‘Group B ’አመራር አባል አብርሃ ደስታ። ሱቕ ጡዑም! ትላለች እናቴ። ሱቕ ጡዑም የአክሱም ተወላጅ ነው፡ የቤታችን የቅርብ ወዳጅ ነበር። በአባቱ በጣም ከታወቁ ተወላጆች ቤተሰብ በኩል ነው። እናትየው በግርድና ሲኖሩ የነበሩ በጣም ‘ጥቁር ቆዳ” የነበራቸው ሴት ወይዘሮ ነበሩ። ተወልጄ አባቱ በድብቅ ስለለመዷቸው ይህ ልጅ ተወለደ። ከገረዳቸው የተወለደው ልጅ እሳቸውም መምሰል ትቶ የናቱ ቀለም በመያዙ “ሱቕ ጡዑም” አሉት። ዝምታ ወርቅ ነው፡ ማለት ነው። ባርያ ብሎ ሲሰድቡት እሱም “ሱቕ ጡዑም” ብሎ ይመልስላቸው ነበር። ዝምታ ደጉ። አክሱም ውስጥ በቻይነቱ በጣም የታወቀው “ሱቕ ጡዑም” በባሕሪው የማይና ሰው አልነበረም። ታዲያ ሁሌም እናቴ አስገራሚ ነገር ሲገጥማት “ሱቕ ጡዑም” ትል ነበር። እኔኑን የገረም ነገር ደግሞ ‘አብርሃ ደስታ’ የተባለው አዲስ ወጠጤ “በጃዋር ላይ የተከፈተው የዲያስፖራ ተቃዋሚ የጥላቻ ዘመቻ እቃወመዋለሁ” ብሎናል። እኛ ነን በጃዋር የጥላቻ ዘመቻ የከፈትነው ወይስ ጃዋር ነው? “ ኢትዮጵያ የምትባሉ ክርስትያኖች፤ አማራዎች እና መሰል ኢትዮጵያዊያኖች ዓይናችሁን ማየት ስለምጠላ “ሶማሌ” እና ‘ኦሮሚያ” ከሚባለው ከአገሬ ውጡ!” ያለን ማነው? የውጡ! ዘመቻ ተከፈተብን አንጂ እኛ የጥላቻ ዘመቻ ከፋቾች አድርጐ እየወነጀልለን ያለው ይህ የ ‘ቡድን ቢ ወያኔ’ አባል ውስጠ ምስጢሩ ምን ይሆን? አመሰግናለሁ። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ አዘጋጅ)

 3. Dear Abraha Desta,
  I read your threads with mixed reaction. you have said so much about the TPLF tyrants who have deprived the people of Tigrai from basic freedom. While this is true, its also not new. I doubt Arena is going to score any success simply because its founding members are the likes of Gebru Asrat, who willingly gave away our port to Eritrea and ironically, he is now openly advocating in favor of just that which makes me grow suspicious about ex TPLF members-turned-opposition leaders. One more thing that’s bothersome about the things you wrote with regard to the saboteur and anti Ethiopia extremist Jawar: I don’t think you know the level and magnitude of hate and vilification that this bigot harbors against Ethiopia. What’s more foolish is that he released a statement which I read in this site as a response to the outcry that he faced as a result of the anti Ethiopia youtube video in which he wrote with brutally unapologetic demeanor exhibiting a rigid attitude claiming that the video has been “doctored.” So if you are trying to defend him without checking the facts firsthand, I will give you the benefit of a doubt. If you condone the racist and anti Ethiopian principle that this mad man called “Jawar” holds however, you are drifting in to the camp of anti Ethiopia anarchists and about time you reexamine yourself as to where you stand in the context of our country’s unity. I strongly support what you stand for (judging from your writing) but you seem to be confused as to the the elements of destruction that have hatched as an outcome of Meles Zenawi’s divide-and-rule policies whose motto is the much despised article 39. Jawar is a poster child of article 39 and he also has an outrageous agenda that he calls “the oromo cause” Bull****

 4. Getachew,
  “ajewjew as usual” why can’t you tackle the contents that Abraha has raised which you don’t agree with instead of showering him with all kinds of names without even considering the patriotic mission up on which he has embarked. I think you are just here to advertise your “ethiopian semai” which I have no clue what the heck the purpose of it is. Abraha’s mission and objective is clear as day light. What is yours? for some weird reason,you just set up your little “ethiopian semai” in order to castigate and vilify knowledgeable and patriotic Ethiopians. I once visited your “blog” and sow your picture “dashing” in Elvis-era white suit that made you look more like a “tenquay” lol j/k. Anyways, I think you are just an attention-seeking goon who is getting old and unable to tolerate diverse views. You can criticize Abraha without resorting to name-calling. But change is hard to come by for some one like you who has dwelt in the business of slandering other Ethiopians for so long. It’s impossible to teach an old dog a new trick….as they say….

 5. I asked Andinet/UDJ representative in Qale Room recently what Abraham Desta recently blogged, ” UDJ for not being trusted by the people of Tigray”. The guest totally rejected that as wishful thinking.

  If Woyane believes what Abraham suggested there was no need of intimidating the pubic not to join UDJ in its public gathering in Mekelle, Why is Woyane intimidating “Arena” a Tigrean speaking opponents of the regime ? Was it not by accusing Arena as “Amhara lovers” ??

  Abraham Desta defending Jawar Mohammed should be seen from this angle. Both are the victims of the last 22 years of “Anti Amhara” ideology wrapped in the name of empowering nations and nationalities.

  The Ethiopian people said no in 2005 to such ideology of hate. Almost a decade after that Abraham Desta and Jawar Mohammed are playing the ethnicity card to divide our people.

  Jawar Mohammed said in public “Ethiopia Out of Oromia”. What Abraham Desta has not yet said so far is “Ethiopia Out of Tigrai”. He is very close to that by telling us that non Tigrean opposition are not trusted in Tigrai.

  Abraham Desta might not accept UDJ/Andinet in his “Republic” but he should know that the Ethiopian people from all the regions died in defending that part of Ethiopia many times in their history. Did he forget the 1998-2000 sacrifice in Badme War. Do not tell us the people of Tigray are not welcoming Woyane opponents in Tigray.

  We need to challenge people like Abraham Desta and Jawar Mohmmed who do not want popular change that will bury Ethnic Divide and Rule. Both Tirgrai and Oromia are Ethiopian and anyone who is telling us otherwise is Woyane Lover !!

 6. Dear all respondents, are you still defining hero in such away, abrha desta is not a person that can represent him self. this is because
  he is simply a populist and he is well disabled to explain him self rather he is the mouse of gebru and asgede. I know him personally he can’t explain what he is writing becuase he is simply posting written documents by prayers. please don’t try tell as about tigray and TPLF we already know them how they are integrated. some of you are sugesting on abrha’s view with out having any evidence. this shows simply your irrationality. please think rational and let us work together for the betterment of our country Ethiopia. am not surprising with Abrha’s idea because he has no ajenda but i am telling you to be your self unlike Abrha.

 7. Toggling between letterbox mopde and fullsceen mode is possible jst by
  double tapping on screen. Since you have got the flexibility to pick an area code other than the one
  you reeside in, this may cause issues if you must use the system.

  After that, you figure ouut what’s wrong with the devie and then repair it with
  ordered parts.

 8. Simply wish to say your article is as surprising.
  The clearness to yyour submit is just cool and i can think you’re a professional on this subject.
  Fine with your permission allow me to grasp ylur RSS feed to keep updated with forthcoming post.
  Thanks a million and please keep uup the rewarding work.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.