ፊፋ አሳውቁኝ ባለ ማግስት ዳኛውን የደበደበው የወልዋሎ ቡድን መሪ አቶ ማሩ ገብረጻድቅ ከማንኛውም የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ዕድሜ ልክ ታገደ

Filed under: News Feature,ስፖርት,የዕለቱ ዜናዎች |


ብስራት ራድዮ የዘገበው እንደወረደ:

በ22/08/2010 በአዲስ አበባ ስታዲየም ከመከላከያ ጋር በተደረገው የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ላይ የተፈፀመውን ጥፋት በሚመለከት ከጨዋታ አመራሮች የቀረበን ሪፖርት ተንተርሶ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ ውሳኔ ማስተላለፉን ብስራት-ስፖርት አረጋግጧል።

የእለቱን አርቢትር እያሱ ፈንቴን የመታው የቡድን መሪ አቶ ማሩ ገብረፃድቅ ከማንኛውም የእግር ኳስ እንቅስቃሴ እድሜ ልክ እገዳ ተጥሎበታል። በቡድን መሪው ጥፋት ምክንያት ተያይዞ የተጣለውን የገንዘብ ቅጣት (20ሺህ ብር) ክለቡ እንዲከፍል ተወስኗል።

የወልዋሎ ተጫዋቾች በረከት አማረ፣ አለምነህ ግርማ፣ አስሪ አልማህዲ፣ ማናየ ፋንቱ፣ በረከት ተሰማ እና አፈወርቅ ኃይሉ ለስድስት ወራት እንዲታገዱ እንዲሁም እያንዳንዳቸው ብር 10ሺህ ቅጣት እንዲከፍሉ ተወስኗል። ሌላው የወልዋሎ ተጫዋች ዋለልኝ ገብሬ የሁለት ዓመት እገዳ እና የ15ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎበታል። ወልዋሎ በጨዋታው የፎርፌ ተሸናፊ እንዲሆንና 250ሺህ ብር መቀጫ እንዲከፍል ውሳኔ ላይ ተደርሷል። የማስጠንቀቂያ ደብዳቤም የተላከላቸው ሁለት የቡድኑ አባላትም አሉ።

የመከላከያ ተጫዋቾች የሆኑት ፍፁም ገብረ ማርያም እና ዳዊት እስጢፋኖስ እንዲሁም የወልዋሎው ተጫዋች ተስፋዬ ደበበ በእለቱ ዳኛውን ከአደጋ ለማዳን ላደረጉት ጥረት የምስጋና ደብዳቤ እንዲደርሳቸው ተወስኗል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.