/

ሃጫሉ ሁንዴሳ መኪና ተሸለመ | ቴዲ አፍሮ በሰሜን አሜሪካ የተሳካ ኮንሰርቶችን በተለያዩ ከተሞች እያቀረበ ነው

1 min read

 


(ዘ-ሐበሻ) ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ በሙያው እያደረገ ላለው የትግል አስተዋጽኦ በሚል በባለሃብቶች የመኪና ሽልማት ተበረከተለት::

ዜናውን በቪዲዮ ለማየት እዚህ ይጫኑ

በካናዳ ካልግሪና ቶሮንቶ ከተሞች የሙዚቃ ሥራዎቹን አቅርቦ ወደ አዲስ አበባ የተመለሰው ሃጫሉ በኦሮሚያ ቄሮ ላደረገው ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል;’ ለዚህም ሽልማት ይገባዋል በሚል ትናንት በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል በተካሄደ ስነ ሥርዓት የኦሮሚያ ባለሃበቶች መኪና ሸልመውታል::

ድምጻዊው መኪናውን ሽልማት ከተረከበ በኋላ ሸላሚዎቹን አመስግኖ ወደፊትህም ከሕዝብ ጎን እንደሚቆም ገልጿል::

በሌላ ዜና በሰሜን አሜሪካ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን እያቀረበ የሚገኘው ድምጻዊው ቴዲ አፍሮ ዛሬ ቅዳሜ. ምሽት በኦሃዮ የሙዚቃ ሥራውን እንደሚያቀርብ ታውቋል:: ድምጻዊውና 13 የባንድ አባላቱ በትናንትናው ዕለት ኦሃዮ የገቡ ሲሆን በኢትዮጵያ ባንድሪያ ያሸበረቁ ኢትዮጵያውያን አቀባበል አድርገውለታል::

ቴዲ አፍሮ ከ2 ሳምንት በፊት በዋሽንግተን ዲሲ ያዘጋጀው ኮንሰርት ወደ 6 ሺህ የሚጠጋ ሰው እንደታደመው ታውቋል:: በአትላንታ; በኦክላንድ; በሎሳንጀለስ እጅግ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ህዝብ በመግባት ኮንሰርቶቹን ታድመዋል:: በቀጣይም ዛሬ በኦሃዮ ሥራዎቹን ካቀረበ በኋላ በላስቬጋስ; በሲያትል; በሚኒሶታና በዳላስ ከተሞች ሥራዎቹን እንደሚያቀርብ ከወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት ተችሏል::

ቴዲ በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ከተሞች እየተደደረገለት ላለው ከፍተኛ አቀባበል ህዝቡን በየመድረኩ እያመሰገነ ነው::

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.