ደስተኛ ለመሆን መደረግ የሌሉባቸው 10 ጉዳዮች

1 min read


1. ሙስና አለመስራት (የምትፈልገውን ለማስፈፀም ተገቢውንና ህጋዊውን መንገድ ተጠቀም እንጂ ሙስናን ፈፃሚም ሆነ አስፈፃሚ ከመሆን ራቅ)
2. ራስህን አታወዳድር (ሁሉም ሰው በራሱ ልዩነት ያለውና የራሱ ፍላጎትና መንገድ እንዲሁም ልዩ አካባቢያዊ ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ ራስህን ከሌሎች ጋር በማወዳደር የበላይም ሆነ የበታችነት ስሜትን አትፍጠር፤ ደስታህን ታጣለህ)
3. አታማር (ምሬት ደስተኝነትን ይነጥቃል፤ የበለጠ ምሬትንም ባብሳል፡፡ ምሬት ኃላፊነትን ለመውሰድ ካለመፈለግና ለጥቀፋትም ለሌሎች በምክንያትነት ከመፈረጅ የሚመጣ ነውና አትማረር/አታማርም፤ ችግሮችን ከምትማረርባቸው ተማርባቸው)
4. ከአፍራሽ ትችት ራቅ (ትችት ሰዎችን የሚገነባ በሆነ መልኩ ደስታን ይፈጥራል፤ ሰዎችን ሆን ብሎ ለመጉዳት ታስቦ በተደረገ ቁጥር ደግሞ የራስንም ደስታን ይጥቃልና ከአፍራሽ ትችት ራቅ)
5. ከአደንዛዥ ዕፆች ራቅ (እነዚህ ለጊዜው የሚያስደስቱ ቢመስሉም በሂደት ግን ጭራሽ ጥገኛ በማድረግ ደስታንና የመኖር ተስፋን ይሰርቁሃልና ስሜት፣ ሲጋራ፣ አልኮልና ሌሎች አደንዛዥ ዕፆች አጥብቀህ ራቃቸው)
6. ታይታንና ውዳሴን አስወግድ (በአኗኗርህ ከሌሎች በልጠህ ለመታየትም ሆነ በሰዎች ሙገሳም ለመደሰት አትሞክር፤ እነዚህ ቋሚ የደስታ ምንጭ አይደሉምና፡፡ ቅንጦት መሳይ የታይታ አኗኗሮችን እንዲሁም ስልጣንና ማዕረግን ለማግኘትም ሆነ ይዞ ለማቆየት የሚያስከፍሉት ዋጋ ውድ ሲሆን ሲያጧቸውም መጥፎ ችግር ውስጥ ይከታሉና ኑሮህ መሃከለኛ ይሁን)
7. ድህነትን አስወግድ (ድህነት የብዙ ማጣቶች መገለጫ ሲሆን በማጣት ውስጥ ዘላቂ ደስታን ማጣጣም አይቻልም፡፡ ሰዎችን በመጥቀም ውስጥ ሃብትን በየጊዜው መገንባት ግን ያስደስታልና አጥብቀህ ብልፅግናን ፈልገው)
8. ውጥረትን አስወግድ (ህይወት የድርጊቶች ጥርቅም ናት፡፡ ሁሉም ስራዎች ውስጥ ራስህን አትክተት፤ ጥቅም የሌላቸውን አስወግድ፡፡ ጠቃሚዎችንም ለሌሎች አካፍል፡፡ ሰዎችንና ቴክኖሎጂን በመጠቀም ኃላፊነቶችህን ቀንስ፡፡ ያኔም ሰላም ይሰማሃል፡፡ ደስታህም ይጨምራል)
9. አትቅና (በሌሎች ስኬትና ማማር መቅናት የሌለብህ ሌሎችን እንዳትጎዳ ሳይሆን አንተ ራስህ ደስታህን በማጣት እንዳትጎዳ ነው፡፡ ይልቅስ የበለጠ ደስ ይበልህ፡፡ የበለጠ ይስካላቸውም ዘንድ ተመኝላቸው፡፡ ያኔም የእነሱ ስኬት፤ ውበትና ደስታ ወዳንተም ይመጣል)
10. አትፍራ (እታመማለሁ፤ አረጃለሁ፤ ወይም እሞታለሁ ብለህ አትፍራ፡፡ እነዚህ ተፈጥሯዊ ለውጦች ናቸው፡፡ ማድረግ ያለብህን ጥንቃቄ በማድረግ ከለውጡ ጋር በደስታ መኖር እንጂ የማይቀረውን በመፍራት ደስታህን አትጣ፤ ሲመጣ ተቀበለው)

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.